ወልቂጤ ከተማ የታታሪ ህዝቦች መኖሪያ፣ ህብረ- ብሔራዊነትን የሚገለፅባት፣ ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች በፍቅርና በሰላም የሚኖሩባት ከተማ እንደመሆኗ መጠን ለኑሮ አመቺና የበለጸገች ከተማ እንድትሆን ይበልጥ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

የበለፀገች ኢትዮጵያና ወልቂጤ ለመፍጠር አንድነት፣ ገዢ ትርክት፣ መቻቻል እና ኢትዮጵያዊነትን ማጽናት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ህዝቡ የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ መንግስት በትኩረት ይሰራል፦ ዶክተር አበባየሁ ታደሰ

ታህሳስ O4/2O18ዓ/ም [ወልቂጤ]

“የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሲካሄድ የነበረው ህዝባዊ የውይይት መድረክ ተጠናቋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት፣ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባል ዶክተር አበባየሁ ታደሰ በውይይት መድረኩ ልዩነቶቻችንን በማጥበብ አንድ በሚያደርጉን ጉዳዮች ላይ አትኩረን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

ወልቂጤ ከተማ የታታሪ ህዝቦች መኖሪያ፣ ህብረ- ብሔራዊነትን የሚገለፅባት፣ ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች በፍቅርና በሰላም የሚኖሩባት ከተማ እንደመሆኗ መጠን ለኑሮ አመቺና የበለጸገች ከተማ እንድትሆን ይበልጥ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

የበለፀገች ኢትዮጵያና ወልቂጤ ለመፍጠር አንድነት፣ ገዢ ትርክት፣ መቻቻል እና ኢትዮጵያዊነትን ማጽናት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ከተማው የብዙ ክልሎች መሸጋገርያ ስትሆን ለኢንቨስትመንት፣ ለንግድ፣ ለቱሪዝም እና በሌሎችም የመልማት አቅም ያላት ከተማ በመሆኗ ሁሉም በትብብር እንዲያለማትና ሰላሟን እንዲያስጠብቅላት ዶክተር አበባየሁ መክረዋል።

የወልቂጤ የድንበር ጣልቃ ገብነት የክልሉ መንግስት በጥናት እንደሚፈታው አመላክተው ህዝቡ የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ መንግስት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በዛሬው እለት በውይይቱ የተነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ለሚመለከተው አካል በአግባቡ ተደራሽ እንደሚደረግም አስታውቀዋል።

በሚኒስተር ማዕረግ የብልጽግና ፓርቲ የጥናትና ምርምር ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር አብድልዋስ አብዱልዋሂ በበኩላቸው እንደሀገር አምስት የኢኮኖሚ ምሶሶዎችን መሠረት በማድረግ የሀገሪቱን እድገት ፈጣንና ቀጣይነት ለማረጋገጥ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን በመጠቀም ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሻገር የሚያስችሉ ስራዎች እየተሠሩ መሆኑን ተናግረዋል።

ዶክተር አብድልዋስ አክለውም አንድነትና መተሳሰብን የዕድገት መሳሪያ አድርጎ በመጠቀም ሁለንተናዊ ለውጥ ለማስመዝገብ በጋራ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።

በስራ ፈጠራ፣ የኑሮ ውድነት በመቀነስ፣ ቱሪዝሙን፣ ከተሜነትን ማዘመን፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሳደግ እንደሚጠበቅ ገልፀው በአገልጋይነት መንፈስ በመስራትና መልካም አስተዳደርን በማስፈን በማህበራዊ፣ በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚና በዲፕሎማሲ የተገኙ ስኬቶችን ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል ዶክተር አብድልዋስ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፍቃዱ በዚህ ወቅት እንዳሉት የጉራጌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እያስመዘገበ ያለው ውጤት እንደ ሃገር የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ የተያዘውን እቅድ ስኬታማ በማድረጉ ላይ የራሱን አሻራ እያኖረ ነው።

ይህም የግብርና ምርቶችን በብዛት በማቅረብ የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት ሚናው የጎላ ነው ያሉት ሃላፊው ከዚህ በተጨማሪም ከሰንበት እስከ ሰንበት ሳምንታዊ የገበያ አገልግሎት እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ እንደ ክልልም ጉራጌ ዞን በኢትዮ ኮደርስ፣በስራ ፈጠራ በግንባር ቀደምት ተሸላሚ መሆኑን ገልጸው በቴክኖሎጂው ዘርፍም እንደ ሀገር ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎች በማበርከት የድርሻውን ሚና እየተወጣ መሆናንም ጠቁመዋል።

በወልቂጤ ከተማም የተጀመሩትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች እጅግ ተስፋ ሰጪ በመሆናቸው ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ከከተማው ወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ በአጥኚዎች ቡድን ተጠንቶ የተጠናቀቀ መሆኑና ውጤቱ ይፋ እስኪደረግ ማህበረሰቡ በትእግስት እንዲጠብቅም አስገንዝበዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር በበኩላቸው የሰላምና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ሰፊ ስራዎች ተሰርተዋል።

በዚህም ከ6 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማውጣት በከተማው አገልግሎት እየሰጡ ለሚገኙ ለሶስቱም ጤና ጣቢያዎች የሲቢሲ ማሽን ግዢ በመፈፀም ለታካሚው ማህበረሰብ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን አስረድተዋል።

የከተማው የቱሪዝም እንቅስቃሴ ለማዘመን የዋቤ ወንዝ ከ3 መቶ ሜጋ ዋት በላይ የሚያመነጭ ፕሮጀክት ተጠንቶ ወደ ተግባር መገባቱ አቶ ሙራድ ጠቁመዋል።

በገቢ አሰባሰቡ ረገድም ጠንካራ የገቢ ሰራዊት ተፈጥሮ እየተሰራ መሆኑንና የከተማው ኮሪደር ልማት እንቅስቃሴ በተሳለጠ መልኩ እየተከናወነ መሆኑንም አስረድተዋል።

ለተሰሩ ውጤታማ የልማት ስራዎች በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት እና የከተማው ነዋሪዎች ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነው ከተማዋ የብልፅግና የስበት ማዕከል ለማድረግ በቅንጅት እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

ተግባራቱን ለማስቀጠል የአመራርና የህብረተሰቡ ቅንጅትና ትብብርን ይበልጥ ማጠናከር ይገባል ሲሉ ከንቲባው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ብልጽግና በየጊዜ እያመጣቸው ያሉ ለውጦች እጅግ አመርቂ መሆናቸውና ሰው ተኮር ፓርቲ በመሆኑ በሰዎች ህይወት ላይ ተጨባጭ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ጠቅሰዋል።

እነሱም መንግስት ያወረዳቸው ኢኒሼቲቮች በአግባቡ በመተግበርና ብልጽግናን በማረጋገጥ የበኩላቸው እየተወጡ መሆኑን ገልጸው በኮሪደር ልማት፣ በግብርና፣ በጤናና በሌሎች የልማት ስራዎች ከመንግሥት ጋር ተቀናጅተው እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

የጉራጌ ማህበረሰብ ከሌሎች ብሔር-ብሔረሰቦች ተዋዶና ተፈቃቅሮ የመኖር እሴቱን ይበልጥ በማጠናከር የወልቂጤ ከተማ ልማት ለማረጋገጥ በአብሮነትንና በመቻቻል እሴት ለከተማው ልማት በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ በከተማው የወሰን ጣልቃ ገብነት መኖሩ የከተማው ሰላም እና ልማት በተፈለገው ልክ እንዳይረጋገጥ እያደረገው በመሆኑ መንግስት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጠው ጠይቀዋል።

cc Wolkite City Administration Government Communication Affairs Office 

Previous “የገቢ አሰባሰብ ስራ የብልፅግና ጉዟችንን የሚያፋጥን የራስን አቅም የመገንቢያ ቁልፍ መሳሪያ ነው” የጉራጌ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል:-

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo