በከተማ አስተዳደሩ ባለፉት 6ወራት በገቢና በማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ስራዎች የህዝቡ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች በቅንጅት ማከናወን ተችሏል።
ጥር 26/2018ዓ.ም [ወልቂጤ ]
በከተማ አስተዳደሩ የአንደኛ ግማሽ አመት 5 መቶ 29 ሚሊዮን 7መቶ 36ሺ 9 መቶ ሀያ ብር ገቢ አሰባሰብ መቻሉ ተገለፀ።
1ኛ ግማሽ ዓመት የገቢ አሰባሰብ ውጤታማነት ለማሻሻል ይሰበሰባል ተብሎ 5መቶ 76 ሚሊዮን 2መቶ 89 ሺ 326 መቶ 50ሳንቲም ታቅዶ 5 መቶ 29 ሚሊዮን 7መቶ 36ሺ 9 መቶ ሀያ ብር መከናወኑን የተገለፀ ሲሆን ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 2 መቶ 8 ሚሊዮን 2 መቶ 96 ሺ 44 ብር ብልጫ ያለው ገቢ ተሰብስቧል።
ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የሚሰሩ ተግባራቶች ላይ ለውጥ እንዲመጣ ትግል በተደረገው መሰረት የደረጃ “ሐ” በአሁኑ በተቀየረው አዋጅ ደረጃቸው “ለ” የሆኑ ግብር ከፋዮች 746 አዳዲስ ግብር ከፋዮች መመዝገብ ተችሏል።
የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ጋር የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት በተለያዩ ዘርፎች የደረጃ ሽግግር ስራ በትኩረት በመምራት የፍትሀዊነት ጥያቄ ለመፍታት በግማሽ አመት 101 የተጨማሪ እሴት ታክስ ግብር ከፋዮችን መመዝገብ ተችሏል።
ግብር ከፋዮች አሰራራቸውን እንዲያዘመንኑ በግማሽ ዓመት 25 የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን ማሰራጨት ተችሏል።
እንዲሁም ለ6257 ግብር ከፋዮች የፊት ለፊት ስልጠና እና ቤት ለቤት ድጋፍና ግንዛቤ የማሳደግ ስራ መስራት ተችሏል።
በከተማ ማዘጋጃ አገልግሎት የማህበረሰቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት በበጀት አመት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ከሚሰሩ የልማት ስራዎች ከገብርኤል -ሰጎመ የሚሰራው አስፓልት 1.26 ኪ.ሜ የአስፓልት መንገድ ስራ 92% በላይ ፣ 7.6 ኪ.ሜ የኮሪደር ልማት በዲዛይኑ መሰረት ተሰርቷል፣የጎርፍ መከላኪያ ቦይ ግንባታ፣አዲስ ጠጠር መንገድ ግንባታ ፣አዲስ ጠጠር መንገድ ከፈታና ጠረጋ፣የመንገድ መብራት ዝርጋታ እና ከልቨርት ግንባታ በበጀት ዓመቱ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ተከናውኗል።
መሬት ልማትና አስተዳደር ስራዎች ለንግድ /ኢንቨስትመንት 3.9861 ሄክታር ፣ቤት ለሚገነቡ ማህበራት 1.ማህበራት 1.8775 ሄክታር ፣ለግል መኖሪያ ቤት ሰሪዎች 2.1714 ሄክታር ፣ለከተማ ግብርና 1.12 ሄክታር ፣ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት 6.3416 ሄክታር እና ለኢንዱስትሪ ልማት 9.04 ሄክታር በድምሩ 24.5366 ሄክታር መሬት ማዘጋጀት ተችሏል በከተማው ውስጥ የደቀቁና ያረጁ አካባቢዎችን በመልሶ ማልማት 0.24 ሄክታር ታቅዶ 0.465 ተሰርቷል።
በመልሶ ማልማት ምክንያት ከይዞታቸው ለተነሱ ባለመብቶች ምትክ የሚሆን 0.11 ሄክታር መዘጋጀቱን የተገለፀ ሲሆን ቤት ለሚሰሩ ማህበራት ፣የግል የመኖሪያ ቤት፣ለኢንቨስትመንት እና ለከተማ ግብርና በጠቅላላ 8.6823 ሄክታር ማስተላለፍ ተችሏል ።
የመንግስት ቤቶች በፍትሀዊነት ለተጠቃሚዎች በኪራይ እንዲተላለፉ የተደረገ ሲሆን ቤቶችን ውል እድሳት የማድረግ እንዲሁም የግል ቤት ሰርተው ይዞታ ያላቸውና በመንግሥት ቤት የሚኖሩ ግለሰቦች የማስለቀቅና በህግና መመሪያ መሰረት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን የማስቻል ስራ ተሰርቷል ።

