በዞኑ የትምህርት መሰረተ ልማት በማሻሻል የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር ችግር ለመፍታት እየተሰራ ያለው ስራ በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

ጥር 17/2017 ዓ.ም

በዞኑ የትምህርት መሰረተ ልማት በማሻሻል የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር ችግር ለመፍታት እየተሰራ ያለው ስራ በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

በወረዳ በወንዝሬ ጎረት ቀበሌ ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በአማርድ ቡራት የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት፣ በአካባቢ ተወላጆች ማህበርና በመንግስት የተገነባው የቡራት አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።

የኢፌድሪ ህብረት ስራ ኮሚሽን ምክትልና የጌታ ወረዳ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ኮሚሽነር ሺሰማ ገብረስላሴ በምረቃው ተገኝተው እንዳሉት ጠንክሮ በመማር ከአካባቢ፣ ከሀገር አልፎ በአለም ደረጃ ተጽዕኖ መፍጠር እንደሚቻል ጠቁመው ለዚህም ትውልዱ በትምህርታቸው ጠንክረው እንዲማሩም አሳስበዋል።

የትምህርት ቤቱ ደረጃ ለማሻሻል የአማርድ የቀድሞ የቡራት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ህብረትና የአካባቢው ተወላጆችና መንግስት ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳደሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በበኩላቸው ባለፉት አመታት በሀገሪቱ ብሎም በዞኑ መንግስት ለትምህርት ልማት ዘርፍ የተለየ ትኩረት በመስጠት ትምህርት ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ በተሰሩ ስራዎች አመርቂ ውጤቶችን ተመዝግቧል ብለዋል።

በመሆኑም ትምህርት ለዜጎች ለማዳረስ ቢሰራም ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶች፣ ግብአቶችና ሌሎችም አስተዳደራዊ ችግሮችን ተዳምረው በተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ አለመቻሉን ገልጸዋል።

በዞኑ ያጋጠመው የተማሪዎች ውጤት ስብራት ችግር ለመፍታት ባለፉት አመታት በንቅናቄ ስራ ማህበረሰቡ፣ ባለሀብቶች፣ ምሁራንና አጋር ድርጅቶችና መንግስት በመተባበር ከ4 መቶ 93 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ የትምህርት መሰረተ ልማት ማሻሻል ተችሏል ነው ያሉት።

በዞኑ ከደረጃ በታች ከነበሩ ትምህርት ቤቶች መካከል የቡራት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንዱ እንደነበር አስታውሰው የአማርድ ቡራት የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት፣ በአካባቢው ተወላጆች፣ በመንግስት ትብብር መገንባቱን ገልጸዋል።

ማህበሩ የትምህርት ቤቶች መልሶ ግንባታና ግብአት በሟሟላትና በሌሎችም ልማቶች እያደረገው ያለው ድጋፍ አመስግነው በቀጣይም የዞኑ መንግስት የተጀመረው የትምህርት መሰረተ ልማት ማሻሻል ስራ ላይ ድጋፋቸው አጠናክረው እንዲያስቀጥሉም ጠይቀዋል።

የዞኑ መንግስት በትምህርት ልማት ስራ የጀመራቸው ስራዎችን በማጠናከር በቀጣይም ያጋጠመውን የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራ አስገንዝበዋል።

የጌታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በህሩ ኸይረዲን የቡራት አጠቃላይ ሁለተኛ ትምህርት ቤት በ2013 ዓ.ም ወደ መሰናዶ ቅድመ እውቅና ቢያገኝም ስታንዳርዳቸው የጠበቁ የመማሪያ ክፍሎች፣ የአስተዳደር ክፍሎች እጥረት፣ የቤተ መጽሀፍትና የቤተ ሙከራ ግንባታዎች እጥረት እንደነበሩበት አንስተዋል።

ይህ ችግር ለመፍታት የአማርድ የቀድሞ የቡራት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ህብረትና የአካባቢው ተወላጆችና መንግስት በመቀናጀት ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የተማሪ የመማሪያ ክፍሎች፣ የማጣቀሻ መጽሀፍቶች፣ የተማሪ መቀመጫ ዴስኮችና ላፕቶፖችን ማሟላት ተችላል ብለዋል።

ይህ ጅምር ስራ በቀጣይም በማጠናከር በትምህርትና በሌሎችም መሰረተ ልማቶች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

የወረዳው ምክትል አስተዳደሪና የትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሀብቱ ወልደኢየሱስ በወረዳው ቅድመ መደበኛ ጨምሮ ከ1ኛ እስከ12ኛ ክፍል 15 ሺህ 504 ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ሲሆን የቡራት አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንዱ ነው።

የአማርድ የቀድሞ የቡራት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ህብረትና አካባቢው ተወላጆች ማህበር ሰብሳቢ አቶ ዋቢ ታደሰ በ2012 ዓ.ም የተቋቋመው ማህበሩ በትምህርት፣ በጤና በአካባቢ ጥበቃና በመሰረተ ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል ነው ያሉት።

በዚህም በገጠር፣ በከተማ፣ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ተወላጆችና መንግስት በመተባበር 4 ደረጃቸውን የጠበቁ የመማሪያ ክፍሎች፣ 12 የመማሪያና የአስተዳደር ህንጻዎችና የቤተመጸሀፍት እድሳት፣ የላይብረሪ፣ የአይሲቲ፣ የላብራቶሪ ቁሳቁሶች፣ የተማሪዎች መግቢያና መውጫ በር ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

የአካባቢው ተወላጅ አቶ ገብሩ ምኑታ እንዳሉት የትምህርት ቤቱ ችግር ተቀርፎ ደረጃቸውን የጠበቁ የመማሪያ ክፍሎች ተገንብቶ በመመረቁ መደሰታቸውን ጠቅሰው ይህም የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር በማሻሻሉ ረገድ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

በትምህርት ቤቱ አግኝተን ያነጋገራቸው ተማሪዎች እንዳሉት ትምህርት ቤቱ ተገንብቶ በመመረቁ ደስተኛ መሆናቸውን ጠቅሰው በዚህም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ጠንክረው እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።

Previous የጉራጌ ማህበረሰብ የሴቶችን መብት አስቀድሞ የተረዳና ለሴቶች የእኩልነት ትግል ያረጋገጠ መሆኑ አንትሮሽት አንዱ ማሳያ መሆኑ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo