የሳምንቱ አበይት ዜናዎች

ሰኔ 9/2016[ወልቂጤ]

📌“ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነትና ክብር “በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ ህዝባዊ ውይይት ተካሄደ ።

📌በህዝባዊ የውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጸጋዬ ማሞ እንዳሉት ኢትዮጵያ ታላቅ ሀገር ብትሆንም ለበርካታ አመታት በተረጂነት መኖሯን ገልጸው ያላትን እምቅ ጸጋዎች በተገቢው በመጠቀም ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ከተረጂነት ለመላቀቅ ሁሉም ርብርብ ማድረግ ይገባል

📌በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መሀመድ ኑሪዬ በበኩላቸው እንደ ሀገር ከተረጂነት ለመላቀቅ የማህበረሰቡ የአስተሳሰብና የአመለካከት ችግር ለመቅረፍ በትኩረት መስራት ይገባል።

📌የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንደገለጹት የሀገር ሉአላዊነት ለማስከበርና ከተረጂነት ለመላቀቅ ያሉ እምቅ አቅሞችን በማቀናጀት መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

📌የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አብድልበር ሰኢድ እንደተናገሩት ከተረጂነት ተላቀን የተሟላ ብልፅግና ለማረጋገጥ የጋራ የተቀናጀ ጥረት በማድረግ ያሉንን የተፈጥሮ ፀጋ ተጠቅመን የሚፈለገውን ግብ ማሳካት ይጠበቅብናል ብለዋል።

📌የአፍሪካ የህፃናት ቀን ዘንድሮ በአፍሪካ ደረጃ ለ34 ጊዜ እንዲሁም በሀገራችን ለ33ኛ ጊዜ” የህፃናት የትምህርት ተሳትፎ እና ጥራትን ማሳደግ ጊዜ አሁን ነው” በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ተከበረ።

📌የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የ2016/17ዓ.ም የመኸር ወቅት የተቀናጀ የግብርና ልማት የንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በጉብርየ 01ቀበሌ ተካሄደ።

📌የጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያና ጉራጌ ዞን ሠላምና ፀጥታ የ1445ኛው የአረፋ በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት የፀጥታ ሰራ መጠናቀቁን እና የከተማ ነዋሪ የሰላሙ ባለቤት መሆን ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለበት ተገለፀ።

📌 በወልቂጤ ከተማ በሚገኙ 4 የፈተና ጣቢያዎች ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የነበረው ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

📌በተመሳሳይ ዜና በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የ2016 ዓ.ም 6ኛ ክፍል ዞን ዓቀፍ የእርከን ማጠቃለያ ፈተና በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች ሲሰጥ የነበረው ፈተና በሰላም መጠናቀቁ።

📌በማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል የመሰረተ ልማት ማዕከል የሆነውን ወልቂጤ ከተማ በሆቴል ኢንቨስትመንት ስራ አበረታች ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ተጠቆመ።

📌በጉራጌ ብሔረሰብ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶት በየአመቱ በድምቀት የሚከበረው የአረፋ በዓል የጉብርየ ሳምንት ገበያ ደምቆ መቆየቱን ተገለፀ፡፡

📌እንኳን ለ1445ኛ የኢድ አል አድሀ አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲል የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት መልዕክት አስተላለፈ ።

📌የኢድ አል አድሀ አረፋ በዓል ምክንያት በማድረግ ሳምንታዊ የፅዳት ዘመቻ በተሻለ መልኩ ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ በሁሉም ቀበሌዎች ተካሄደ።

📌የዘንድሮ የኢድ አል አድሀ አረፋ በዓል ገበያ ካለፈው አመት ገበያ ሲነፃፀር ምርቶች ላይ መጠነኛ ጭማሪ መታየቱ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ንግድ ገበያ ልማት ፅህፈት ቤት አስታወቀ ።

📌የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ የእንኳን ለ1445ኛው የኢድ-አል አድሀ አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ ።

📌የአረፋ በአል የመስዋዕትና የደስታ በአል በመሆኑ ሙስሊሙ ህብረተሰብ አረፋ በአል ሲያከብር አቅም የሌላቸው ወገኖች በደስታ እንዲያሳልፉ ድጋፍ በማድረግ መሆን እንዳለበት በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብድልበር ሰይድ ገልፀው ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለአረፋ በአል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

📌ከተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የኢድ- አል አድሀ የአረፋ በዓል ለማክበር ወደ ዞኑ መቀመጫ የሆነችው ወልቂጤ ከተማ በርካታ የአካባቢው ተወላጆችና እንዲሁም በዓሉን ለመታደግ ወደ ከተማዋ የሚገቡ እንግዶች ተቀብላ እያስተናገደች ተቀብላለች ።

📌የ 2ተኛ ዙር በተስፋ ንዳ በማህበራዊ ሚዲያ ቤተሰቦች የመቶ ብር ቻሌንጅ ገንዘብ በማሰባሰብ የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ ተካሄደ።

Previous ጉራጌ ዞን በአጠቃላይ ውጤት 1ኛ ደረጃ በመያዝ ተሸላሚ ሲሆን ውጤት የተመዘሀበባቸው ዘርፎች:-

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo