በአቅሜ ልክ አዋጣለሁ በህመሜ ልክ እታከማለሁ በሚል መሪ ቃል የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽህፈት ቤት የንቅናቄ መድረክ አካሄደ።

ታህሳስ 11/2017(ወልቂጤ)

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በ2016ዓ.ም 10,458 የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የማዕጤመ አገልግሎ በመጠቀም ህክምና አግኝተዋል::

በአቅሜ ልክ አዋጣለሁ በህመሜ ልክ እታከማለሁ በሚል መሪ ቃል የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽህፈት ቤት የንቅናቄ መድረክ አካሄደ።

የንቅናቄ መድረኩ ዋና ዓላማም የጤና መድህን ስርዓትን በሀገራችን ተግባራዊ በማድረግ የጤና አገልግሎት ወጪ በህብረተሰቡ ላይ የሚያስከትለውን ጫና በመቀነስ ፍትሀዊና ተደራሽ የሆነ የጤና አጠቃቀምን በማጎልበት ሁሉ አቀፍ ሽፋን ማረጋገጥ እንደሆነ ተገልጿል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የሆኑት አቶ ሙራድ ከድር እንደገለጹት ፓርቲያችን ሠው ተኮር ነው። በመሆኑም የጤና መድህን የመጣው ለማህበረሰቡ ተጠቃሚነት መሆኑን ማወቅ ተገቢ ነው ብለዋል።

አምራች ዜጋን ለማግኘት ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ ሊኖር ያስፈልጋል ያሉት ክቡር ከንቲባው ጤናው የተጠበቀ ዜጋ እንዲኖር ለማድረግ ደግሞ በገንዘቡ ልክ ሳይሆን በህመሙ ልክ መታከም የሚችልበትን ዕድል መፍጠር ስንችል ብቻ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የጤና መድን ማጤመን የሚገባውን ዋጋና ትርጉም ሰጥተን ማሳካት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ተረድተን ማህበረሰባችን የሚረዳበትን አግባብ ልንፈጥር ይገባል ብለዋል::

የማዕጤመ ተጠቃሚው ማህበረሰባችን በገንዘቡ ልክ ሳይሆን በህመሙ ልክ ሊታከም ይገባል ያሉት ክቡር ከንቲባው ማህበረሰባችን የዚህ እድል ተጠቃሚ እንዲሆን የተለያዩ የልማት ድርጅቶች ለማዕጤመ መክፈል ለማይችሉ የበኩላቸውን ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ክቡር ከንቲባው አያይዘውም በ2017 ዓ.ም ከወትሮ በተለየ መልኩ የማጤመን ፋይዳ ተረድተን ሊመጥን በሚችል አመራርነትና ባለሙያነት ተሰጥተን በመስራት ሁሉ አቀፍ የሆነ ውጤት ልናስመዘግብ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ሙባሪክ ዘይኑ በበኩላቸው መንግስት የጤናውን አገልግሎት ለማሳለጥና ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

ከእነዚህም መካከል አንዱና ዋነኛው የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አንዱ ነው።

በመሆኑም ዜጎች ለጤና አገልግሎት በሚያወጡት ከፍተኛ ወጪ ምክንያት ለከፋ ድህነት እየተዳረጉ ከመሆኑም በላይ አብዛኞቹ የሚከፍሉትን ገንዘብ በማጣት ሊድን በሚችል ህመም እየተሰቃዩ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ እንደሚዳረጉ ገልጸዋል።

ለዚህ መሳካት ደግሞ የከተማ ፣የክፍለ ከተማ አመራር የቀበሌ ስራ አስኪያጆች እንዲሁም የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ተጋግዘን ማሳካት ይገባል ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ረዳት የመንግስት ተጠሪ የሆኑት አቶ ጴጥሮስ አስራት እንደገለጹት ጉድለቶችን የዕቅድ አካል በማድረግ መስራት ያስፈልጋል።

ስለዚህ በ2017 በጀት ዓመት ከቀበሌ መዋቅር ጀምሮ የማዕጤመ ስራችንን ለመስራት በቁርጠኝነት መነሳት ያስፈልጋል።

አቶ ጴጥሮስ አያይዘውም በታችኛው መዋቅር ላይ የሚታዩ አንዳንድ መገፋፋቶች በአስቸኳይ ሊታረሙ እንደሚገባ ገልጸው ለዚህ ስራ መሳካት በተቀናጀ፣ በተናበበና በጋራ በጋራ መንፈስ በጥንቃቄና በሰለጠነ መንገድ የማዕጤመን ፕሮግራም ማሳካት ይገባል ብለዋል

መታረም ያለባቸውን ጉዳዮች ማረምና በተደመረና በመልካም መንፈስ ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረግን በማሰብ በተያዘው መሠረት ማስኬድና መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በወልቂጤ ከተማና በጉብርየ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የቀበሌ ስራ አስኪያጆችም ሠው በገንዘቡ ለክ ሳይሆን በህመሙ ልክ መታከም እንዳለበት በማመን ለስራው መሳካት የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

በመጨረሻም በ2016 በጀት አመት የተሻለ አፈጻጸም ላመጡ ጤና ተቋማት፣ ቀበሌዎች፣ ባለሙያዎች እንዲሁም ጤና ኤክስቴንሽኖች የዕውቅና ሽልማት ተሰጥቷል።

በዚህ የንቅናቄ መድረክም የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ታደለ በቀለ፣ የከተማ አስተዳደሩ አመራር፣ የቀበሌ ሊቀመናብርትና ስራ አስኪያጆች፣ የጤና ጣቢያ ሀላፊዎች ጤና ኤክስቴንሽኖች እንዲሁም ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

Previous እንደ ሀገር የተቀመጡ ግቦች በመንግስት ብቻ ማሳካት ረጅም ጊዜ የሚወስድ እንደመሆኑ መጠን በትምህርት ቤት ልማታዊ ስራዎች የግል ባለሀብቶች ማሳተፍ አካባቢ በማልማት እንዲሁም ለደረጃ የሚመጥኑ የትምህርት ተቋማቶች እንዲገነቡ በማድረግ ወቅቱን የሚመጥን ተወዳዳሪ ትውልድ መፍጠር ነው ብለዋል።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo