በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የዘመናት በህብረተሰቡ ጥያቄ ሲቀርብባቸው የነበሩ አከባቢዎች የመንገድ ከፈታ ሥራ በጉብሬ ዲስትሪክት በከተማ አሰተዳደሩ እና በህብረተሰቡ ጠንካራ ተሳትፎ የመንገድ ከፈታ ስራ ተከናወነ።

በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጉብርየ ክ/ከተማ በኤዋን ቀበሌ የጎቲየና ጭቋራ መንደሮች የህብረተሰቡን የዘመናት የመንገድ ከፈታ ጥያቄ ምላሽ አገኘ::

ጥር 17/2017 ዓ.ም [ወልቂጤ]

በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የዘመናት በህብረተሰቡ ጥያቄ ሲቀርብባቸው የነበሩ አከባቢዎች የመንገድ ከፈታ ሥራ በጉብሬ ዲስትሪክት በከተማ አሰተዳደሩ እና በህብረተሰቡ ጠንካራ ተሳትፎ የመንገድ ከፈታ ስራ ተከናወነ።

በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በኤዋን ቀበሌ በጎቲየና ጭቋራ መንደሮች በህብረተሰቡ የረዥም ጊዜ ጥያቄ የነበረ የመንገድ ከፈታ ሥራ ተካሄደ ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እንዳሉት ማህበረሰባችን በዚህ ልክ ተደስቶ በማየቴ እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ጠቁመው የመንገድ ከፈታ የመንግስት የግዴታ ስራው መሆኑንም ተናግረዋል::

ክቡር ከንቲባው አያይዘውም እየተሰሩ ያሉትን የከፈታ ሥራ የመስክ ምልክታ ማድረግ ለዘመናት የቆየውን የህብረተሰቡን የመሠረተ ልማት የመንገድ ከፈታ ጥያቄ ለመፍታት በኤዋን ቀበሌ የጎቲየና የጭቋራ አከባቢ የተከፈተው መንገድ በሌሎችም ቀበሊያት ቅንጅታዊ ሥራዎችን በማጠናከርና የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማጎልበት ተጠናክሮ ሊቀጠል እንደሚገባው አሳስበዋል ።

የአካባቢው ማህበረሰብ ላነሷቸው ሌሎች የልማት ጥያቄዎች በቀጣይ በተዋረድ ምላሽ እንደሚሰጥና ማህበረሰቡ እያደረገ ያለው የልማት ተሳትፎውን አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበትም ክቡር ከንቲባው አመላክተዋሌ::

በኤዋን ቀበሌ በጎቲየና ጭቋራ መንደር በጉብሬ መንገዶች ዲስትሪክት በህብረተሰቡ እና በከተማው አስተዳደሩ በጋራ ተሳትፎ የተጀመረው የመንገድ ከፈታው ስራ ያለቀለት እንዳልሆነና በቀጣይ የሚቀሩት ስራዎችን ከሌሎች ባለድርሻ ጋር በመሆን ባጠረ ጊዜ መፍትሄ እንደሚሰጠውም ክቡር ከንቲባው ጠቁመዋል ።

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ጉብሬ ዲስትሪክት ሀላፊ የሆኑት አቶ ትዛዙ በርታ እንደገለፁት የመንገድ ከፍታው የቆየ የነዋሪዋች ጥያቄ መሆኑን ያስረዱት ኃላፊው በመንግስትና በህብረተሰቡ ተሳትፎ ከ2.5 ኪ/ሜትር በላይ የተሰራ መሆኑን አስረድተው።

ይህ ልማት የተከናወነው ከመደበኛ የስራ ቀን ውጪ ከከተማ አስተዳደሩና ከቀበሌው ማህበረሰብ ጋር በቅንጅት የተሰራና ለስራው አስፈላጊ የሆኑትን ሁሉ በከተማ አስተዳደሩና በቀበሌው ማህበረሰብ የተሸፈነ መሆኑን ጠቁመዋል::

በሁለቱም መንደሮች ላይ በተደረገው የመንገድ ከፈታ የአጥር ግንባታዎችን ከማስነሳት ጀምሮ የተለያዩ የምንጣሮ ስራዎችም ማህበረሰቡ በማድረግ ላደረገው እገዛም አቶ ትዕዛዙ አመስግነዋል።

አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንዳሉት መንገዱ እንደሚከፈትልን ለዘመናት ስንዋሽ የነበረው ችግር በከተማ አስተዳደሩና በጉብሬ መንገዶች ዲስትሪክት መፈታቱ እጅግ እንደተደሰቱና በቀጣይ በየትኛውም የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር እንደሆኑም ተናግረዋል

መንገዱ ባልተከፈተበት ወቅት የታመመውን በቃሬዛ እንኳን ይዘን ወደ ህክምና ተቋም ማድረስ ሳንችል የህይወት መስዋዕትነት እንዳሰከፈላቸው በማንሳት

አሁን ላይ ለተደረገላቸው ሁሉ ከተማ አስተዳደሩንና የጉብሬ ዲስትሪክቱን በማመስገን ብልጽግና ፓርቲያችን ለተቸገሩ ሁሉ ደራሽ እንደሆነ በእናንተ ተመልክተናል ብለዋል::

Previous በዞኑ የትምህርት መሰረተ ልማት በማሻሻል የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር ችግር ለመፍታት እየተሰራ ያለው ስራ በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo