ለረጅም አመታት ግንባታቸው ሲጓተት የነበሩ የልማት ፕሮጀክቶችን በማስቀጠል የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትሯ በአብነት ጠቅሰዋል።
በክልሉ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ውጤታማ ናቸው – ጫልቱ ሳኒ የኢፌድሪ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር
(ሆሳዕና፣የካቲት 16/2017) በኢፌድሪ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር በወ /ሮ ጫልቱ ሳኒ የተመራ ልኡክ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝቷል

የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወ /ሮ ጫልቱ ሳኒ በጉራጌ ዞን ልዩ ልዩ የልማት ስራዎችን በጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት በክልሉ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ውጤታማ ናቸው ብለዋል።
በክልሉ በመንግስት እና በግል የኢንቬስትመንት ልማት ስራዎች ላይ የታየው አበረታች ውጤት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።
ለኢትዮጵያ ከተሞች የትንሳኤ ዘመን ነው ያሉት ሚኒስትሯ
ከተሞቻችን አምራች፣የፈጠራ ማዕከል እንዲሁም የብልጽግና ማሳያ እንዲሆኑ የተጀመረው ጥረት ውጤታማ ስለመሆኑም አመላክተዋል ።
ለረጅም አመታት ግንባታቸው ሲጓተት የነበሩ የልማት ፕሮጀክቶችን በማስቀጠል የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትሯ በአብነት ጠቅሰዋል።

በከተሞች የማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት ለማዘመን የተጀመሩ ስራዎች መሻሻል ማሳየታቸውንም ጠቅሰዋል።
የመንገድ መሠረተ ልማት ስራ ማስፋፋት፣ ጽዱ ከተማ እና አረንጓዴ ልማት ስራን ማጠናከር እንደሚገባም አስረድተዋል።
በከተሞች የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት፣የውስጥ ለውስጥ መንገድ እና ተዛማጅ የከተማ ልማት ስራ ላይ የተጀመሩ ተግባራትን ቀጣይነት ማረጋገጥ እንደሚገባም ሚኒስትሯ አብራርተዋል።

ምልከታ ባደረጉበት የወልቂጤ ከተማ የሌማት ትሩፋት፣የስራ እድል መፍጠር የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች፣እያደገ የመጣውን የግብርና ልማት ስራን ወደ ኢንዳስትሪ ማሸጋገር የሚያስችሉ ተቋማትን ማየት መቻላቸውን ጠቅሰዋል።
በክልሉ በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የላቀ አበርክት ማድረግ የሚችሉ በትን እድል ተፈጥሯል ያሉት ሚኒስትሯ በጉራጌ ዞን የአቶ ዳኜ ዳባን የእርሻ ልማት በአብነት ጠቅሰዋል።
የግብርና ኢንቬስትመንትቱ ለወጣቶች የስራ እድል የሚፈጠርበት፣ የኑሮ ውድነት የሚረጋጋበት፣ኤክስፖርት አቅምን በማሳደግ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ የሚገኝበት ዘርፍ መሆኑንም ሚኒስትሯ አስረድተዋል።
በወልቂጤ ከተማ የተመሰረተው እልፉ ባልትና ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል ከመፍጠር ባለፈ የጠንካራ እንስቶች አብነት መሆኑንም ሚኒስትሯ አስረድተዋል።
በልማት ስራ ጉብኝት በመርሐ ግብሩ የቤኒሻንጉል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ፣የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ይሁን አሰፋ፣የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

