የወልቂጤ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ ለማስጠበቅ ህብረተሰቡ ለሰላም በየአካባቢው ዘብ መቆም እንዳለበት ተገለፀ።

በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ በሶስቱም ክፍለ ከተማ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በከተማው ሰላምና ልማት ዙሪያ ውይይት አካሄደ።

በውይይት መድረኩም በወልቂጤ ከተማ የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ሁሉም የከተማው ነዋሪ የድርሻውን በመወጣት የጥፋት ሀይሎች በህግ ተጠያቂ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት የከተማው ነዋሪ አጋዥ ሊሆን እንደሚገባ ተገለፀ።

በከተማው እየተፈጠረ ያለውን ሰላም ለማስጠበቅ የፀጥታው መዋቅር ህግን ለማስከበር ተጠናክሮ እየሰራ እንደሚገኝ በውይይቱ ተገልጿል።

ወልቂጤ ከተማ የሁሉም ብሔር ብሄርሰቦች በአንድነት የሚኖሩባት ከተማ ስትሆን በጥቂት የጥፋት ሀይሎች ለግል ጥቅማችው ለማስከበር ከተማዋ እንዳትረጋጋና ከልማት ጎዳና ለመነጠል የሚያደሩጉትን እንቅስቃሴ የከተማው ህዝብ በባለቤትነት ሊታገል እንደሚገባና መንግሥት ያስቀመጣቸው ጉዳዮች በጊዜና በአግባቡ የሚፈቱ እንደሆነና እስከዛው ድረስ ማህበረሰቡ ፊቱን ወደ ልማት በማዞር የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ከመንግስት በጋራ በመሆን አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበትም በውይይቱ ተገልጿል ።

በክፉም ሆነም በደጉ አብሮ የኖረን የጉራጌ እና የቀቤና ብሔረሰብ ለማጋጨትና የራሳቸው ኑሮ አመቻችተው የሌላውን ሰላም በማደፍረስ እየተንቀሳቀሱ ያሉ አካላት ህጋዊ የሆነ እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚገባና በዚህ ተግባር ተሳታፊ የሆኑትን ፀረ ሰላም ሀይሎችን ለፀጥታው መዋቅር አሳልፈው መስጠት እንዳለባቸውም ተነስቷል ።

እንዲሁም ትምህርት ቤቶች ሀገር ተረካቢ ዜጋ መፍጠሪያና ከየትኛውም ፖለቲካ እና ዘረኝነት ነፃ ሆነው ትውልድ የሚቀረፅባቸው መሆን ሲገባቸው በጥቂት ፀብ ጫሪዎች ተነሳሽነት የህፃናትን አእምሮ በመጠቀም ለመረበሽ ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ መታቀብ እንዳለባቸው በውይይቱ ተገልጿል ።

ከተሳታፊዎች ከተነሱ አስተያየቶች መካከል የከተማችን ማህበረሰብም እንዲህ አይነት ችግር በሚያጋጥምበት ወቅት በተለመደውን ባህላዊ ስርዓትን በመጠቀም ችግሮች በሰላም እንዲፈቱ ውይይቶች መደረጋቸው መልካም መሆኑን ተናግረዋል።

በከተማው የተጀመሩ የልማት ስራዎች መልካም ጅማሮ ላይ ሲሆኑ በቀጣይም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የራሱን አሻራ በማሳረፍ ለከተማዋ እድገት የሚደሰጉ የመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ በቁርጠኝነት አጋዥ እንደሚሆኑም ተናግረዋል።

ከወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ አሁንም ቢሆን የህብረተሰቡ ጥያቄ መሆኑና ሁል ጊዜ ለሚፈጠሩ ችግሮች መንስኤ ሲሆን መንግስት ባስቸኳይ የህግ የበላይነትን በማስከበር የከተማዋን ሰላም እንዲያረጋግጥ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

ትውልድ ይዞ የሚያድገው ከቤተሰብ ብሎም ከማህበረሰቡ የሚወስደው አስተሳሰብና አመለካከት ስለሆነ ወላጆች ለልጆቻቸው መልካም ስነ-ምግባር እና ሀገርን ሊረከብ የሚችል ትውልድን ለመፍጠር መስራት እንዳለባቸው አንስተዋል።

የከተማችን ማህበረሰብም የተፈናቀሉት ሰዎችን ወደ ነበሩበት የመመለስ ስራው በመስራትና ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በመቀናጀት የአካባቢውን ሰላም ለመጠበቅ በሚደረገው እንቅስቃሴ የፀጥታ ሀይሉ ሊያግዝ እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን ነዋሪውም ችግር በሚያጋጥመው ወቅት ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በመቀናጀት መረጃ ልውውጥ እንዲያደርግም ከመድረኩ ተመላክቷል ሲል የዘገበው የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው።

Previous በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ባሉ ቅድመ መደበኛ ትምህር ቤቶች ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ህፃናት በአፋ መፍቻ ቋንቋቸው መማር እንደሚጀምሩ ተገለፀ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo