ከቃል ወደ ተግባር ጊዜ ላይ ያለን በመሆናችን የህብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ በልዩ ትኩረት መስራት ይጠበቅብናል ያሉት ሚኒስትሯ ከክልልና ከዞን ጋር በቅንጅት በመስራት ሆስፒታሉ በያዝነው በጀት አመት እና በቀጣይ በጀት ዓመት እንዲጠናቀቅ የምንሰራ ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል

2017 ዓ/ም (ወልቂጤ )

በኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የተመራው ልዑክ በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ በጤናው ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ጉብኝት አድርጓል።

ሚኒስትሯ እና በእርሳቸው የተመራ ልኡክ በወልቂጤ ጤና ጣቢያ የነፍሰ ጡር እናቶች ማቆያ ፣የድህረ ወሊድ፣ የህክምና፣ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም እንዲሁም በጤና ጣቢያው በተለያዩ የስራ ክፍሎች እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት የተመለከቱ ሲሆን በተጨማሪም እየተገነባ ያለውን የወልቂጤ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አሁን ያለበት የግንባታ ደረጃ ጉብኝት ተደርጓል ።

በጉብኝቱ የሆስፒታሉ የስራ ተቋራጭ አቶ ዮሀንስ ሀይሌ በሠጡት ማብራሪያ ግንባታው በ2012 ዓ.ም ወደ ስራ መገባቱን ገልፀው በተለያዩ ምክንያቶች በተቀመጠለት ጊዜ ማጠናቀቅ እንዳልተቻለ አብራርተዋል።

አሁን ላይ ግንባታው የፊዚካል ስራ 85 በመቶ መጠናቀቁን ገልፀው አሰፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ በአጭር ጊዜ የሆስፒታል ግንባታው አጠናቆ ማስረከብ እንደሚቻልም አስረድተዋል።

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በጉብኝቱ እንደገለፁት በከተማ አስተዳደሩ በጤናው ዘርፍ እየተሰሩ ባሉ ተግባራት መደሰታቸውን ገልፀዋው።

የወልቂጤ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግንባታ አሁን ያለበት አፈፃፀም መነሻ በማድረግ በአጠረ ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲውል ጠንካራ ስራዎች መስራት ይገባል ብለዋል።

ከቃል ወደ ተግባር ጊዜ ላይ ያለን በመሆናችን የህብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ በልዩ ትኩረት መስራት ይጠበቅብናል ያሉት ሚኒስትሯ ከክልልና ከዞን ጋር በቅንጅት በመስራት ሆስፒታሉ በያዝነው በጀት አመት እና በቀጣይ በጀት ዓመት እንዲጠናቀቅ የምንሰራ ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል ።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንደተናገሩት የወልቂጤ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የብዙ የሀገራችን ሆስፒታሎች ሞዴል መሆን የሚችል በልዩ ስታንዳርድስ እየተገነባ ያለ ግንባታ መሆኑን ገልፀዋል ።

የሀገርና የህዝብ ሀብት ወጪ የተደረገበት በመሆኑ ሁላችንም ተረባርበን ለታለመለት ዓላማ እንዲውል የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም ለኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በሀገር ሽማግሌዎችና አባቶች በጉራጌ ባህል መሠረት የክብር ስምና ስጦታ የተበረከተላቸው ሲሆን “የትከ አጂየት” በማለት የክብር ስም ተሰይሞላቸዋል።

በመርሐ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አብዱልቃድር ገልገሎ (ዶ/ር )፣ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ደረጄ ዱጉማ (ዶ/ር )፣ የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድርን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

Previous የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እንደገለጹት፥ እንደ ሀገር በርካታ ፈተናዎችን እየተሻገርን አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ የሚያስችል አቅም ተፈጥሯል ብለዋል።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo