
የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነት ለመቀነስ ዘርፈ ብዙ ተቋማዊ አደረጃጀቶች በመፍጠር ሲሰራ የነበረ ሲሆን ይህንንም በስፋትና በጥራት እየተከናወነ መሆኑን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና ንግድ ገበያ ልማት ፅህፈት ሀላፊ አቶ ሙባሪክ ዘይኑ የገለፁ ሲሆን በቀጣም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት በጋራ በመስራት ወደ ሰፋፊ የገቢያ ቦታዎች በማሸጋገር ሁለንተናዊ የግብይት ስርአት ለመፍጠር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።





