ሐምሌ 26/2O17 ዓ/ም [ወልቂጤ]
“ጽዱ ከተማን ለመፍጠር በየሳምንቱ የተጠናከረ የጽዳት ዘመቻ ስራ እያከናወንን እንገኛለን፦ አቶ ሙራድ ከድር የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ
ኬሮድ 5ኛ ዙር የጎዳና ላይ ሩጫ “ኑ ለኢትዮጵያ ሰላም እንሩጥ” በሚል መሪ ቃል ለሚካሄደው ሩጫ አከባቢውን ጽዱ ለማድረግ ህብረተሰቡን ያሳተፈ ሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻ በወልቂጤ ከተማ ተካሄዷል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር በዚህ ወቅት እንዳሉት ጽዱ ከተማን ለመፍጠር በየሳምንቱ የተጠናከረ የጽዳት ዘመቻ ስራ እያከናወንን እንገኛለን።
በከተማው ሁሉን ያሳተፈ የአካባቢ የጽዳት ስራ መስራት እንዲሁም ቆሻሻን የሚጸየፍ ማህበረሰብ መፍጠር እጅግ ወሳኝ ነው ያሉት ከንቲባው ዛሬ በወልቂጤ ከተማ እየተከናወነ የለው የጽዳት ስራውን ልዩ የሚያደርገው የሩጫ ዋዜማ ላይ በመሆን ነገ ወደ ከተማችን የሚመጡ እንግዶች እንደነ፣ አትሌት ሰለሞን በረጋ፣ አትሌት ተሰማ አብሽሮ እንድሁም ሌሎችንም እንግዶችን ለመቀበል ተሳቢ ያደረገ የጽዳት ዘመቻ እየተከናወነ መሆኑን አብራርተዋል።
በእድሜዋ ልክ ያለማችው ወልቂጤ ከተማ ወደ እድገት ጎዳና ለማሻገር መንግስትና ማህበረሰቡ ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑንም ከንቲባው ገልፀዋል።
የከተማው ሰላምና ደህንነት ይበልጥ አስተማማኝ እንዲሆን ከነዋሪው፣ ከወጣቱ፣ ከሃይማኖት አባቶችና ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
በከተማው የተጀመረው የኮሪደር ግንባታ ልማት ስራ እየተፋጠነ መሆኑን ገልፀው ሌሎች የውስጥ ለውስጥ መንገድና የመሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወነ መሆኑንም አክለዋል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የረዥም ርቀት አሰልጣኝ ረዳት ኮሚሽነር ሁሴን ሽሞ በበኩላቸው ከዚህ በፊት በከተማው በተካሄደው በኬሮድ ሩጫ ለሁለተኛ ጊዜ መምጣታቸው ገልፀው ከተማዋ በአሁኑ ሰዓት በለውጥ ጎዳና ላይ ትገኛለች ብለዋል።
የጀግኖች አትሌቶች መፍለቂያ በሆነችው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማ ላይ የታላቁ የኬሮድ ሩጫን ዝግጅት በማስመልከት በፅዳት ዘመቻና በችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ በመሳተፋቸው እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ከተማ አስተዳደሩ ልማቱን ለማሳለጥ ከአመራሩ፣ ከባለሃብቶችና ከነዋሪው ጋር በቅንጅት እየተሰራ ያለው ተግባር ለሌሎች ከተሞች ተምሳሌት ሊሆን የሚችል ስራ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
ማህበረሰቡ ስራ ወዳድና እንግዳ ተቀባይ መሆኑ በከተማው ተዘዋውረው እንቅስቃሴ ባደረጉበት ወቅት መመልከታቸውን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ ይህን አኩሪ ባህል የሆነውን እሴት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አሳስበዋል።

ኮማንደር አትሌት ሰለሞን ባረጋ በበኩሉ የወልቂጤ ከተማ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለውጥ እያሳየች መሆኑ እጅግ የሚደነቅ ተግባር መሆኑን ገልጾ ለኬሮድ 5ኛ ዙር የጎዳና ላይ ሩጫ ለመሳተፍ ወደ ወልቂጤ በመምጣቱ ደስተኛ እንደሆነ ተናግረዋል።
በተለይም ለነገ ሩጫ ለተመልካቾች ከተማዋ ጽዱ ለማድረግ እየተከናወነ የማገኘው የጽዳት ስራ የሚበረታታ መሆኑን ያስታወሰው ኮማንደር አትሌት ሰለሞን ባረጋ ይህ ተግባር በሌላም ጊዜ መጠናከር እንደለበት አሳስቧል።
በጽዳት ዘመቻ እና በችግኝ ተከላው ላይ የተሳተፉ የከተማው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት በየሳምንቱ በሚካሄደው የጽዳት ዘመቻ ስራ እየተሳተፉ መሆናቸውን ጠቁመው በተለይ በነገው እለት በሚካሄደው ታላቁ የኬሮድ ሩጫ ፕሮግራም ዋዜማው ላይ መሆኑ ይበልጥ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

