የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 2ኛ ዙር 11ኛ አመት 39ኛ መደበኛ ጉባዔ ያካሄደ ሲሆን በጉባዔውም በከተማው በተለያዩ የልማት ዘርፎች የተሰሩ ስራዎች ገምግ

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ዋና አፈ-ጉባዔ አቶ ሸምሱ በሽር በጉባዔው መክፈቻ ወቅት እንደገለፁት የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ የምክር ቤት አባላት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል ።

ምክር ቤቶች የህዝብን ሉዓላዊነት መገለጫዎች መድረኮች በመሆናቸው የምክር ቤት አባላትም የተጣለባቸው ሀላፊነት መወጣት አለባቸው ሲሉ ክቡር አፈ-ጉባዔ አስገንዝበዋል ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው እንደገለፁት የከተማው ማህበረሰብ እየጠየቀ ያለው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ህዝቡን አሳትፈን ደረጃ በደረጃ እንሰራለን ብለዋል።

ወልቂጤ ከተማ እንዳይረጋጋ እና ሰላም እንዳይሆን ከሚሰሩ አካላት ከተማውን በመታደግ ለከተማዋ ሰላም በጋራ ልንቆም ይገባል።

ከተማውን ከልማት ለማውጣት በተለያዩ ቦታዎች አመፅ የሚያነሱ ግለሰቦችን ተጠያቂ ለማድረግ ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በትኩረት እየተሰ እንደሚገኝ ገልፀው በየትኛው አጀንዳ ተጠቂ ሳንሆን የከተማችንን እድገት ማፋጠን አለብን ሲሉ ከንቲባው ገልፀዋል።

ለዘላቂ ሰላምና ፀጥታ የሀይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች ትልቁ ሚና የሚወስዱ ሲሆን ትውልድን መልካም ነገር ተምሮ እንዲያድግ ሁላችንም በሃላፊነት ልንሰራ ይገባል ሲሉ ከንቲባው አሳስበዋል።

የከተማዋ ልማት ልናረጋግጥ የምንችለው የገቢ ምንጫችን በማሳደግ በመሆኑ የተጀመሩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅ ገቢ የምናገኝበት አማራጮቻቻችንን በማስፋት ህዝቡ በማሳተፍ ውጤት ያለው ስራ መስራት አለብን ብለዋል።

እንዲሁም የንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦ ችግር ለመቅረፍ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ሲገኝ በኢፌዴሪ ውሀና ኢነርጂ በተገኘው ድጋፍ የጣጤሳ የውሀ ፕሮጀክት አሁን ላይ አገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆን የቦዠባር የውሀ ፕሮጀክት አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል በባለሙያዎች ጥገና እየተደረ እንደሚገኝ ገልፀዋል ።

ከምክር ቤት አባላት ከተነሱ ሀሳቦች መካከል ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ ሁላችንም ለሰላም ዘብ መቆም አለብን ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ አስቸጋሪ የነበሩ መንገዶችን ከፈታና ጠረጋ ስራ መልካም አፈፃፀም የታየበት ሚበረታታ መሆኑን ገልፀው በቀጣይም ቀሪ መንገዶችን ህብረተሰቡ በማሳተፍ መጠናከር እንዳለበትም ተናግረዋል።

በከተማዋ እየተፈጠረ ያለው የሰላም መደፍረስና የሰው ልጅ ህይወት መጥፋት መንግስት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ያሉ ሲሆን በዚህ ጥፋት የተሳተፉ አካላት በህግ እንዲጠየቁ ጠይቀዋል።

እንዲሁም መሰረታዊ ችግሮች በመለየት ከተማዋ ወደ ነበረችበት መልካም ገፅታዋ እንድትመለስ እና የተለየ ተልኮ ተቀብለው ለሚቀሳቀሱ አካላት ተጠቂ እንዳንሆን የበኩላችንን እንወጣ ሲሉ አስተያየታቸውን አስቀምጠዋል ።

የጥፋት ሀይሉ ገና ምንም የማያቁ ልጆች ላይ ትኩረት በማድረግ የነገ ሀገር ተረካቢ እና ተተኪ ትውልድ ላይ ጥላቻ በመዝራት የሚያደርገው እንቅስቃሴ ወላጆች ልጆቻቸውን መከታተል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል ።

በከተማው የስራ እድል ከመፍጠር አንፃር እንቅስቃሴ ማነስ፣የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት እየተሰራ አለመሆኑ፣የእሳት አደጋ መኪና ከታለመለት አላማ ውጪ መዋል፣ የጎዳና ንግድ ክትትል ማጣት፣-ትራንስፖርት የትኬት ስራ ቢኖርም መንገድ ላይ ጭማሪ መጠየቅ የመሳሰሉ ጥያቄዎች ከምክር ቤት አባላት ተነስቷል ።

ለተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ከተቋማት ሀላፊዎች እና ከመድረኩ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን ቀጣይ ሁሉም የሚመለከተው በመውሰድ ለውጤት እንዲሰራ ተገልጿል።

በመጨረሻም የ2016 በጀት አመት የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር እቅድ የውል ስምምነት በመፈራረም በ2015 በጀት ዓመተ አፈፃፀም ምዘና ለሴክተሮች የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል።

ሲል የዘገበው  የወልቂጤ ከተማ መንግስት ኮሚኒኬሽን ነው

Previous ሆቴሎች ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ የማህበረሰቡን ባህል በማስተዋወቅ እረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo