የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ከወልቂጤ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በኮደር ስልጠና ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የግብ ስምምነት ተፈራረሙ።

የግብ ስምምነቱ የተቋማቱ ተግባርና ሃላፊነትን በግልፅ በመለየት የተቀመጠውን ራዕይ በአግባቡ ለማሳካት ያስችላልም ተብሏል፡፡

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሃምዱ ካሚል በዚህ ወቅት እንደገለፁት የግብ ስምምነቱ ቀጣይ በሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ይኖረዋል።

ከኮሌጁ ጋር የግብ ስምምነት መደረጉ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ላይ ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ የቴክኖሎጂ ስራዎችን በተገቢው በማልማትና በመተግበር በዘርፉ የወጣቱን አቅም ለማዳበር ያስችላል ነው ያሉት ሀላፊው።

እንደሃገር ብሎም እንደከተማ በዘርፉ የተቀመጡ ተግባራት ከግብ ለማድረስ በሚደረገው ጥረት የተቋማቱ በቅንጅት መስራት ወሳኝ ነው ያሉት ሃላፊው ለዚህም ያመች ዘንድ የአሰራር ስርአትን ለመርጋት አጋዥ የሆነ የህግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱንም ተናግረዋል።

ከወረቀት ንክኪ ነፃ የሆነ አሰራር ለመዘርጋት የተጀመረው ስራ እውን እንዲሆን በሶስት አመታት ውስጥ እንደከተማ 6ሺህ ወጣቶችን ለማሰልጠን እቅድ መያዙን ገልጸው የታቀዱ ተግባራትን በውጤታማነት ለመፈጸም የአመራሩ እና የባለሙያው የላቀ ጥረት እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።

የወልቂጤ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሃይሩ አህመዲን በበኩላቸው ሃገሪቱ በ2025 ለወጠነችው የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ መሰረት ያደረገ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ለዘህም መንግስት 5 ሚልየን ዜጎች የኮዲንግ ስልጠና እንዲያገኙ ከተባበሩት አረብ ከኤሜሬትስ መንግስት ጋር ውል መግባቱን አስታውሰዋል።

ኮሌጁ በተለይም ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ላይ በትኩረት የሚሰራበት በመሆኑ በዚህም ከከተማው ሳይንስና ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ጋር በመቀራረብ እየሰሩ እንደነበር ገልጸው የግብስምምነቱንም በቀጣይ የበለጠ ለመስራት የሚያስችላቸው መሆኑን ነው ያወሱት።

የግብ ስምምነቱ የተቋማቱ ተግባርና ሃላፊነት ምንድነው የሚለውን ለይቶ ለማወቅና የተቀመጠውን ራዕይ እንዴት በጋራ ማሳካት ይቻላል የሚለውን ተግባር በአግባቡ ለመወጣት ከፍ ያለ ሚና ይጫወታልም ነው ያሉት አቶ ሃይሩ።

በመሆኑም ወጣቱ የተመቻቸውን እድል በመጠቀም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የበለፀገ የእውቀት ባለቤት መሆን ይጠበቅበታልም ብለዋል።

Previous በተለያዩ ሙያ ዘርፎች ፍላጎታቸው መሰረት ያደረገ በመሰረታዊ በኮምፒውተር ክህሎት ስልጠና ፣በጋርመንትና በሶፍትዌር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ለ550 ለሚሆኑ ተማሪዎች ለአንድ ወር ስልጠናው መሰጠቱን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅህፈት ቤት ገለፀ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo