የጉራጌ ዞን ሴቶች የጀመሩት የብልጽግና ጉዞ ውጤታማነት በቀጣይም ሀገራዊ ተልእኮዎች ላይ መድገም ይገባል፦የአማራ ክልል ሲቭል ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ በአንቺአምላክ ገ/ማረያም

የካቲት 9/2018(ወልቂጤ)፦በጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት አስተባባሪነት “በሴቶች ተሳትፎ የጸናችና የበለጸገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ዞናዊ የማጠቃለያ መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል።
የአማራ ክልል ሲቭል ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ በአንቺ አምላክ ገ/ማረያም ብልጽግና ፓርቲ ለሴቶች በሰጠው ልዩ እድል ሴቶች በማህበራዊ ፣በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ዘርፍ ተጠቃሚነታቸው ማረጋገጥ ችለዋል።
በዚህም ማህበራዊ መስተጋብሮቻችን ይበልጥ በማሳለጥ ማድ በማጋራት እና ቤት በመስራት በርካታ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች መስራት መቻሉ አብነት አንስተዋል።

ወ/ሮ በአንቺ አምላክ አክለውም የቀጣይ ምርጫ ሰላማዊ፣ፍትሀዊና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ሴቶች ከጅምሩ እስከ ፍጻሜው መሪ ተዋናይ መሆን እንደሚጠበቅባቸው አስታውቀዋል።
ሴቶች ለሰላም ፣ለአብሮነት፣ ለመቻቻልና ሰርቶ ለመለወጥ የላቸው ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው ያሉት ወ/ሮ በአንቺአምላክ እንደ ሀገርም የጉራጌ ሴቶች ደግሞ ለዚህ አንዱ ማሳያ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።
በመሆኑም የጉራጌ ዞን ሴቶች የጀመሩት የብልጽግና ጉዞ ውጤታማነት በቀጣይም ሀገራዊ ተልእኮዎች ላይ አጠናክረው ሊያስቀጥሉ ይገባል ሲሉ መክረዋል።
በዚህ ደግሞ የዞናችን ሴቶች የነበራቸው ሚና እጅግ ከፍተኛ ነበር ያሉት አቶ አለማየሁ በቀጣይም የበለጸገች ኢትዮጵያ ለመፍጠር የሴቶች ድርሻ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪና ይህን ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል እንዳሉቱ ዞናችን በራስ አቅም የመቻል እና የፓርቲው ኢኒሼቲቮች ተግባራዊ ማድረጊያ ተምሳሌት ዞን ነው።
የሴቶች አደረጃጀቶች በማጠናከር የሚያነሱት የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመፍታት መንግስት በትኩረት ይሰራልም ብለዋል።
በመሆኑም የቀጣይ ምርጫ ሰላማዊ፣ነፃ ፣ዲሞክራሲያዊና በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያለው እንዲሆን በአደረጃጀታቸው ታቅፈው የበለጠ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የክልሉ ሴቶች ክንፍ አስተባባሪ አባል ወ/ሮ አስቴር ይርዳው በጉራጌ ዞን በሴቶች የሚሰሩ ስራዎች በክልልና በሀገርም ሞዴል ተግባራቶች ናቸው።
እቁብ፣እድር እና ውጆ ባህላቸው የሆነው የዞኑ ሴቶች እነዚህን በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል።
በዞኑ ሴቶች በአመራርናነት እንዲቀመጡና በሌሎችም ውሳኔ ሰጪ እንዲሆኑ እየተሰራ ያለው ተግባር የሚበረታታ ነው ብለዋል።
ወ/ሮ አስቴር አክለውም የሴቶች ጉልበት፣ጊዜና ገንዘብ ሊቆጥቡ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎች በማቅረብ እረገድ መንግስት በትኩረት እንደሚሰራበት አስገንዝበዋል።

የጉራጌ ዞን ሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት ሲቲ አብራር እንደተናገሩት በሀገራችን የተጀመረው ለውጥ ሴቶችን ከተመለካችነት ወደ ተዋናይነ፣ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፣ ከማጀት ወደ መድረክ ያመጣ ለውጥ መሆኑን በተግባር የታየበት ነው ብሏል።
የጉራጌ ዞን ሴቶች የፓርቲው የድልና የስኬት ጉዞ እንዲሁም ለሀገራዊ ፕሮጀክቶች ስኬት ግንባር ቀደም ሚናቸው ተወጥተዋል ነው ያሉት።
በጉራጌ ዞን የፖርቲው ተልእኮና ኢኒሼቲቮች በትክክል ተግባራዊ ተደርገዋል ያሉት ወ/ሮ ሲቲ በቦንድ ግዢ፣በአርጓዴ አሻራ፣በበጎ ፍቃድ ፣በግብርና፣በጤና ፣ገበያ በማረጋጋት፣በትምህርት እና በሌሎችም ሞዴል ስራዎች ማከናወናቸው ተናግረዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ ሴቶች እንዳሉት ከለውጡ መንግስት ጀምሮ ሴቶች በተፈጠረላቸው የልማትና የውይይት እድል በማግኘታችን በአግባቡ ተጠቃሚ ሆነናል ብለዋል።

በሌማት ትሩፋት፣በጤና ፣ በግብርና፣በከተሞች ልማት፣በኑሮ ማረጋጋት፣በበጎ ፍቃድና በሌሎችም የመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ ተጠቃሚ መሆናቸው አንስተዋል።
በቀጣይ በውሃ፣በመብራት፣በስራ እድል እና በግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ በትኩረት እንዲሰራበት ጠይቀዋል።
የዘንድሮ ምርጫ ሰላማዊ ፣ፍትሀዊ ፣ዲሞክራሲያዊ እና ታማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላችን እንወጣለን ብለዋል።
የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ

