በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ የማህበረሰብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

“ንቁ ብቁ ጤናማ ማህበረሰብ ሲቪል ሰርቫንት እና አመራር ለላቀ አገልግሎት ❗️በሚል ሚሪ ቃል የማህበረሰብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል ።

የካቲት 16/2016ዓ.ም [ወልቂጤ ]

በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ የማህበረሰብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ‼️

“ንቁ ብቁ ጤናማ ማህበረሰብ ሲቪል ሰርቫንት እና አመራር ለላቀ አገልግሎት ❗️በሚል ሚሪ ቃል የማህበረሰብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል ።

የማህበረሰብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ የተገኙት የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እንዳለ ስጦታው ስፖርት በአካልና በአእምሮ የጎለበተ ማህበረሰብ ለመፍጠር ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልፀዋል ።

የማህበረሰብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሰዎች አካላዊ ብቃታቸው ከመጠበቅ ባሻገር ስለ ሰላም ፣ፍቅር ፣አንድነት እንዲሁም ወንድማማችነት የሚያጠናክሩበት መሆኑን ተናግረዋል ።

በከተማችን የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ለማሳለጥ የስፖርቱ ማህበረሰብ አጋዥነት ከፍተኛ መሆን መቻል አለበት ያሉ ሲሆን በዚህ መርሀ ግብር ላይ ለተሳተፉት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ስራጅ ኑርበገን እንደተናገሩት የእርስ በእርስ ግንኙነት በማጠናከር ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

በከተማችን ሁሉንም ህዝብ ያሳተፈ ለሶስተኛ ጊዜ የተዘጋጀው የማህበረሰብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በየአስራ አምስት ቀኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

የማህበረሰብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው አበክረን የምንሰራ ይሆናል ያሉት አቶ ስራጅ በከተማች የሚገኙ ስፖርት ቤቶች እያደረጉት ያለው ድጋፍ ከፍተኛ ሲሆን ሳሬም ጂም ፊትነስ የዛሬው መርሀ ግብር በተሳካ ሁኔታ እንዲሳካ ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

በዛሬው የማህበረሰብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፍ አካላት በማመስገን ቀጣይም የከተማችን ነዋሪም እንዲሳተፍ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

Previous የሆቴል ኢንቨስትመንት ቱሪስቶችን ከመሳብ ባለፈ ለዜጎች የሚፈጥረው የስራ እድል ከፍተኛ በመሆኑ ዘርፉን ለማሳደግ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo