የማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል ፀረ-ሙስናና ስነምግባር ኮሚሽን የሱፐርቪዥን ቡድን በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፅህፈት ቤት በመገኘት የስነምግባርና ፀረ ሙስና ስራዎች የድጋፍና ክትትል አደረገ ።

ጥር 15/2018ዓ.ም [ወልቂጤ ]
የክልሉ ፀረ-ሙስናና ስነምግባር ኮሚሽን የድጋፍና ክትትል ቡድን አባላት በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት በስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ስራዎች አፈፃፀም ላይ ድጋፍ ክትትል አድርጓል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና ጤና ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሙባረክ ዘይኑ እንደገለፁት በፀረ -ሙስናና ስነምግባር በከተማ አስተዳደሩ ለሚሰሩ ስራዎች ውጤታማነት የድጋፍና ክትትል ስራ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።የትብብርና ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት በበጀት ዓመቱ የማህበረሰብ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየት መልካም አፈፃፀም መመዝገቡን አንስተዋል።

በከተማ አስተዳደሩ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ስልጠና በማዘጋጀት እና የተለያዩ አጋጣሚዎች በመጠቀም ግንዛቤ የማስጨበጥና ቅድመ የመከላከል ሰራ አፅንኦት ተሰጥቶ መሰራቱን አብራርተዋል።
የድጋፍ ክትትል ቡድኑ በከተማ አስተዳደሩ በፀረ-ሙስናና ስነምግባር የተገኙ ውጤቶች ለሌሎች ምሳሌ መሆን የሚችል ስራ መሰራቱን በድጋፍና በክትትል ወቅት መገንዘባቸውን ተናግረዋል።

መረጃዎች በማደራጀት አሰራርን በመትከል በፀረ-ሙስናና ስነምግባር አሰራርና መመሪያ የሚፈለገውን ውጤትና ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ አንስተዋል።
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ፣ስልጠና ፣አስቸኳይ ሙስና መከላከል ስራ፣የኦዲት ግኝትና ሀብት ማሳወቅና ምዝገባ እየተሰሩ ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ የቡድን አባላት አስረድተዋል።

በፀረ-ሙስናና ስነምግባር ላይ ለሚከናወኑ ተግባራት የተሻለ ውጤት ለማምጣት እና የህዝብና የመንግሥት ሀብት በአግባቡ ለሚፈለገው አላማ ለማዋል ሁሉም የድርሻውን ወስዶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
ምቹ የስራ አካባቢ በመፍጠር በህዝቡ የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በሀላፊነት መፍታት ይገባል ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፅህፈት ቤት የሀላፊ ተወካይ አቶ ቃልአብ ደመቀ እንደተናገሩት እንደዚህ አይነት ድጋፎች መደረጋቸው ለቀጣይ ተግባራት ትልቅ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

በፀረ ሙስናና ስነምግባር እንደከተማ አስተዳደር በርካታ ችግሮች የተፈቱበት እና ተጠያቂነትን በማስፈን ቀልጣፋና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለህብረተሰቡ መስጠት መቻሉን አብራርተዋል ።
ቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት ችግር የሆኑ ጉዳዮችን ተቀራርቦ በመፍታት እና ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር የተጀመሩ አበረታች ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

