‎ግልፅና ፍትሀዊ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት በህዝቡ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመፍታት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ገለፀ።

ግልፅና ፍትሀዊ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት በህዝቡ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመፍታት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ገለፀ።

‎ነሀሴ 5 /2017 ዓ.ም [ወልቂጤ ]

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የ2017ዓ.ም የመልካም አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጥ ችግር ልየታና አፈታት ሪፖርት እና የ2018 ዓ.ም እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ።

‎የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እንደገለፁት በሁሉም ዘርፍ በህዝቡ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ ፓርቲና መንግስት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ በበጀት ዓመቱ በርካታ ተግባራት መከናወን መቻሉን ገልፀዋል።

ተቋማት የማህበረሰቡን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት እያደረጉት ያሉውን ጥረት በማጠናከር በየአለንበት የስራ ዘርፍ የህዝባችን ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ በሚችሉ ስራዎች የድርሻችንን በመወጣት ነገ ለትውልድ የሚተላለፍ ስራ መስራት ከሁላችንም ይጠበቃል ሲሉ ከንቲባው ተናግረዋል ።

‎በዓመቱ በማህበረሰቡ በመልካም አስተዳደር የተነሱ ችግሮች ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ያነሱት ከንቲባው ቀጣይ የተፈፀሙ የነበሩ ጉዳዮች በማጠናከር የታዩ ውስንነቶችን ለይቶ የእቅድ አካል በማድረግ ቀልጣፋ ጥራት ያለው አገልግሎት ለህብረተሰባችነ ተደራሽ ለማድረግ ቅንጅታዊ አሰራሮችን በመዘርጋት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

‎ከንቲባው ቀጣይ ግልፅ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት አፅንኦት ሰጥተው ልንሰራባቸው ይገባል ብለው ካነሱዋቸው ነጥቦች መካከል ፍትሀዊ የገቢ አሰባሰብ ስርዓት፣ብድር ማስመለስና ስራ እድል ፈጠራ፣ህገወጥ የንግድ ስርዓት ፣የፍትህና ፀጥታ፣የትራንስፖርት አገልግሎት ፣ግዢና ጨረታ፣የሀብት አስተዳደር ስርዓት ፣ህገወጥ የመሬት ወረር፣ የሀብት አስተዳደር ስርዓት እንዲሁም የመድኃኒት አቅርቦት በቀጣይ በጀት ዓመት ሁሉም የድርሻው በመውሰድ በህዝቡ ተሳትፎ ልዩ ትኩረት ሰጥተን የሚከናወወኑ ተግባራት መሆናቸው ጠቁመዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ግርማ ንቅበሸዋ እንደተናገሩት ተቋማት የተሰጣቸውን ተልዕኮና የሚጠበቅባቸውን ውጤት ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ለማሳካትና የላቀ አፈፃፀም ለማስመዝገብ እንዲሁም የህዝቡ ተጠቃሚነት ውጤታማነት ለማረጋገጥ የሚያግዙ ስልቶች በመደፍ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

‎ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠትና ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመታገል፣ የዜጎችን ንቁ ተሳትፎ ለማጎልበት፣ ግልፅነትንና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ፣ የህግ የበላይነትን ለማስከበርና በአገልግሎት አሰጣጥ ቅንነትና ታማኝነትን ለማስፈን የተፈጸሙ ተግባራት በወቅቱ በመገምገም በመልካም አስተዳደር የሚስተዋሉ ክፍተቶችን መለየት እንደሚገባ ተናግረዋል።‎በውይይት መድረኩ ከተሰጡ ሀሳብና አስተያየት የከተማችን ልማትና እድገት ማረጋገጥ የምንችለው በማህበረሰቡ የሚነሱ የተለየ ትኩረት የሚሹ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍታት ስንችል ነው።በ2017 በጀት ዓመት ቅንጅት የተሰሩ መልካም አፈፃፀም የተከናወኑ ተግባራት በማስቀጠል ያልተከናወኑ ተግባራት በመለየትና በሚስተዋሉ ክፍቶች ላይ የመፍትሄ አቅጣጫ በማስቀመጥ የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።

‎በማህበራዊና በኢኮኖሚ ዘርፍ የህዝብ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ተቋማት በአገልጋይነት መንፈስ እንዲሁም ከክራይ ሰብሳቢነት አመለካከት ነፃ በመሆን ህዝቡ ማግኘት ያለበትን አገልግሎት መስጠት እንዲያገኝ ማስቻል እንደሚገባም ተናግረዋል።

‎ከዚህ በፊት በህብረተሰቡ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግር ለመቅረፍ ከፍተኛ ጥረት መደረጉን አንስተው እንደ ከተማ በተለያየ ምክንያት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች እና በመሰረተ ልማት ዘርፍ በህዝቡ ተሳትፎ የተሰሩ ያሉ ተግባራት በዓመቱ መልካም አፈፃፀም የተመዘገበበት እንደነበረ አብራርተዋል።

‎የህዝብና የመንግስት ሀብት በአግባቡ አጠቃቀማችንን በማስተካከል የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት በማዘመን ጥራትና ያለው ፍትሀዊ አገልግሎት ለማህበረሰባችን ልንሰጥ ይገባል ብለዋል።

‎

Previous የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo