ሳይንስ፣ኢኖቬሽንናቴክኖሎጂ የመጪው ትውልድ ቋንቋ ነው።” በሚል መሪቃል የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት 3ተኛ ዙር የሳይንስ ሳምንት በከተማ ደረጃ በሰላምበር ትምህርት ቤት በድምቀት አከበረ።

በtማሪዎች የሚሰሩ የሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ሥራዎች ዘላቂ ሀገራዊ ለውጥን ለማስመዝገብ የሚፈጥሩት አሻራ ከፍተኛ መሆኑን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሃምዱ ካሚል ገልፀው።
ለሀገራችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ የመጠቁ ዜጎችን ለማፍራት የባለድርሻ አካላት አስተዋጽኦ የሚጠይቅና ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ፈጠራ ዝንባሌን ለማጎልበት በየትምህርት ቤታቸው በሚገኙ የፈጠራ ክበቦች በመሳተፍ የሳይንስና ቴክኖሎጂ አቅማቸውን ማዳበር ይጠበቅባቸዋል ያሉ ሲሆን

ሳይንስና ቴክኖሎጂን በመጠቀም የዳበረ የፈጠራ አቅም በማጎልበት ልማትን የሚያሳካ ትውልድ ለመፍጠር ተባብረን በመሥራት የሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የፈጠራ ባህል አድማሱን በማስፋት እስከታች ባሉ ትምህርት ቤቶች ላይ አጠናክረን እንሰራለን ሲሉ አቶ ሃምዱ ካሚል ገልጸዋል።

የሰላምበር 1ኛደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ኑርጋ ገብሬ እንደገለፁት በትምህርት ቤታችን የሳይንስ ሳምንት ሲከበር የተማሪዎቻችን የሳይንስ ትምህርት ፍላጎት ለማሳደግ እንደሚያግዝና ሳይንሳዊ እንቅስቃሴዎችና የፈጠራ ሥራዎች ለማጠናከር እንደሚረዳ እሙን ነው ያሉ ሲሆን
ሳይንስ ለአንድ ሀገር እድገት ብልፅግና ወሳኝ በመሆኑ መምህራን ተማሪዎችን በሳይንስና ፈጠራ እውቀት ብቁ እንዲሆኑ እየሰሩ ይገኛሉ ሲሉ አብራርተዋል።
ተማሪዎች ያላቸውን የሳይንስና ፈጠራ እምቅ ችሎታ እንዲያወጡ ትምህርት ቤቶች መነሻ በመሆኑ የፈጠራ ክህሎት ያላቸው ተማሪዎች በከተማችን ብሎም በዞናችን በመኖራቸው የፈጠራ ሥራዎቻቸውን በስፋት እንዲያስተዋውቁ ልናግዛቸው ይገባል ሲሉ የትምህርት ጽህፈት ቤት ባለሞያ የሆኑት አቶ ደምስ ፈቀደ ገልጸዋል።

የሳይንስ ሳምንት በተከበረበት ወቅት ያነጋገርናቸው የፈጠራ ስራ ካቀረቡ ተማሪዎች መካከል ተማሪ ሙአጅር ካሚል አበሩስ ወልቂጤ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና ፍፁም ወርቁና ይገኙበታል ።

ተማሪዎቹ ከሰሩት የፈጠራ ስራዎች መካከል የሆቴል ወስጥ የተለያዩ መስተንግዶ የሚሰጥ ርሆቦት እና ዘመናዊ የሆነ የቤት መቋጣጣሪያና የቤት ውስጥ እቃዎችን በዘመናዊ መንገድ መጠቀም የሚያስችል ቴክኖሎጂ ሲሆን በውስጡ ዝርዝር ተግባሮችን የያዘ የፈጠራ ስራዎችን መስራታቸውን ገልጸዋል ።

ተማሪዎቹ እንደገለፁት በዞናችንም ሆነ በከተማችን ብዙ አቅም ያላቸው ተማሪዎች እንዳሉ ገልጸው አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ ቢደረግ ከዚህ የተሻሉ የፈጠራ ሥራዎችን መስራት እንደሚቻል አብራርተዋል።
በመርሃ-ግብሩ ላይም የተማሪዎች የመማሪያ ላቦች ጉብኝት የተደረገ ሲሆን በተማሪዎች የተሰሩ የፈጠራ ስራዎች ፣የቤተ ሙከራ ጉብኝት እና የጥያቄና መልስ ውድድር እንዲሁም ቀኑን የሚመለከት በተማሪዎች ጭውውት ቀርቧል።

እንዲሁም የፈጠራ ስራ ላቀረቡ ተማሪዎች የእውቅና የምስጋና ሠርተፍኬት ለትምህርት ቤቱ፣ጥያቄና መልስ ላሸነፉ ተማሪዎች የመጽሐፍና የሰርተፍኬት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ።
በመድረኩም የከተማ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ኃላፊና ባለሞያዎች፣የሰላምበር ትምህርት ቤት መምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል።









