የወጣቶች መልካም ስብዕና መገንባት በሀገሪቱ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፏቸው እንዲያሳድጉ እንደሚረዳቸው የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት አዘጋጅነት በወጣቶች ስብዕና ግንባታ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል።

ግንቦት 16/2O17 ዓ/ም [ወልቂጤ]

የወጣቶች መልካም ስብዕና መገንባት በሀገሪቱ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፏቸው እንዲያሳድጉ እንደሚረዳቸው የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት አዘጋጅነት በወጣቶች ስብዕና ግንባታ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል።

በስልጠናው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አስራት ታደለ እንዳሉት ወጣቶች የሀገሪቱ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እድገት ለማረጋገጥ የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው፡፡

በመሆኑም መንግስት ለወጣቶች የስራ እድል ከመፍጠሩም ባለፈ የወጣቱ ስብዕና በትምህርትና በቴክኖሎጂ በመገንባት በሀገሪቱ ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ ተሳትፏቸው በማሳደግ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡

ሀገሪቱ የእድገት ደረጃና የወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የማይጣጣም በመሆኑ በርካታ ስራ ፈላጊ ወጣቶች መኖራቸውን ጠቁመው ወጣቶች በሱስ ተጠምደው ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውንና እውቀታቸውን አልባሌ ቦታ ከማዋል ይልቅ የራሳቸውን ስራ ፈጥረው በመስራትና በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይ ተሳትፏቸውን በማሳደግ ሀገራቸውንና ወገናቸውን ሊጠቅሙ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ቶፊቅ ጀማል በበኩላቸው ለወጣቶች በቂ ትኩረት በመስጠት እና ምቹ ሁኔታዎች በመፍጠር ስብዕናቸው በተገቢው ሁኔታ መቅረጽ ግድ የሚል ተግባር ነው ብለዋል።

በከተማው የወጣቶች ስብዕና ለመገንባት እና በስነ-ምግባር እንዲታነጹ ለማድረግ በክበባት፣ በአደረጃጀቶች እና በወጣት ማዕከላቶች የተለያዩ የሰብዕና ግንባታ ስራዎች እየተሰራ መሆኑም ተናግረዋል።

ወጣቶች አዳዲስ ነገሮችን የመፍጠርና የመመርመር ብቃታቸውን በመጠቀም ለሀገር እድገትና ብልጽግና በማበርከቱ ረገድ አስተዋጽአቸው የላቀ በመሆኑ በተግባር ማሳየት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ወጣቶች በመልካም ስነ-ምግባር በመታነጽ ለነገ ታዲጊ ህፃናት አርአያነት ያለው ነው ያሉት አቶ ቶፊቅ በከተማው፣ በዞኑ ብሎም በሀገሪቱ የልማት የዴሞክራሲና የሰላም ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳታፊ መሆን እንዳለባቸውም አብራርተዋል።

ጽህፈት ቤቱ የወጣቶችን ስብዕና ከመገንባት ባለፈ በክረምትና በበጋ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት በማሰማራት በከተማው በርካታ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚሁ ወቅት የስልጠናው ሰነድ ያቀረቡት የከተማ አስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት የወጣቶች ማብቃትና ንቅናቄ ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ ፍቅሬ መስፍን እንደገለፁት በስብዕና የታነፀ ወጣት በማፍራት በሀገረ መንግስት ግንባታ የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከት ይገባል ብለዋል።

ወጣቶች የአመለካከትና የተግባር አንድነት በመፍጠር ስራ ጠባቂ ብቻ ሳይሆኑ ስራ ፈጣሪም ጭምር በመሆን ሁለንተናዊ ብልፅግና ማረጋገጥ እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

በእውቀትና በምክንያት የሚያምን ለለውጥ ዝግጁ የሆነ ወጣት ማህበረሰብ መገንባት ይገባል ብለዋል።

መሰል ስልጠና መሰጠቱ ወጣቶች ጊዜያቸውን አልባሌ ቦታ እንዳያውሉ ከማድረግ ባለፈ ለሁለንትናዊ ለውጣቸው አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የተናገሩት ደግሞ የስልጠናው ተሳታፊዎች ናቸው።

ፕሮግራሙን በማስፋፋት የተጀመረውን የወጣቶች ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም በኤች አይቪ ኤድስ መከላከልና በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ዙሪያ ላይ ለወጣቶች ግንዛቤ ተፈጥሯል።

በኤች አይቪ ኤድስ መከላከልና በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ዙሪያ ላይ ለወጣቶች ግንዛቤ ተፈጥሯል።

Previous አዲሱ የገበያ ማዕከል መከፈት ለከተማው እድገትና ለማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ላይ አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው፡- አቶ ሙራድ ከድር የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo