ጥር 14/2017ዓ.ም [ወልቂጤ ]
ጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓታቸውን በማስፋት ጤናማ ዜጋና ማህበረሰብ ለመፍጠር እያደረጉት ያለው ተግባራት ማስቀጠል መቻል እንዳለባቸው የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅህፈት ቤት አስታወቀ ።
የወልቂጤ ጤና ጣቢያ የ2017ዓመተ ምህረት የግማሽ ዓመት የማህበረሰብ የውይይት መድረክ አካሄደ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የከተማ ጤና ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሙባሪክ ዘይኑ እንደገለፁት ወልቂጤ ጤና ጣቢያ ለከተማዋ ማህበረሰብ በጤናው ዘርፍ እያበረከተ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ተቋሙ የአገልግሎት አድማሱ በማስፋት ከከተማው ማህበረሰብ አልፎ ለአጎራባች ወረዳዎች በተለያየ መልኩ ድጋፍ እያደረገበት ያለው መንገድ ከፍተኛ ነው ያሉ ሲሆን በከተማች የሚገኙ ጤና ተቋማት ተሞክሮ ወስደው ሊማማሩበት ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል ።
አቶ ሙባሪክ አያይዘው ውጤታማ ስራ ለመስራት የሁሉም ርብርብና ቅንጅታዊ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ጠቅሰው የተቋሙ አመራር ፣የማኔጅመንት አካላትና ባለሙያዎች ጥንካሬና የአገልጋይነት ስሜት አመስግነው ጤና ጣቢያውን ከፍ ብሎ ሆስፒታል ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ተግባራ ሁላችምም በሃላፊነት አግዘን ማስቀጠል መቻል አለብን ሲሉ ጠቁመዋል።
ከተማ አስተዳደር ባለው አቅም ተቋሙ እየገጠመው የግብዓት ችግር ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ሲሆን የኬሚስትሪ ማሽን ለማስገባት ሙሉ ዝግጅት የተጠናቀቀበት አግባብ መኖሩንም አንስተው ከተማ አስተዳደር ተቋሙን ለመደገፍ ከሌላ ጊዜ በተሻለ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ከማዕጤመ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ህብረተሰቡ በጉብሬ ሆስፒታል መጠቀም የሚችልበት ሁኔታ መፈጠሩን አንስተው አሁንም ማህበረሰቡ የማዕጤመ ተጠቃሚ በመሆን በህመሙ ልክ ሳይሆን በአቅሙ ልክ መታከም የሚችልበት ሁኔት የተፈጠረበት አግባብ በመኖሩ ተጠቃሚ መሆን መቻል አለበት ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ ታለደ በቀለ እንደተናገሩት ወልቂጤ ጤና ጣቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለማድረግ ሁላችንም የድርሻችንን ወስደን ልንሰራ ይገባል።
ህብረተሰባችን የሚያነሳው ልማትና እድገት ለማሳለጥ ጤና የሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ ጤናውን የተጠበቀ ማህበረሰቡ ለመፍጠር ቅድመ በሽታ የመከላከል ስራ ላይ ትኩረት በመስጠት የአካባቢ ፅዳትና ውበት ከጤና ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት ማህበረሰቡም ሀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ጠቁመዋል ።
በማህበረሰባችን ከፍተኛ መዘናጋት የሚስተዋለው የኤችአይቪ ስርጭት፣አጎበር በአግባቡ አለመጠበቅ ፣የማዕጤመ አገልግሎት ተጠቃሚ አለመሆን ትኩረት ልንሰጠው ይገባል ብለዋል።
በየትኛው የስራ ዘርፍ ማህበረሰብና ህዝብን ማገልገል መቻል መመረጥ በመሆኑ የህዝባችን ጤና፣እድገትና ለውጥ እንዲሁም ብልፅግና ሊያረጋግጡ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ እንደ ሀገር በወረደው የኮሪደር ልማት ላይ አሻራ በማሳረፍ የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

የወልቂጤ ጤና ጣቢያ ሃላፊ አቶ በድሉ ሳህሉ እንደተናገሩት ተቋሙ ለከተማችንን ማህበረሰብ በጤናው ዘርፍ እየሰጠው ያለውን አገልግሎት ለማሳደግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና አጋዥ አካላትን አሳትፈን የተሻለ ስራ ለመስራት አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
በእናቶችና በህፃናት አገልግሎት ፣ ተላላፊ የሆኑና ያልሆኑ በሽታዎች ቅድመ መከላከል ፣ወባ በሽታ ቅድመ የመከላከል ስራ በግማሽ አመቱ መልካም አፈፃፀም የተመዘገበበት እንደነበረ አንስተዋል።
ተቋሙ ለከተማው ማህበረሰብ አልፎም አጠቃላይ ለአጎራባች ወረዳዎች በተለያየ መልኩ ባለው አቅምና እውቀት ድጋፍ እያደረገበት አግባብ መኖሩን አንስተው በሚፈለገው ልክ አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ የግብዓት እጥረት እንዳለም አመላክተዋል።
የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለማድረግ የህበረተሰብና የመንግስት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን አንስተው ከተማ አስተዳደሩ ኬሚስትሪ ማሽንና ለማስገባ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ቀጣይ ተቋሙ የሁሉም ማህበረሰብ እና ባለድርሻ አካላት ድጋፍና ክትትል ሊሰሩ የታቀዱ ተግባራት ኬሚስትሪ ማሽን በመረከብ አገልግሎት ማስጀመር ፣የተኝቶ ህክምና ስራ ማጠናከር፣በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ማድረግ ፣ግቢውንና አካባቢውን አረንጉዴ፣ጽዱናማራኪ እንዲሆን ማድረግ፣የመነጽር (Eye Glass Workshop) አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ማስጀመር፣ተቋሙን ሆስፒታል ለማድረግ የሚያግዙ ተግባራትን መስራት እንዲሁም የእናቶች ፋርማሲ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ማስጀመር የሚጠበቁብን ዋና ዋና ተግባራት ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።
በውይይት መድረኩ የተሳተፉ የማህበረሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት ተቋሙ በየጊዜ መሻሻሎች እያሳየበት አግባብ መኖሩን ጠቁመው መስጠት የሚገባው አገልግሎት መስጠት እንዲችል ለማስቻል የሁሉም ድጋፍና ክትትል ሊደረግ ይገባል ብለዋል።
ተቋሙ ወደ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች በማሳለጥ ባላቸው አቅም በገንዘብ ሆነ በጉልበት አጋዥነታቸውን ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
በሽታን ቀድሞ ከመከላከል አንፃር ጤና ተቋሙ በርካታ ተግባራት ሲያከናውን መቆየቱን አንስተው የባለሙያዎች ከስነምግባር ጋር ተያይዞ ለሌላ ጤና ተቋም ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

