ግንቦት 14/2O17 ዓ/ም [ወልቂጤ]
አዲሱ የገበያ ማዕከል መከፈት ለከተማው እድገትና ለማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ላይ አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው፡- አቶ ሙራድ ከድር የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ

በዛሬው ዕለት የጉብርየ አዲሱ የገበያ ማዕከል በይፋ ተመርቋል።
በምረቃው ዕለት የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እንዳሉት የግብርና ምርቶች በብዛት ወደ ከተማው እንዲገቡ በማድረግ የገበያ አለመረጋጋቱን በመቅረፍ የከተማውን ነዋሪ የኑሮ ጫና ለማቅለል እየተሰራ ነው ብለዋል።
ገበያ የኢኮኖሚ መነቃቃት በመፍጠሩ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረው አዲሱ የገበያ ማዕከል መከፈት ለከተማው እድገትና ለማህበረሰቡ ተጠቃሚነት በማረጋገጡ ላይ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

ይሁን እንጂ የጉብርየ ገበያ እድሜ ጠገብ ቢሆንም የቦታው አቀማመጡ ምቹ ባለመሆኑ በሚፈለገው ልክ ሊዘምን እንዳልቻለ አስታውሰው በዚህም የረዥም ጊዜ ጥያቄ የነበረው ገበያ በኢዲስ መልኩ ስራ በመጀመሩ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።
ጉብርየ ገበያ በቀጣይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትልቁን ገበያ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራም ጠቁመው
ገበያው ምቹና ዘመናዊ እንዲሁም ለሸማቹ ማህበረሰብ የሚፈልገውን እንዲያገኝ ከተማ አስተዳደሩ የድርሻውን እንደሚወጣም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ መላኩ ብርሃኔ በበኩላቸው የጉብርየ ገበያ በይፋ መጀመሩ ለዞኑም ብሎም ለከተማው ትልቅ ፋይዳ ያለው በመሆኑ የዞኑ መንግስት ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ከዚህ በፊት ማህበረሰቡ ይገበያይበት የነበረው የገበያው ቦታ ምቹ ባለመሆኑ ለተለያዩ ስቃይና እንግልት ይዳረግ እንደነበር አውስተዋል።
በቀጣይም በወልቂጤ ከተማ በበኩር ክፍለ ከተማ ያለውን ትልቁ የገበያ ማዕከል ለመመስረት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

አቶ መላኩ አክለውም ለከተማው ልማትና ዕድገት ሁሉም ማህበረሰብ ከመንግሥት ጎን በመሆን የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብድልከሪም መሐመድ እንደገለፁት የዛሬ ገበያ በይፋ መጀመሩ ለከተማችን ዕደገት እንዲሁም ለኢኮኖሚው መነቃቃት ትልቅ ፋይዳ እደለውም ጠቁመዋል።
ሸማቹ ማህበረሰብ የሚፈልገውን ግብይት በቅርበት ለማግኘት ሚናው የጎላ ነው ብለዋል።

በቀጣይም የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የተጠናከረ ስራ እንደሚሰራም አቶ አብድልከሪም ተናግረዋል።
አቶ መኮ ሙዝየ እና አቶ ደግፍ አጥምዛ በሰጡት አስተያየት በክፍለ ከተማው አዲስ የገበያ ማዕከል በመቋቋሙ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ከዚህ በፊት ማህበረሰቡ ሲገበያይ ለተለያዩ አደጋዎች ይዳረግ እንደነበር ጠቁመው ይህንን የገበያ ማዕከል መቋቋሙ ማህበረሰቡ ለዘመናት ሲመኘው እንደነበር ጠቁመዋል።

በቀጣይም በክፍለ ከተማው እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ማህበረሰቡ ከመንግሥት ጎን በመሆን የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በመድረኩም የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ሙራድ ከድር፣ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊና የታክስ ህግ ማስከበር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ውድነህ፣ የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ መላኩ ብርሃኔ፣ የወልቂጤ ከተማ አስተባባሪዎችና የከተማው አመራሮች፣ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች፣ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው

