የካቲት 17/2018ዓ.ም[ወልቂጤ]
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሥራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት በ2018ዓመተ ምህረት በ7 ወር የተከናወኑ ተግባራትን የተቋሙ ኃላፊ አቅርበው አስገምግመዋል።
በመድረኩም የአሰራር ማዕቀፎች፣የሥራ ዕድል ፈጠራ አዲስ አስተሳሰብ፣የብድር አስመላሽ ግብረ ሃይል ተግባርና ኃላፊነት፣የሼድ አቅርቦትና አስተዳደር እንዲሁም በቀጣይ በግብረ ኃይሉ የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በምክር ቤቱ ውይይት ላይ የተገኙት የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እንደገለፁት ሥራ ዕድል ፈጠራ ኢኮኖሚና ፖለቲካነው ስለሆነም ያሉንን ፀጋዎች በመጠቀም ለወጣቱ ስራ ዕድል በመፍጠር የኢኮኖሚ ችግሩን እንዲፈታ ልንሰራ ይገባል ሲሉ ጠቁመው
ስራ ዕድል ስንፈጥር ኢኮኖሚ እናሳድጋለን የብልፅግና መንግሥት ቁልፍ ተግባር ብሎ ከያዛቸው መካከል የሥራ እድል ፈጠራ እናሳካለን ሲሉም አስገንዝበዋል።
የህዝብና ወጣት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከልየታው እስከ ሥራ እድል ፈጠራው ድረስ የዜጎች እኩል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት እንዲሆኑ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር በፍትሀዊነት መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል።

የወልቂጤ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ታደለ በቀለ እንዳሉት መድረኩ ለቀጣይ ስራዎች መነሳሳት የሚሆን በመሆኑ ከዚህ በፊት የነበረውን የተሳሳተ አመለካከት ተቀርፈው በርካታ ስራዎች እየተሰራ ያለበት ሁኔታ መኖሩን ጠቁመው
ክህሎትን በማዳበርና ኃላፊነትን በመውሰድ የተወሰደው ብድር በማስመለስና አላግባብ ተይዘው ያሉ ሼድና የግንባታ ቦታዎች ያሉበትን ሁኔታ በመከታተል በተገቢው ለወጣቱ የስራ እድል መፍጠር ይገባልም ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ተካልኝ አቡሌ እንደገለፁት በ7ወር አፈጻጸም ብድር ስርጭና አመላለስ ዙሪያ፣የቁጠባ ሞቢላይዜሽን ተግባራት ሼድ አቅርቦትና አስተዳደር ላይ ከስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤትና ከብድር አስመላሽ ግብረ ሃይል ጋር ለመወያየት ይህ መድረክ መዘጋጀቱን ገልፀው

የስራ ዕድል ፈጠራ ከዳቦ በላይ ሃብት መፍጠር ገቢ ምርቶች በመተካት ወጪ ምርቶች ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ዘላቂና አስተማማኝ ሥራ በመፍጠር የሥራ ባህል ማሳደግ ተገቢ ነው ብለዋል።
በቀጣይ ወራት የግል ዘርፍን በማበረታታት፣ ከባንኮች እና ከማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር የሥራ ፈጠራን እንዲጠናከር እንደሚሰራ ተገልጿል።

የሼድና የመሸጫ ቦታዎች አቅርቦት፣ የስራ ፈላጊዎች ልየታና መረጃ አያያዝ፣ ቁጠባ፣ብድር አመላለስና ስርጭት፣ የማሽነሪና የመሰረተ ልማት አቅርቦት፣ የገበያ ትስስር መፍጠር እና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከቤቱ ሀሳብ አስተያየት ተነስተው ከመድረኩ ሰፊ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።

