የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ተቋማት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በቅንጅት የመስራት እንደሚገባ:-አቶ ሙራድ ከድር ገለፁ።
=======================
ጥቅምት 7/2018ዓ.ም [ወልቂጤ]
በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት አመት 1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ከተቋም አመራሮች በጋራ በመሆን ገምግሟል::
በወቅቱ የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ሙራድ ከድር እንደገለፁት የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ተቋማት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በቅንጅት የመስራት እንደሚገባ ገልፀው።
የህዝባችንን ችግር ደረጃ በደረጃ በመፍታት ከተማችንን የስበት ማዕከል ለማድረግ አስበን እየሰራን በመሆኑ በ1ኛ ሩብ አመት የተከናወኑ ተግባራዊ መልካም መሆናቸውን ጠቁመው
ሥራን ቆጥሮ በመስጠትና በመረከብ የአገልጋይነት ስብዕናን በመላበስ ህዝብንና ከተማን የሚያሻግር ሥራ መስራት ይገባል ያሉ ሲሆን
በ2017 ያሳካናቸውን ስኬቶች በተጠናከረ መልኩ 2018አመት ሊደገሙ እንደሚገባ በኮሪደር ልማት፣በገፅታ ግንባታና መሰል በሆኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ላይ የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማሳደግ በርካታ ተግባራትን ማከናወን እንደሚገባ ጠቁመው።
የሚታቀዱ ስራዎች ጥራታቸውን ለማስጠበቅና ውጤታማ እና የተሳካ እንዲሆን ለማስቻል ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት በ1ኛ ሩብ አመት ያላሳካናቸው ተግባራት ቢኖሩ ለቅሞ በመያዝ በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ መስራትና የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የመድረኩ ተሳታፊዎች እንደገለፁት አደረጃጀቶችን በማጠናከርና ትስስር ያላቸውን ሴክተር መስሪያ ቤቶች በመቀናጀት ማህበረሰብ ሊያስጠቅም የሚችል ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝና ይበልጥ መጠናከር እንዳለበት አመላክተው
የከተማው ጽዳት ህዝባዊ ከማድረግ፣ስድ እንስሳትን ከመቆጣጠር፣የጉራጊኛ ቋንቋ ከማዳበር፣ምክኒያታዊ ያልሆኑ የዋጋ ጭማሪዎች መቆጣጠር፣ግብይትን የደረሰኝ ቁጥጥር ስርአት በተመለከተና መሰል ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሀሳቦች ቀርበዋል።
ከቀረበው ሪፖርት በመነሳት በከተማው የተሰሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ጥንካሬዎችን በመለየት ጉድለቶች ላይ እንዲሁም በተነሱ ሀሳብ አስተያየቶች ዙሪያ ከቤቱ በስፋት ውይይት ተደርጎበት ሁሉም የድርሻውን መውሰድ እንዳለበት የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጦ መድረኩ ተጠናቋል።

