የማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገትና ብልፅግና ለማረጋገጥ ያላቸው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።

ግንቦት 23/2016ዓ.ም [ወልቂጤ]

በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት የሶስተኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀምም ግምገማ አካሄዱ።

በውይይት መድረኩ የተሰሩ የሶስተኛ ሩብ ዓመት ተግባራት ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በቀጣይ በጀት ዓመት ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠል የታዩ ጉድለቶችን በመሙላት እንደ ከተማ የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚገባው ተገልጿል ።

ለአንድ ሀገር እድገትና ለውጥ ትምህርት ትልቁን ድርሻ የሚይዝ መሆኑ ተውቆ በትምህርት ቤቶች መሰረተ ልማት በማሟላት እና ያሉትን በማሻሻል የተማሪ ውጤት ለማሳደግ የትምሀርት ውስጣዊ ብቃትና ተገቢነት ማሻሻል ላይ የሁሉም ባለድርሻ አካል ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ከመድረኩ ተገልጿል ።

ሀገር ተረካቢ ዜጋ ለመፍጠር በትምህርት ዘርፍ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ አፅንኦት በመስጠት በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባም ከመድረኩ ተብራርቷል ።

ከከተማው ፅዳትና ጤና አጠባበቅ ጋር ተያይዞ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና እንዲሁም የመኖሪያ አካባቢዎች ላይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተጠቁሟል ።

እንዲሁም ተቋማት አገልግሎት አሰጣጣቸው ለማዘመን የተጀመሩ ስራዎች በማጠናከር ወቅቱና ጊዜው የሚመጥን የቴክኖሎጂ ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የህበረተሰቡ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባው ተመልክቷል ።

አመራሩና ሰራተኛው በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ አመለካከቱን በመለወጥና ብቃቱን በማሳደግ ህብረተሰቡን በቅንነት እና በታማኝነት የሚያገለግል ጠንካራና ውጤታማ ሲቪል በርቫንት ማብቃት እንደሚገባም ከመድረኩ ተጠቁሟል ።

የመንግስት እና የህዝብ ቀጥታ ግንኙነት በማጠናከር ሁለንተናዊ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ቅድሚያ በመስጠት የህዝብን ፍላጎት የዳሰሰ ጥናት ማድረግ እንደሚገባ ተመላክቷል።

በመንግሥት የሚሰሩ የልማት ስራዎችን መረጃ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ አማራጮችን ተጠቅሞ ለማህበረሰቡ ግልፀኝነት የተሞላበት መረጃ መስጠት እንደሚገባ ተገልጿል ።

በመድረኩ ተሳታፊዎች ከተነሱ አስተያየቶች መካከል ትምህርት ቤቶች ትውልድ የሚቀረፅበት እንደመሆኑ መጠን ምቹ የመማሪያ ስፍራ መፍጠርና ከአልባሌ ሱስ ደባል የመሆን ዕድላቸው ልንታደገው ይገባል ብለዋል።

ከተማችን ከፍተኛ የሆነ የቱሪስት ፍሰት ያላት መሆኑን ገልፀው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ቱሪስቱን በሚፈለገው ልክ ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን አለመሆናቸው ድጋፍ ክትትል ሊደረግ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የከተማው ስፖርት ህዝባዊነቱን ለማረጋገጥ አዎንታዊ አመለካከትን ለማዳበር ሀሳብን በአወንታዊ መንገድ በመግለፅ ለህብረተሰቡ የጋራ ውይይት እንደሚያስፈልግ አስተያየት ሰጥተዋል።

በተለያዩ ጊዜያት በህዝቡ እየተነሳ ያለው ከዚህ በፊት በተለያየ ምክንያት ተጀማምረው ያልተጠናቀቁ መሠረተ ልማት የተቆፍፈሩ ቦታዎች ዝናብ በዘነበ ቁጥር በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ የጤና ችግር እንደሚያደርስ ጠቁመው የሚመለከተው አካል ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም ለተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የተገኙ የተቋማት ሀላፊዎች እና የማኔጅመንት አካላት ሰፊ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ያልተከናወኑ ተግባራት እንደ ግብዓት ተወስደው ሊሰራባቸው እንደሚገባ በመጠቆም መድረኩ ተጠናቋል ።

Previous ግንቦት21/2016ዓ.ም

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo