ግንቦት 27/2016ዓ.ም [ወልቂጤ]
ዜጎችን ከተረጂነት አስተሳሰብ ለማላቀቅ እና በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት እንዳለበት ተገለፀ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፅህፈት ቤት “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ፣ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነትና ክብር ” በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ዜጎችን ከተረጂነት አስተሳሰብ ለማላቀቅና በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከተማ አቀፍ እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አብድልበር ሰኢድ እንደገለፁት የተረጂነትን አስከፊነትና ጉዳት ከሀገር ሉዓላዊነትና ሁለንተናዊ ብልፅግና አኳያ በጥልቀት በመረዳት ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል ።
ተረጂነትን ማስወገድ የሚቻለው የኪራይ ተሰብሳቢነትና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከቀኝ ግዛት አስተሳሰብ መውጣት ሲቻል እንዲሁም ለራሱ ሉአላዊነትና ክብር ያለው ህብረተሰብን መፍጠር ሲቻል መሆኑም ገልፀዋል።

አቶ አብድልበር አያይዘውም የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት የማይበገር ማህበረሰብ በመፍጠር ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገረውና የወረስነውን እዳ ለልጆቻቸን እንዳናስተላልፍ ተረጂነትን በማስቀረት የበኩላችንን መወጣት አለብን ሲሉ ጠቁመዋል ።
የከተማ ግብርና በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ የመምራት እና የምግብ ዋስትና በማረጋገጥ ወጣቱ ክፍል የአንበሳውን ድርሻ በመውሰድ ማህበረሰባችንን ከጠባቂነት አስተሳሰብ ማላቀቅ እንደሚገባም አቶ አብድልበር አስገንዝበዋል ።
የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ያለንን ጥቂት ቦታ በአግባቡ በመጠቀም ለራሳችንና ለማህበረሰባችን ተምሳሌት በመሆን እየተፈጠረ ያለውን የኑሮ ጫና መቀነስ እንደሚገባም አብራርተዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ ጴጥሮስ አስራት እንደተናገሩት ሉዓላዊነታችን በማስከበር እና ክብራችንን በማስጠበቅ የተረከብናትን ሀገር ለማልማትና ድህነትን ለማስቀረት ማህበረሰባችንን የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ የሌማት ትሩፋት ተጠቃሚ እንዲሆን የማስቻል ስራ አጠናክረን ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
ከተማችን በሁሉም መስክ በሚባል ደረጃ በቂ የተፈጥሮ ሀብት ፣እውቀት እንዲሁም የሰው ሀይል ያላት ሲሆን በአስተሳሰብ ድህነት ምክንያት የራሳችንንና የከተማችንን ማህበረሰብ ክብር የማይመጥኑ ድርጊቶችን በመለየት ሁሉም ባለበት የሀላፊነት ቦታ የድርሻውን ወስዶ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል ።
አያይዘውም አቶ ጴጥሮስ ውጤታማ ስራ ሰርተን በሁሉም ቤተሰብ ደረጃ የራሱ የምግብ ዋስትና በማረጋገጥ ከጠባቂነት አስተሳሰብ በመራቅ እንዳለበትም ጠቁመዋል ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት ወይዘሮ መንዚላት አህመድ እንደተናገሩት የተረጂነት አስከፊነት በመረዳት ያሉንን መልካም አጋጣሚዎች ተጠቅመን ለከተማችን ነዋሪዎች ግንዛቤ በመፍጠር መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
ተረጂነት ለአንድ ሀገር ያለው ተፅዕኖ ከፍተኛ ሲሆን የረጂዎችን ፖለቲካዊ ፍላጎት እያስታመምን አሊያም በተወሰነ ደረጃ በጥቅማችን እና በፖሊሲ ጉዳዮች ሙሉ በሙሉ ነፃነት እንዳይኖረን በመፍቀድ በኢኮኖሚና በፖለቲካ ከፍተኛ ውድቀት እንደሚያስከትልም ተናግረዋል ።
ወይዘሮ መዚላት አያይዘውም “እንችላለን ” በሚል እሳቤ ፈጥረን ቀበሌ ድረስ ህዝቡን አነቃንቀን ለችግር የዳረጉንን ኢኮኖሚያዊ መንስኤዎች አየለየን የጠባቂነት እና የተረጁነት አስተሳሰብ ከህብረተሰባችን ነቅለን ማውጣት ይኖርብናል ብለዋል።
በውይይት የተሳተፉት አመራሮች እንደተናገሩት ዜጎቻችን ከተረጂነት አስተሳሰብ ለማላቀቅ እና በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ሁላችንም በተሰማራንበት የስራ ዘርፍን ሆነ በመኖሪያ አካባቢያችን ያለንን ቦታ በመጠቀም ሰርተን በማሳየት ምሳሌ መሆን አለብን ሲሉ ተናግረዋል ።

ይህንን መልካም ስራ ለማሳለጥ የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት የልመናና የተረጂነት ስሜት በማስወገድ እንዲሁም የምግብ ዋስትናን በዘላቂነት ለመፍታት የከተማው አመራርም ሆነ ነዋሪ ውጤታማ ስራን ለመስራት በጋራ መረባረብ እንደሚገባ ገልፀው መድረኩን ተጠናቋል ።

