የብልጽግና ፖርቲ ስራ አስፈጻሚና የኢፌድሪ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በወልቂጤ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው

የካቲት 16/2017 (ወልቂጤ)

የብልጽግና ፖርቲ ስራ አስፈጻሚና የኢፌድሪ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በወልቂጤ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው

የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ፣የኢፌድሪ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ፣ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የቤኒሻንጉል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ በወልቂጤ ከተማ እየተከናወነ ያለ የልማት ስራዎች ጉብኝት እያደረጉ ነው።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንዲሁም በከተማው በግል የኢንቬስትመንት የተሰማሩ ባለሀብቶችን የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ከወረቀት ነጻ በሆነ መልኩ ለተገልጋዩ ህብረተሰብ እየሰጠ ያለውን አገልግሎት ሚኒስትሯ እና በእርሳቸው የተመራው ልኡክ ጉብኝት አድርገዋል።

በወልቂጤ ከተማ እልፉ ባልትና እንዲሁም የወልቂጤ ከተማ ዘመናዊ የቄራ ግንባታ ተጎብኝቷል።

ሚኒስትሯ እና በእርሳቸው የተመራው ልኡክ በነገዉ እለት የሚካሄደዉን ሀገር አቀፍ ህዝባዊ ዉይይት ለመምራት ነው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማ የተገኙት።

በመርሐ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ይሁን አሰፋ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየው ገ/መስቀል ፣ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እና ሌሎች የፌዴራ የክልል የዞንና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

Previous የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ከትምህርት ጽህፈት ቤት በመተባበር “የሳይንስና ቴክኖሎጂ ለሁለንተናዊ ብልጽግና ” በሚል በትምህርት ቤቶች ለሚገኙ ለሳይንስ ክበባት ተጠሪዎች ናየፈጠራ ባለቤቶች ስልጠና ተሰጠ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo