በሁሉም ዘርፍ በከተማችን ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት ለማረጋገጥ በህብረተሰቡ የሚነሱ የነበሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ደረጃ በደረጃ በፍጥነት በጥራት የተሰራ ይገኛል :-የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር
ነሀሴ 16/2017ዓ.ም [ወልቂጤ ]

የወልቂጤ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዙር -12ኛ ዓመት 46ኛ መደበኛ ጉባዔ አካሄደ።የወልቂጤ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፈሰሰወርቅ ገ/ሰንበት እንደተናገሩት ዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የምክር ቤት አባላት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የዜጎች ሰብዓዊ መብቶች በአግባቡ እንዲጠበቅና እንዲከበር የድርሻቸውን ወስደው ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።በልማቱ የህዝቡ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የአስፈጻሚ አካላት ቁጥጥርና ክትትል ስራዎች በማጠናከር የመንግስት እና የህዝብ ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ በማዋል ለጋራ ውጤትና ልማት ልንሰራ ይገባል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እንደገለፁት 2ዐ17 በጀት ዓመት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚ ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች በቀጣይ በጀት ዓመት አጠናክረን ማስቀጠል መቻል አለብን ሲሉ ተናግረዋል።በሁሉም ዘርፍ በከተማችን ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት ለማረጋገጥ በህብረተሰቡ የሚነሱ የነበሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ደረጃ በደረጃ ለመፍታት በፍጥነት በጥራት የተሰራበት ያለ አግባብ መኖሩን አብራርተዋል።

በመደበኛና በማዘጋጃ ቤት የገቢ አሰባሰብ ስርዓታችን ከባለፈው አመት በንፅፅር የተሻለ አፈፃፀም መኖሩን የተናገሩት ከንቲባው ቀጣይ ከተማዋን በልማትና በብልፅግና ከፍ ለማድረግ ከተማዋ ያላትን ፀጋና ሀብት በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል።
በከተማችን የተጀመሩ የልማት ስራዎች በጥራትና በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ከተማ አስተዳደሩ የክትትልና የቁጥጥር ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል ።
ህዝብ ከህዝብ የሚያቀራርብ ስራዎችን ተቀራርበን በመስራት የከተማው ሰላምና ፀጥታ በሚያረጋግጡ ተግባራት በማከናወን ልማታችንና ብልፅግናችንን ልናረጋግጥ ይገባናልም ብለዋል ።

በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ በትምህርት ፣በጤና ፣ በመሰረተ ልማት ፣አንፃራዊ ለውጥ የታየበት የንፁህ ውሃ አቅርቦት እንዲሁም ውብ ፅዱና አረንጓዴ ከተማ ለመፍጠር በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀው ቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል ሲሉ አንስተዋል።
የቀጣይ እቅዳችን ከተማዋን ሊለውጥና ሊያሻግር በሚችሉ ተግባራት እና ወቅቱን የሚመጥን በሀገራችን ካሉ ከተሞች ተወዳዳሪ ሆና ህዝቦቿ በሰላም ወጥተው የሚገቡባት እንዲሁም የብልፅግና ማዕከል እንድትሆን ለማስቻል የከተማው ነዋሪ በሁሉም ዘርፍ በባለቤትነት ማገዝ ሲችል መሆኑን ጠቁመዋል ።ከምክር ቤት አባላት በሰጡት አስተያየት ወልቂጤ ከተማን በልማትና በመልካም አስተዳደር ስራዎች የሚጠበቀውን ውጤት ለማምጣት ሁሉም በቅንጅት በባለቤትነት መስራት ሲችል መሆኑን አንስተው ሁላችንም የድርሻችንን ወስደን ልንሰራ ይገባል ብለዋል።

በጉባዔ ለተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድርና የተቋማት የስራ ሀላፊዎች ምላሽና ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።የወልቂጤ ከተማ ምክር ቤት፣ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የቀጣይ የ2018 በጀት ዓመት ጠቋሚ እቅድ ላይ ከምክር አባላት ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓ።
በመጨረሻም የ2018 በጀት ዓመት የከተማ አስተዳደሩ የልማት የመልካም አስተዳደርና የሰላምና ፀጥታ ተግባራት ከምክር ቤቱ ጋር የውል ስምምነት በማድረግ ባለፈው በጀት አመት ተቋማት በገቡት የግብ የውል ስምምነት እና ሞዴል የምክር ቤት አባል እውቅና ተሰጥቷል ።

