
ባለፉት ስድስት ወራት በልማትና በመልካም አስተዳደር ስራዎች አመራሩ ከህብረተሰቡ፣ ከባለሀብቱና ከግል ዘርፉ ጋር በመሆን ያስገኛቸው ውጤቶች አጠናክሮ ሊያስቀጥል እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ!!
ጥር 28/2018(ወልቂጤ)
በዞኑ በ2018 በጀት ዓመት በ6 ወሩ የተሰሩ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል።
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ከለውጡ አመታት ጀምሮ በዞኑ የማህበረሰቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች የተፈቱበት እንደነበር አስታውሰዋል።
ለአብነትም በዘንድሮ አመት ወደ ስራ የገባው የአማርድ አዳሪ ትምህርት ቤት የህዝቡ የዘመናት ጥያቄ የነበረ ሲሆን በአሁን ሰአት ማህበረሰቡ በሚመጥን መልኩ የመማር ማስተማር ስራ እያከናወነ ይገኛል።
አክለውም በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ማህበረሰቡን በማሳተፍ ከ1 ቢለየን ብር በላይ የትምህርት ቁሳቁስ በማሟላት ሞዴል ስራ ተሰርቷል።
በባህልና ቋንቋም የማህበረሰቡ እሴቶች ጎልተው እንዲወጡ የተሰራ ሲሆን ጀፎረን የማልማትና ከገጠር ኮሪደር ልማት ጋር ማስተሳሰር ተችሏል ነው ያሉት።
የጉራጊኛ ቋንቋ ለትምህርት፣ለስራና ለሚዲያ እንዲውል መደረጉ የገለጹት አቶ ላጫ የጉራጌ የማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጣበያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስራ ለማስጀመር ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በግብርና ዘርፉም በሌማት ትሩፋት፣በቡናና ቅመማ ቅመም፣በእንሰት ልማት፣ባህርዛፍ አንስቶ በሰብል በመሸፈን ጥሩ ስራዎች ቢሰሩም ገና ብዙ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
የጉራጌ ማህበረሰብ የሚመጠን ስራ ለመስራትና በዞኑ ብልጽግና ለማረጋገጥ አመራሩ በቁርጠኝነት፣በአንድነት እሳቤ፣በአስተሳሰብ ለውጥ ሊሰራ ይገባል።
የሀይማኖት አክራሪነት የሀገርም ሆነ የዞኑ ማህበረሰብ አንድነትና ሰላም የሚያናጋ በመሆኑ በዚህ ተግባር የሚሳተፉ አካላትን ከድርጊታቸው ማስቆም ያስፈልጋል ሲሉ አስታውቀዋል።
በለውጡ መንግስት በዞኑ የተረጋጋ አመራር መፈጠሩ ያመላከቱት አቶ ላጫ ይህንን አቅም በመጠቀም ብልሹ አሰራሮች ማረም፣የገቢ አሰባሰብ ማጠናከር ፣የተገኘው አንጻራዊ ሰላም ማስቀጠል፣ጽንፈኞችን ለይቶ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ መክረዋል።
ቀጣይ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፣ፍትሀዊና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን በትኩረት እንዲሰራ አስገንዝበዋል።
አቶ ላጫ አክለውም በዞኑ በቀጣይ ተጨማሪ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ለማከናወን አመራሩ ወቅቱን ተረድቶ ተልእኮውን በብቃት መፈጸም እንዳለበት መክረዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል እንዳሉት አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመፍጠር የአመራሩ ሚና ከፍተኛ ነው ብለው ዞናዊ አንድነት ይበልጥ ማጠናከር ያስፈልጋል።
በጉራጌ ዞን የፓርቲ ኢኒሼቲቮች ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር እንደ ሀገር ሞዴል ናቸው ያሉት አቶ አለማየሁ በቀጣይም ኢኒሼቲቮች በጥራት፣በፍጥነትና በብዛት ሰርቶ ማሳየት እንደሚገባ ተናግረዋል።
አክለውም የማህበረሰቡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የግብርና ዘርፉ ይበልጥ ማሳደግ እንደሚገባ አንስተው የግል፣የወል፣ የሀይማኖትና የመንግስት ተቋማት መሬቶች በአግባቡ ማረስ ያስፈልጋል።
አቶ አለማየሁ አክለውም የማህበረሰቡ ባህልና እሴት ይበልጥ ማጉላት እንደሚገባ ጠቁመው ይሁን እንጂ የማህበረሰቡ እሴት ያልሆኑ በሱስ የመጠመድ ድርጊቶች በአፋጣኝ ማረም ይጠበቃል።
መዋቅሮች በአፈጻጸም እንዲቀራረቡ በማድረግ፣ችግሮችን በአፋጣኝ በመፍታት ደሞክራሲን ማጽናት ያስፈልጋል ብለዋል።
ሚዲያን ለበጎ አላማ በመጠቀም የተሰሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች አጉልቶ በማውጣት የጽንፈኛ አክቲቪስቶች ድርጊት ማክሸፍ እንደሚገባ አቶ አለማየሁ ተናግረዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ የስራ ኃላፊዎች እንዳሉት በግማሽ ዓመቱ በዞኑ የተሰሩ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች አበረታች ናቸው።
ሆኖም ግን በቀጣይ ከዞኑ አቅምና ጸጋ እንዲሁም ከማህበረሰቡ ንቃተ ህሊና አንጻር ገና ብዙ መስራት ይገባል ነው ያሉት።
አመራሩ የህዝቡ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ተግባራት ላይ ማትኮር እንዳለበት ያነሱት ሀሳብ ሰጪዎቹ ከመዘናጋት ይልቅ መዘጋጀት እና ለጠንካራ ስራ ይበልጥ መትጋት ይጠበቅበታል ሲሉ ተናግረዋል።
ኢኒሼቲቮችን በላቀ ሁኔታ መፈጸም ፣የአካባቢ ሰላምና ጸጥታ ማረጋገጥ ፣አመራሩ የጋራ አንድነት መፍጠር ፣ብልሹ አሰራሮችን መከላከልና የአስተሳሰብ ለውጦች ማምጣት ከሁሉም ይጠበቃል።

ከዚህ በፊት የታዩ የህዝቡና የመንግስት አቅሞች ማቀናጀት ፣የልማት ጉድለቶች መሙላት፣የህብረተሰቡ ኢኮኖሚያ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ማድረግ ይኖርበታል ሲሉ አብራርተዋል።
#gurageZone government communication affairs

