ጉራጌ ብልፅግናዊ እሳቤና እሴት ያለው፣ፈተናዎችን እንደ እድል እየተጠቀመና እየፀና ጀምሮ በመጨረስ ልምድና ስነልቦና የታነፀ ህዝብ ነው፦ አቶ ላጫ ጋሩማ

ጥር 20/2018 ዓ/ም (ወልቁጤ)፦የጉራጌ ዞን አስተዳደር እና የኦሮሚያ ብርድካስቲንግ ኔትወርክ የጉራጌ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ስቱዲዮ ግንባታ ለማከናወን የውል ስምምነት ተፈራርመዋል!!
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በስምምነቱ ወቅት እንደገለፁት ከአምስት አመታት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ጉራጊኛን የሚዲያ ቋንቋ በማድረግ በዞኑ የሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ካለምንም ክፍያ በሳምንት ለሶስት ሰዓታት በሚዲያው በማስተላለፉ ኦቢኤን ትልቅ ምስጋና ያስፈልገዋል፡፡

ኦቢኤን ከሀገሪቱ አልፎ በአፍሪካ ደረጃ ከሚገኙ ሚዲያዎች ግንባር ቀደም ተቋም ለመሆን እየሰራቸው የሚገኙ ተግባራት አበረታችና ሌሎችም ሊማሩባቸው የሚገቡ ናቸው ያሉት አቶ ላጫ ድርጅቱ የጉራጌ ማህበረሰብ ቴሌቭዥን በማቋቋም ሂደት ውስጥ አሻራው እንዲያሳርፍ መወሰናችን ተገቢነት ያላው መሆኑንም አብራርተዋል።

የጉራጌ ማህበራሰብ በተቋሙ ያለው እምነት ከፍተኛ ነው ያሉት አቶ ላጫ ከዚህም በመነሳት የጉራጌ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ስቱዲዮ ግንባታ እንዲገነባ መወሰኑን አውስተዋል፡፡
ከድርጅቱ ጋር በጋራ መስራት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚያስገኝ የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው የጉራጌ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ስቱዲዮ ከመገንባት ባለፈ የህዝብ ለህዝብ ትስስር በማጠናከር፣ለባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት፣ የጥገና ስራዎች ለማከናወንና ሌሎችም በሂደቱ የሚያስፈልጉ ተግባራት ጭምር እንደሚያግዝ ገልፀዋል፡፡
ጉራጌ ገና በጥልቀት ሊጠኑና ሊፈተሹ የሚችሉ ቱባ ባህሎችና ፀጋዎች ያሉት ህዝብ ነው ያሉት ክቡር አስተዳዳሪው የዞኑ ማህበረሰብ ቋንቋውን፣ ባህሉን፣ ታሪኩንና ሌሎች የልማት ስራዎች የሚያስተላልፍበት የቴሌቪዥን ጣቢያ ባለመኖሩ ለህዝቡም ሆነ ለሌሎች ተደራሽ ማድረግ እንዳልተቻለ አብራርተዋል፡፡

ማህበረሰቡ ችግሩን በመደጋገፍ እንዲፈታ እቁብ፣ ሀዘን ሲገጥመው እድር፣ ከሀገሪቱ ባለፈ እንደ አፍሪካ ቀዳሚ የሆነ የመንገድ ልማት ስራ ድርጅት በማቋቋም ፈር-ቀዳጅ ተግባራት ያከናወነ ማህበረሰብ እንደሆነ አስረድተው የቴሌቭዥን ጥያቄም ለረዥም ጊዜ ሲጠይቀው የነበረ መሆኑን አውስተዋል።
ስለሆነም ይህንን ጥያቄ በመመለስ ጉራጊኛ ወደ አንድ ለማምጣት፣ ህብረተሰቡ በልማት ለማነቃቃት፣ ብዙ ያልተነገሩ፣ ጎልተው ያልወጡና ያልተዋወቁ ባህሎች በማልማት ማስተዋወቅ እንዲቻል የጉራጌ ቴሌቪዥን ሚናው የላቀ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ህዝቡን የሚመጥን የሚዲያ ተቋም ለማቋቋም ከኦቢኤን ጋር በመሆን የተጀመረው ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላ ብለዋል፡፡

የኦቢኤን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ጋዜጠኛ ፍሰሃ በላይነህ በበኩላቸው የጉራጌ ህዝብ እጅግ በጣም አኩሪ ታሪክና የስራ ባህል ያለው ነው!!
ጉራጌ ብልፅግናዊ እሳቤን የያዘና በመንደር ያልታጠረ በመላ ሀገሪቱ በመንቀሳቀስ እየሰራ ያለና ያለበትንም ከተማ የሚያለማ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ኦቢኤን የህዝቡ ትልቅነትና ስፋትን በመገንዘብ እንደዚሁም በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በስፋት በመኖሩ በነፃ ሰፊ የአየር ሰዓት በመስጠት በሳምንት ሶስት ቀናት በጉራጊኛ ቋንቋ እያስተላለፋ መሆኑን አብራርተዋል።

ተቋማቸው ኦቢኤን በሀገሪቱ የኢዚአን ጨምሮ የተለያዩ ስቱዲዮችን መገንባቱን የገለፁት ዳይሬክተሩ የጉራጌ ማህበረሰብ ቴሌቭዥን ስቱዲዮን ደግሞ ከሌሎች ያካበተውን ልምድ በመጣቀምና ዘመኑ የደረሰበትን ደረጃ ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንደሚገነባ ገልፀዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ነወ!።

