በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት 1ኛ አመት 1ኛ ዙር ጠቅላላ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ አካሄደ።
ጥር 24/2018ዓ.ም [ወልቂጤ]
እስልምና ጉዳዮች ምክር ጉባኤውም በተከበረው ቅዱስ ቁርአን በኡስታዝ ሚስባህ ቀርቦ ተጀምሯል።
በምክር ቤቱ ጉባኤ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እንዳሉት እስልምና የሰላም፣ የወንድማማችነት፣ የመቻቻልና የሰው ልጆች እዝነት አስተማሪ እንደሆነ ተናግረዋል።

ክቡር ከንቲባው አክለውም በአላህ ትዕዛዝና በነብዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም መሪነት ስንማር የመጣን በመሆኑ ምክር ቤቱ እንደ መንግስት በሚሰሩ ስራዎች አቅም በመሆንና በአካባቢዎች የሰላም ችግሮችም በማገዝ ቻይነትን በማስተማር ትልቅ ሀላፊነት አየተወጣና በቀጣይ እንዲወጣም አመላክተዋል።
ምክር ቤቱ ሲቋቋም በወልቂጤ ከተማውና ዙሪያው በህዝበ ሙስሊሙ ፈትዋ የሚፈልጉ ጉዳዮች ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ሸሪዓዊ መርህ ተከትሎ በማስተማር ለማገዝ ያለመ ነው ሲሉ ጠቁመዋል ።
በህዝበ ሙስሊሙ የሚነሱ ጥያቄዎችን ሹራህ በማድረግ ተከታትሎ ማስተካከል ና ማረም ይኖርብናልም ሲሉ አቶ ሙራድ አመላክተዋል።
የማዕከላዊ ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ኡስታዝ በህጃ አብድልጀሊል እንደተናገሩት ህዝበ ሙስሊሙ በሰላምና ልማት ላይ ተሳትፎው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው በተሰጠው ሀላፊነት ከተጠያቂነት ለመዳን መስራት እንደሚያስፈልግም አብራርተዋል።
ከመንግስት በተገባው ቃል መሰረት የመቋቋሚያ ድጋፉ ተደርጎለት ለተቋቋመት አላማ መስራት እንዲችል ሊታገዝም ይገባልም ብለዋል።
እስልምና ጉዳዮች ምክርቤት በ2017 ጠንካራ አሰራር ወደ ተግባር የተገባበት ግልጽ የሆነ ምርጫ የተካሄደበት ተገቢው ውክልና የሚያገኝ አካል ማህበረሰቡ የመረጠበት ነው ሲሉ የጉራጌ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክርቤት ፕሬዝዳንት ተወካይ ወንድም ሷሊህ ገልጸዋል።
የሆኑ አካባቢዎች ላይ ሰፊ ስራዎች መስራት እንደሚጠይቅም የገለጹት ወንድም ሳሊህ ቤተእምነቶችም ሰላማዊ አኗኗር እንዲኖራቸው ወጣቶችና ሴቶችን የመሪነት ስራ ላይ የማሳተፍ እድል ተጠቅመው ስራዎች መስራት እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል።
በከተማው የሚገኙ መስጂዶችና መካነ-መቃብሮች ከቀበሌ እስከ ክፍለ-ከተማ ለይቶ በማወቅ በመንከባከብና በማብቃቱም ረገድ መጅሊሱ ብቁና ተወዳዳሪ ተቋማዊ ሆኖ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ተቀራርቦ እንደሚሰራም ተናግረዋል።
በጉባኤው ንግግር ያደረጉት የወልቂጤ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ኡስታዝ ሃይረዲን ዲነካ እንደገለጹት ምክርቤቱ ሙስሊሞች በሀገራቸው ሰላምና ልማት ላይ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት እድል የፈጠረ ነው ብለዋል።
ተቋሙ በመቋቋሙ ረገድ ሁሉም በያለበት የድርሻውን ወስዶ በማገዝ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር አብሮ እንደሚሰራም አንሰተዋል።
ወልቂጤ ከተማ የእስልምና አስተምሮቶችን የተከተለ የእምነቱ ተከታይ በማፍራት ሰርተን የታቀደው እቅድ ለማሳካት ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅም ኡስታዝ ሃይረዲን ተናግረዋል።
ከተሳታፊዎች የተነሱ አስተያየቶች ለቀጣይ እቅድ መሳካት በግብአትነት የሚሰራበት መሆኑንም ገልጸዋል።
ተሳታፊዎቹ በሰጡት አስተያየትም የታቀደው እቅድ ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም በየሀላፊነት ዘርፉም የሚጠበቅበትን መስራት ይኖርበታል ብለዋል።
ይህ ሀላፊነት ስንወጣ ልዩነቶቻችን በመቻቻል የእስልምናው አስተምሮት በሚያዘው ልክ እየተመራ እውቀት ያለው በእውቀቱ ገንዘብ በገንዘቡ በመተጋገዝ ተቋሙ ተቋማዊ ይዘት ማስያዝ ያስፈልጋል ሲሉ ጠቁመዋል።
ከመድረኩም የ5 አመት ስትራቴጂክ እቅድ በእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጸሀፊ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
በመጨረሻም የቀረበው እቅድ በምክርቤቱ አባላት ከነማሻሻያው በሙሉ ድምጽ የጸደቀ ሲሆን በከተማው በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትና ተቋማት የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።
በምክር ቤቱ ጉባኤውም ላይ የወልቂጤ ከተማ የብልጽግና ፖርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ና ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ሰፋ ዘይኑ፣ የሰላምና ጸጥታ ሀላፊ አቶ አስቻለው ገብሬ እንዲሁም የየመስጅዱ ኢማሞችም ተሳትፈዋል።

