‎በከተማ አስተዳደሩ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ስልጠና በማዘጋጀት እና የተለያዩ አጋጣሚዎች በመጠቀም ግንዛቤ የማስጨበጥና ቅድመ የመከላከል ሰራ አፅንኦት ተሰጥቶ መሰራቱን አብራርተዋል።

‎

የማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል ፀረ-ሙስናና ስነምግባር ኮሚሽን የሱፐርቪዥን ቡድን በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፅህፈት ቤት በመገኘት የስነምግባርና ፀረ ሙስና ስራዎች የድጋፍና ክትትል አደረገ ።

‎

‎ጥር 15/2018ዓ.ም [ወልቂጤ ]

‎የክልሉ ፀረ-ሙስናና ስነምግባር ኮሚሽን የድጋፍና ክትትል ቡድን አባላት በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት በስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ስራዎች አፈፃፀም ላይ ድጋፍ ክትትል አድርጓል።

‎

‎

‎የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና ጤና ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሙባረክ ዘይኑ እንደገለፁት በፀረ -ሙስናና ስነምግባር በከተማ አስተዳደሩ ለሚሰሩ ስራዎች ውጤታማነት የድጋፍና ክትትል ስራ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።የትብብርና ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት በበጀት ዓመቱ የማህበረሰብ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየት መልካም አፈፃፀም መመዝገቡን አንስተዋል።

‎

‎በከተማ አስተዳደሩ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ስልጠና በማዘጋጀት እና የተለያዩ አጋጣሚዎች በመጠቀም ግንዛቤ የማስጨበጥና ቅድመ የመከላከል ሰራ አፅንኦት ተሰጥቶ መሰራቱን አብራርተዋል።

‎

‎የድጋፍ ክትትል ቡድኑ በከተማ አስተዳደሩ በፀረ-ሙስናና ስነምግባር የተገኙ ውጤቶች ለሌሎች ምሳሌ መሆን የሚችል ስራ መሰራቱን በድጋፍና በክትትል ወቅት መገንዘባቸውን ተናግረዋል።

‎

‎መረጃዎች በማደራጀት አሰራርን በመትከል በፀረ-ሙስናና ስነምግባር አሰራርና መመሪያ የሚፈለገውን ውጤትና ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ አንስተዋል።

‎

‎የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ፣ስልጠና ፣አስቸኳይ ሙስና መከላከል ስራ፣የኦዲት ግኝትና ሀብት ማሳወቅና ምዝገባ እየተሰሩ ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ የቡድን አባላት አስረድተዋል።

‎

‎በፀረ-ሙስናና ስነምግባር ላይ ለሚከናወኑ ተግባራት የተሻለ ውጤት ለማምጣት እና የህዝብና የመንግሥት ሀብት በአግባቡ ለሚፈለገው አላማ ለማዋል ሁሉም የድርሻውን ወስዶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

‎

‎ምቹ የስራ አካባቢ በመፍጠር በህዝቡ የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በሀላፊነት መፍታት ይገባል ብለዋል።

‎

‎የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፅህፈት ቤት የሀላፊ ተወካይ አቶ ቃልአብ ደመቀ እንደተናገሩት እንደዚህ አይነት ድጋፎች መደረጋቸው ለቀጣይ ተግባራት ትልቅ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

‎

‎በፀረ ሙስናና ስነምግባር እንደከተማ አስተዳደር በርካታ ችግሮች የተፈቱበት እና ተጠያቂነትን በማስፈን ቀልጣፋና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለህብረተሰቡ መስጠት መቻሉን አብራርተዋል ።

‎

‎ቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት ችግር የሆኑ ጉዳዮችን ተቀራርቦ በመፍታት እና ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር የተጀመሩ አበረታች ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

Previous ‎የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ፕሮግራም ማህበረሰቡ ለህክምና የሚያወጣውን ከፍተኛ ወጪ በመቀነስ ዜጎች በህመማቸው መጠን የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል:- የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ታደለ በቀለ

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo