***********

“በ2030 ወደ አምስተኛው ትውልድ የጦር መሣሪያ ቴክኖሎጂ እንሸጋገራለን” የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
************
በ2030 ወደ አምስተኛው ትውልድ (5th Generation) የጦር መሣሪያ ቴክኖሎጂ እንሸጋገራለን ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢፌዲሪ አየር ኃይልን 90ኛ ዓመት በማስመልከት በተዘጋጀው የጥቁር አንበሳ የአየር ላይ ትርዒት መርሐ-ግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በ2030 ወደ አምስተኛው ትውልድ የጦር መሣሪያ ቴክኖሎጂ እንሸጋገራለን ብለዋል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል አቅም በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በእጥፍ እንደሚያድግም ተናግረዋል።

አሁን ላይ አራተኛውን ትውልድ (4th Gen) የመዋጋት ብቃት የገነባው አየር ኃይላችን፣ በ2030 ወደ አምስተኛው ትውልድ ቴክኖሎጂ ይሸጋገራል ነው ያሉት።

“ውጊያን በቴክኖሎጂ በማሳጠር የሚደርሰውን ጉዳት መቀነስ ቀዳሚ አቅጣጫችን ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለዚህም መንግሥት በጀት እና የቴክኖሎጂ ምንጭ ለይቶ ወደ ሥራ መግባቱን አረጋግጠዋል።

