የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ፅህፈት ቤት የበጋ በጎ ፍቃድ መዝጊያና የክረምት መክፈቻ በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጲያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል በጉብሬ ክፍለ ከተማ የአንድ የአእምሮ ታማሚ እናት ቤት በወጣት ባለሀብት ግንባታ የማስጀመርና በአባ ፍራንሷ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ ዉስጥ የችግኝ ተከላ ተካሄዷል።

ሰኔ 21/10/2016ዓ.ም [ወልቂጤ]

በበጋ ወራት በሁሉም ዘርፎች የተመዘገበዉ የበጎ ፍቃድ ስራ አገልግሎት በክረምቱ ወቅት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አስታወቀ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ፅህፈት ቤት የበጋ በጎ ፍቃድ መዝጊያና የክረምት መክፈቻ በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጲያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል በጉብሬ ክፍለ ከተማ የአንድ የአእምሮ ታማሚ እናት ቤት በወጣት ባለሀብት ግንባታ የማስጀመርና በአባ ፍራንሷ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ ዉስጥ የችግኝ ተከላ ተካሄዷል።

የ2015 ዓ.ም በበጋ ወራት በተሰሩ የተለያዩ የልማት ስራዎች ከመንግስት ይወጣ የነበረዉ በርካታ ገንዘብ ማዳን እንደተቻለም ተገልጿል።

በጎ በመስራትና በመተግበር የማህበረሰቡና የተለያዩ ችግር ያለባቸዉ ወገኖች መታደግ እንደሆነም ይታወቃል።

የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት ወጣቶች ያለምንም ክፍያ በፈቃደኝነት እና በጎነት ላይ ተመስርተው እውቀት ጉልበትና ጊዜያቸውን በማህበረሰባቸው ውስጥ የሚታዩ ችግሮችን ለማቃለል በተለያዩ መስኮች ተሰማርተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛል።

የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታዉ እንዳሉት በዘንድሮ የክረምት ወራት ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ የተለያዩ የልማት ስራዎች በዘላቂነት የሚከናወን እንደሆነም አመላክተዉ በዚህም በተቀደሰዉ ተግባር እንደወትሮም በርካታ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶችና ባለሀብቶች የድርሻቸዉን ሊወጡ እንደሚገባም ተናግረዋል።

በጎ ተግባር ከመስራታችን በፊት በጎነት ከራሳችን በመጀመር የወጣት ስብዕና ግንባታ ላይ ወጥ በሆነ መንገድ ሰርተን

ወጣቱን በአደረጃጀት አጠናክረን መሄድ አለብን ብለዋል።

በበጋ ወራት በሁሉም ዘርፎች የተመዘገበዉ የበጎ ፍቃድ ስራ አገልግሎት በክረምቱ ወቅት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አመላክተዋል።

በሀገራቸው እየተካሄደ ባለው የልማትና የለውጥ ሂደት ውስጥ የወጣቶች ተሳትፎአቸውን በተግባር የሚያረጋግጡበትና ከማህበረሰቡ ጠቃሚ እሴቶችን ልምዶችና ተሞክሮዎችን የሚቀስሙበትና የመንፈስ እርካታን የሚያገኙበት መሆኑን አቶ ይድነቃቸው ፍቃዱ የወልቂጤ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት የወጣቶች ዘርፍ ሀላፊ ገልፀዋል ።

በመድረኩ የተገኙ ባለድርሻ አካላት በሰጡት አስተያየ የወጣቶች ማዘውተሪያና መዝናኛ ባለሀብቱን በማስተባበር አሰርተን ወጣቱን አልባሌ ቦታ እንዳይወድቅ በመታደግ እውቀቱን፣ ጉልበቱንና ጊዜውን ለማህበረሰቡ እንዲጠቅም ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ከቀይ መስቀል ጋር ያለው ነገር ብዙ ወጪ ቀናሽ ስለሆነ ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት ይኖርበታል ሲሉ አሳስበዋል።

በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከጤና ደም ልገሳና በትምህርት ተቋም የተማሪዎችን ውጤት ለመቀየር የሚሰራው ልዩ ተግባር ሲሆን ይህም ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት እንደሚገባ አቶ ሞሳ አብራር የወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ስፖርት ዘርፍ ሀላፊ ገልፀዋል።

አያይዘውም ጧሪ ቀባሪ የሌላቸውን አቅመ ደካማ አረጋዊያን ለመርዳት የጉብሬ ሆስፒታል የጀመረ ሲሆን ወጣት በጎ ፈቃደኛውም ይህን በማገዝ አጠናክሮ መስራት ይኖርበታል ብለዋል።

አጠቃላይ ከመድረኩ የተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ለቀጣይ ስራ የሚያግዝ ግብአት መሆኑን ገልፀው ከተማችን ውስጥ ልማት ላይ ብቻ ያተኮረ ወጣት ስላለን ከክረምት በጎ ፈቃድ ሌላ ፍላጎት የሌላቸዉ ህብረተሰቡ ሲጠቀም እኔም ተጠቀምኩ ብለው የሚያስቡ ልማታዊ ወጣት አካተን መስራት አለብን ሲሉም አቶ እንዳለ ስጦታው ተናግረዋል።

ከፊታችን የሚገኘው ክረምት ወጣቱን ህብረተሰቡን በማንቃት በለውጥ ጉዞ ውስጥ እግር ጎታች ሳንሆን ለለውጥ

የበኩላችንን አሻራ የምናሳርፍ ሆነን ልንሰራ ይገባል አክለዋል።

በጉብሬ ክፍለ ከተማ በአንዲት ደሳሳ ቤት የምትገኝ የአእምሮ ህመምተኛ የአንድ ልጅ እናት የሆነች ሴት ቤት ፈርሶ በአዲስ ተገንብቶ ሙሉ የህክምና ድጋፍ በበጎ ፈቃዱ እንደሚሰሩ ተመላክቷል።

በዛሬ ዕለት ወጣቱ ባለሀብት አቡበክር ፈድሉ የወልቂጤ ከተማ አመራሮችና ወጣቶች በተገኙበት የዚች የአእምሮ ታማሚ እናታችን ቤት አፍርሶ በአዲስ መልክ ለመገንባት የማፍረስ ስራ መጀመሩም ታዉቋል።

በጉብሬ አባ ፍራንሷ 2 ኞ ደረጃ ትምህርት ቤት የክረምት ማስጀመሪያ ኘሮግራም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ በማድረግ መድረኩ ተጠናቋል።

Previous የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የገቢ አቅም ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo