የጉራጌ ዞን ባህል ኪነት ቡድን ከክልሉ ካሉ የባህል ኪነት ቡድኖችም አሸናፊ ሆነ።

የባህል ኪነት ቡድኑ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄዳ በነበረው የ3ኛው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስፖርት ሻምፒዮናና የባህል ስፖርት ፌስቲቫል ላይ ስራዎቹን አቅርቦ ነው አሸናፊ የሆነው።

የካቲት 19/2018 (ወልቂጤ)

የጉራጌ ዞን ባህል ኪነት ቡድን ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ማህበረሰቡን እያዝናኑ ከማስተማር ጎን ለጎን የጉራጌን ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ባህል፣ እሴቶችን መሠረት በማድረግ በጎ ማህበራዊና ባህላዊ መስተጋብራችን በማጎልበት የጉራጌን ባህል ኪነጥበብን ያስተዋውቃል።

በጉራጌ ብሄረሰብ ውስጥ ያሉ እየተረሱ የመጡ ባህላዊና ትውፊታዊ ክዋኔዎችን በማጥናት፣ በመሰነድ ለህዝብ የማስተዋወቅ እንዲታወሱና እንዲበለጽጉ ያደርጋል።

የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ የኪነት ቡድን አስተባባሪ አቶ አስመላሽ ገብሬ እንዳሉት መሰል ውድድሮች መከናወናቸውን ብሄር ብሄረሰቦች ባህላቸው እና ታሪካቸው እንዲታወቅ እና ኪነ ጥበብ ዘርፉ እንዲያድግ እድል ይፈጥራል።

ኪነት ቡድኑ ባህላዊ ሙዚቃዎችን፣ ግጥምና ዜማ በማዘጋጀት፣ በባህላዊ ውዝዋዜ፣ በትያአትርና በሥነጹሁፍ በማቅረብ ከማዝናናት አልፎ አስተማሪ ስራዎችን ለታዳሚው ያቀርባል።

እነዚህም በተለያዩ መንግስታዊ ዝግጅቶች፣ህዝባዊ መድረኮች፣የመሰረተ ልማት ምርቃቶች፣ ልዩ ልዩ በዓላት ላይ በመገኘት የህዝቦችን የእርስ በርስ ግንኙት በሚያጠናክሩና በባህላዊና ማህበራዊ እሴቶችን በሚያጎለበት መልኩ ለህዝቡ የማቅረብ ስራ ይሰራል።

ስለ ሥራ ባህል፣ ስለ አብሮነት፣ ስለ ቁጠባ፣ ስለ ሠርግ ሥርዓቱ፣ ስለ ሴቶች (አንትሮሽት) ስለ ልጆች አስተዳደግ፣ ስለ ሽምግልና ሥርዓቱ በሌሎችም ኪነ ጥበባዊ በሆነ መንገድ ይሰራል።

ይህንን ልምድና አቅም በመጠቀም ዘንድሮ ወልቂጤ ከተማ ላይ እየተካሄደ ያለው የክልሉ ልዩ ልዩ የስፖርት ውድድርና የባህል ፌስቲቫል ጨዋታ የውድድር ስራውን በማቅረብ በክልሉ ካሉ የየዞንና የልዩ ወረዳዎች የኪነት ቡድኖችን በማሸነፍ አንደኛ በመሆን አጠናቋል።

አንትሮሽት (የእናቶች) ቀን የጉራጌ ሰርግ፣ባህላዊ ዘፈኖችና ውዝዋዜዎች ፣ጉራጌን በማስተዋወቅ፣የምግብ አዘገጃጀት እና ሌሎችም በማቅረብ በተመልካቹ አግራሞትንና አድናቆትን ተችሮታል።

በውዝዋዜ፣በቲያትርና በድራማዊ ክዋኔዎችን ነው የኪነት ቡድኑ ስራዎቹን ያቀረበው።

መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት የጉራጌ ዞን ባህል ኪነት ቡድን በልምድና በእውቀት የዳበሩ ነባር አባላቱን ይዞ አዳዲስ ተተኪ ወጣቶችን በአዲስ መልክ ማደራጀቱ ጠቁመዋል።

አቶ አስመላሽ አክለውም የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እንዲያገኙ፣ ባህላዊ አልባሳትና ቁሳቁስ በማሟላት የኪነጥበብ ዘርፉ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ በፖለቲካዊ ዘርፍ የጎላ ሚናውን እንዲጫወት አድርጓል ሲል የጉራጌ ዞን ኮሙዩኒኬሽን ዘግቦታል።

Previous ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በርካታ ሥራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ስራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽህፈት ቤት ገለፀ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo