
ህዳር 19/2017ዓ.ም(ወልቂጤ)
የወልቂጤ ከተማ እድገት ለማፋጠን ከመሬት ሀብትና ከህንፃ ግንባታ ስራዎች ጋር በተያያዘ ከከተማው ባለሀብት ጋር ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
የውይይት መድረኩን ያስጀመሩት የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እንደተናገሩት ባለሀብቶች ያላቸው የገንዘብ አቅም፣ ጊዜና ጉልበት ሳይሰስቱ ለነገው ትውልድና ለከተማዋ እድገት ማፋጠን ላይ ማዋል ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ገልፀው።

ከተማችን ከህንፃ ስራና ከገፅታ ሁኔታ አንፃር ከዚህ በፊትም ክፍተቶ የነበሩ መሆኑን አመላክተው በቅርብ ዓመታት አንዳንድ ግንባር ቀደም ባለሀብቶች የሚታይ ስራዎች እየሰሩም እንደሚገኙ ገልፀዋል።
የውይይቱ አላማ ከተማዋ እድሜዋን በሚመጥን የእድገት ደረጃ ላይ አለመገኘቷ ሊያስቆጭ እንደሚገባ የገለፁት ከንቲባው ባለሀብቶች ከመንግስት ጋር በመቀናጀት ለከተማዋ እድገት ትኩረት በመስጠት የግንባታ ስራው እንቅስቃሴ የማስጀመር ስራ ያለመ መሆኑ ጠቁመዋል።


