ከንቲባ ችሎት በህብረተሰቡ ዘንድ የሚነሱ የልማትና መልካም አስተደደር ጥያቄዎችን እና ቅሬታዎችን አግባብነት ባለው መልኩ መልስ ለመስጠት ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው።
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳምንታዊ ከንቲባ ችሎት ተጠናክሮ ቀጥሏል።
“ከንቲባ ችሎት” የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ሰብሳቢነት ከህብረተሰቡ የሚነሱ አቤቱታዎችና ቅሬታዎች ቀርበው የሚታዩ ሲሆን ችሎቱ የቀረበዉን አቤቱታ እየሰማ ከሚመለከታቸዉ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ጋር በመምከር ዉሳኔዎችን ይሰጣል።
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር በችሎቱ እንደተናገሩት ከንቲባ ችሎት በህብረተሰቡ ዘንድ የሚነሱ የልማትና መልካም አስተደደር ጥያቄዎችን እና ቅሬታዎችን አግባብነት ባለው መልኩ መልስ ለመስጠት ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ሲሉ ገልፀዋል ።
መንግስት በህዝብ ዘንድ ተዓማኒነት እንዲኖረው መልካም አስተዳደርን የማስፈን አሰራርን ማጠናከርና ቀጣይነቱን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

ከከንቲባ ችሎት ተገልጋዩ ህብረተሰብ ያለምንም እንግልት በከንቲባ ችሎት መቅረብ የሚችሉ ጥያቄዎች እና ቅሬታዎች በማቅረብ በቀላሉ መፍትሔ የሚያገኝበት መሆኑን ገልፀዋል።
በከተማችን የተሰሩ ያሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ለማሳለጥ በህዝብ ተሳትፎ ከፍተኛ ርብርብ እየተከናወነ መሆኑ የገለፁት አቶ ሙራድ በዚህም ስራ የከተማችን ማህበረሰብ በተለያየ መልኩ ተጎጂ እንዳይሆን በህግና በአሰራር ችግሮችን እየለየን አስተዳደራዊ ስራዎች እየፈተሽን እንሄዳለን ብለዋል።

በማህበረሰቡ ዘንድ የሚነሱ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች ደረጃ በደረጃ አሰራርና መመሪያ መሠረት ያደረገ ሁሉም የድርሻውን ወስዶ ሊሰራ እንደሚገባ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ሀላፊ አቶ ቶፊቅ ሱልጣን ተናግረዋል።
በተለያየ መልኩ በማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚቀርቡ ቅሬታዎችና ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም ገልፀዋል።
በከንቲባ ችሎት የሚቀርቡ ጉዳዮች ማህበረሰቡ ግንዛቤ ሊኖረው እንደሚገባ ተጠቁሟል።

በከንቲባ ችሎት ከሚነሱ ጉዳዮች ከከተማ መሬት አስተዳደር ፣ከግዢ ስርዓት፣ከፍትህ ስርዓት አገልግሎት አሰጣጥ፣ከመንግሰት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ከግብይትና ከንግድ ስራዎች ፣ከትራንስፖርት እና ስምሪት እንዲሁም አጠቃላይ ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ላይ የሚነሱ ቅሬታዎች የሚስተናገዱበት መሆኑን ተጠቁሟል ።

በከንቲባ ችሎት የማይታዩ ጉዳዮች በፍርድ ቤት የተወሰነ ወይም በሂደት ያለ፣የታክስና የግብር ፣ከፍተኛ የሙስና ወንጀል ፣ወንጀል ሌብነትና ዘረፋ፣በተለያየ ደረጃ ምክርቤቶች እየታዩ ያሉ፣በካታ ኮሚቴ እየታዩ ያሉ ጉዳዮች ችሎቱ እንደማያስተናግድ ተነስቷል ።

