ሆቴሎች ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ የማህበረሰቡን ባህል በማስተዋወቅ እረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ።

የጆካ ኢንተርናሽናል ሆቴል የጉራጌን ባህል ለማስተዋወቅ እና ለትውልድ እንዲተላለፍ የበኩሉን እንደሚወጣ አቶ ሰይፈ ሀ/ማረያም የጆካ ኢንተርናሽናል ባለቤት ገልጸዋል

ጉራጌ የራሱ ባህል፣ወግ፣እሴት እና ትውፊት ያለው ማህበረሰብ ነው።ማህበረሰቡ ከጥንት ጀምሮ ሲገለገልባቸው እና ጠብቆ ያቆያቸው የባህል ቁሳቁሶች ባለቤት ነው ጉራጌ።

የባህል ቁሳቁሶች በወልቂጤ ከተማ የሚገኘው በጆካ ኢንተርናሽናል ሆቴል በባህል ምግብ ቤት ውበት ሆነው ይታያሉ።

የጆካ ኢንተርናሽናል ሆቴል የራሱ ባህላዊ የምግብ አደራሽ ያለው ሆቴል ሲሆን ከጥንት ዘመን ጀምሮ ጉራጌ ሲገለገልባቸው የቆየው ባህላዊ የዕደ ጥበብ ስራዎች ዛሬ ላይ ሲታዩ እጅግ ውብና አስደናቂ ናቸው።

የጆካ ኢንተርናሽናል ሆቴል ባለቤት አቶ ሰይፈ ሀ/ ማርያም እንዳሉት ከዚህ በፊት ጉራጌ በከተማው በቂ እንግዳ መቀበያ የለውም የሚል አስተሳሰብ ለመቀየር የጆካ ሆቴልን ደረጃውን ለማሻሻል እየተሰራ ነው ብለዋል።

ሆቴሉ በየጊዜው የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ሰፉፊ ስራዎችን በመስራት በአሁን ሰዓት ዘመናዊና ባህላዊ የሆቴል አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል።

በውስጡም ደረጃቸው የጠበቁ አልጋዎች፣የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች፣ የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ጂም እንዲሁም የባህል ምግብ ቤት፣የጉራጌን ባህል የሚገልጹ የጉራጌ የጥንት መገልገያ ቁሳቁሶች በስፋት የማስገባት ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

ከምግብ ደግሞ የጉራጌ መገለጫ የሆነው የጉራጌ ክትፎ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እና ሌሎች የባህላዊ ምግቦች በየደረጃቸው ያሚቀርቡ ሲሆን ባህላዊ ቡና እና ሌሎችም እንደ ተገልጋዩ ፍላጎት እንደሚሰጥ አቶ ሰይፈ ተናግረዋል።

አክለውም የጆካ ኢንተርናሽናል ሆቴል የጉራጌን ባህል በሁሉም ካባቢዎች ለማስተዋወቅ እና ለትውልድ እንዲተላለፍ የበኩሉን ይወጣል

ሆቴሉ ደረጃው በጠበቀ መልኩ የተሰራ ሲሆን በ4ቱም አቅጣጫ መጥተው ወልቂጤ ከተማ ለሚያርፉ እና በከተማው ያሉ ማህበረሰቦች የሚፈልጉት አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ቀጣይም ይህንን ፈልጎ ለሚመጣ ማንኛውም አካል ከጥሩ መስተንግዶ ጋር እንቀበላለን ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ መሰረት አመርጋ እንዳሉት መምሪያው ለቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፍቃድ የመስጠት፣የመደገፍና የመከታተል ስራ እንደሰራ ተናግረዋል።

ሆቴሎች የምግብ አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ የአንድን ማህበረሰብ ባህል በማስተዋወቅ እረገድ ከፍተኛ ሚና አላቸው ብለዋል ወ/ሮ መሰረት።

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የሚገኘው የጆካ ሆቴል በየጊዜው አገልግሎት አሰጣጡን በማስፋት ለከተማው ውበት በመሆን፣ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በማሳደግ፣እንግዶች ከመቀበል አልፎ የጉራጌን እደ ጥበብ ማሳያ ሆቴል ነው ብለዋል።

ሆቴሉ ወልቂጤ ከተማን አቋርጠው የሚሄዱ እንግዶች ወደ ሆቴሉ በሚገቡበት ጊዜ የጉራጌን መገለጫ የሆኑ የባህል ቁሳቁሶች፣የጉራጌ ክትፎ ተመግበው እንግዳ አቀባበልነት አይተው ሲሄዱ ባህሉን በሌሎች አካባቢዎች እንዲተዋወቅ በማድረግ ትልቅ ሚና ይጫወታል ነው ያሉት።

በሆቴሉ ውስጥ የሚሰጡና የሚታዩ ባህላዊ ክዋኔዎች ለትውልድ እንዲተላለፍ የሚያደርግ መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ መሰረት ሆቴሉ እያደረገ ያለው ዘመናዊና ባህላዊ ስራ በሁሉም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ተግባራዊ እንዲሆን መልእክታቸው አስተላልፏል።

Previous

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo