ትምህርት ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ብልፅግናና የእድገት ስልጣኔ ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እሴቶች ለመገንባት አይነተኛ ሚና የሚጫወት ቁልፍ መሳሪያ በመሆኑን የሁላችንም ትኩረት ይሻል የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ሙራድ ከድር

በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት “የላቀ ትጋት ለላቀ የትምህርት ጥራት” በሚል መሪ ቃል የ2016 ዓ.ም የትምህርት ጉባኤ ተካሄደ ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር ባደረጉት ንግግር ጥራትን ከግንዛቤ ያላስገባ ተደራሽነት ላይ ብቻ ያተኮረ የትምህርት ፖሊሲ ስንከተል መቆየታችን ገልጸው።

ዛሬ ላይ አለም የደረሰችበት ለመድረስና ግሎባላይዜሽን ሊያመጣ የሚችል ትውልድ እንዳንቀርፅ ተፅዕኖ አድርጎብናል ብለዋል።

አቶ ሙራድ አክለውም ለውጡ ከመጣ በኋላ ግን የትምህርት ስርዓት በማዘጋጀት ስብራቱን ከመነሻው ተገቢውን ትኩረት በመስጠትና በመገምገም ስርነቀል ለውጥ በትምህር ጥራትና ውጤት ላይ ለማምጣት ወደ ተግባር መገባቱን አመላክቷል ።

የትምህርት ተቋማት መጪውን አገር ተረካቢ ትውልድ የምናፈራበት ስፍራ በመሆኑ መንግስት ትልቅ ትኩረት ሰጥቶት እየሰራበት ያለ ዘርፍ እንደሆነና አጠናክሮም እንደሚቀጥልም ክቡር ከንቲባው አመላክተዋል።

በስራው ተመዝኖ የገባ ምህርና ሱፐርቫይዘር ነገ ውጤታማ ማይሆንበት አጋጣሚ ስለማይኖር የተጣለብንን ሀገራዊ ሀላፊነት ከግምት በማስገባት በተማሪዎች ውጤት ላይ በትኩረት መስራት አለብን ያሉት የከተማው ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ታደለ በቀለ ናቸው ።

በዚህ በጀት አመት እንደ ከተማ አስተዳደራችን ጠንካራ የትምህርት ተቋማትንና ብቁ እንዲሁም የነገ አገር ተረካቢ ዜጎችን የምናበቃበት የትምህርት ዘመን እንዲሆን ሁላችንም ተግተን በጋራ መስራት አለብን በማለት አቶ ታደለ አሳስበዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ስሜነሽ ግርማ በበኩላቸው የሀገሪቱ ሁለንተናዊ ልማት ለማረጋገጥ ብቁ ተወዳዳሪና ቴክኖሎጂ መጠቀም የሚችል እውቀት ያለው ዜጋ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት የመምህራንና የተማሪ ሚና ከፍተኛ ነው ያሉ ሲሆን።

የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ ጎን ለጎን እየተከናወኑ የሚገኙት ተግባራት እንዲጎለብቱ የክትትልና ድጋፍ እገዛ ሥራዎች ተቋማችን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ሀላፊዋ ጠቁመዋል።

የጉልባማ ዋና ዳይሬክቶሬት አቶ ቅባቱ ተሰማ እንደገለጹት ትምህርት ቤቶች ላይ የተለያዩ አደረጃጀቶች መኖራቸው ይታወቃል

በመሆኑም እነሱን አጠናክሮ መጠነ ማቋረጥ በመቀነስ በተማሪ ውጤትና ስነምግባር ላይ በትኩረት ልንሰራ ይገባልም ብለዋል።

እንደ ልማት ማህበሩ ለ2017 ትምህርት ዘመን እጥረቶችን ለመቅረፍ በጋራ ርብርብ በመሥራት መምህራንን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የትምህርት ጥራቱ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁነታችንን ጭምር እንገልፃለን ብለዋል::

ለተማሪዎች ምግብ በማቅረብ የትምህርት ብክነት መቀነስና የተማሪዎች ውጤታማነት ማሻሻል እንዲሁም ጤናማና አምራች ዜጎችን መፍጠር ነው ያሉት የጽህፈት ቤቱ የትምህርት ቤቶች መሻሻል እና ሱፐርቫይዘሮች ስራ ሂደት ወይዘሮ ሰሚራ አብራር ሲሆኑ።

የቅድመ አንደኛና መጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎ እና ውጤታማነት በማረጋገጥ ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ ማስቻል ነው ብለዋል።

አንዳንድ የጉባኤው ተሳታፊዎች እንደገለፁት ችግሮች ለመፍታት ችግሮች መለየት አስፈላጊ በመሆኑ ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ ወደ ተግባር ገብቶ በተማሪ ውጤት መሻሻል ዙሪያ ውጤታማ የሆነ ለውጥ ማየት ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸው ።

የትምህርት ስራ ለውጥ የሚፈልግ እንደመሆኑ መጠን ሁሉም ማህበረሰብ ለትምህርት ያለው ስሜት ከተማሪ ስነምግባርና ውጤት ጋር የተሳሰረ መሆን መቻል አለበት ሲሉም ተደምጠዋል ።

እንደ ከተማችን በትምህርት ጥራት ዙሪያ የገጠመንን የትምህርት ስብራት ለመጠገን በየደረጃው ሁሉም ባለቤት በመሆን የተሻለ ውጤት አስመዝግበን ነገ ተወዳዳሪ የሆነ ትውልድ ማብቃት መቻል አለብን ብለዋል።

አያይዘውም ለውጤት መሻሻል ምቹ የሆነ የመማሪያ ስፍራ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑ ከግምት በማስገባት ከመምህራን ማህበር ጀምሮ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል ሲሉ አመላክተዋል ።

የ2017ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት የከተማው የመምህራን ማህበር የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በስተመጨረሻም ትምህርት ቤቶች የግብ ስምምነት ተፈራርመው በ2016ዓ.ም የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችና በትምህርት መሻሻል ላይ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላቶች የእውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸው መድረኩ ተጠናቋል ።

Previous ትልቁ የባህል መሰረት የሆኑት የሀይማኖት አባቶችንና የሀገር ሽማግሌዎችን ማክበርና መታዘዝ የሁሉም ዜጋ ግዴታ መሆን መሆን እንዳለበት ተገለጸ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo