ሀገራችን በ2025 ዲጂታል ኢትዮጵያ ለመፍጠር በምታደርገው ጥረት የፈጠራ ስራዎች ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን ተገለፀ።

ሀገራችን በ2025 ዲጂታል ኢትዮጵያ ለመፍጠር በምታደርገው ጥረት የፈጠራ ስራዎች ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን ተገለፀ።

በጉራጌ ዞን ዞናዊ የሳይንስና ፈጠራ ስራዎች ውድድርና ኤግዚብሽን በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል::

ተማሪዎች ዝንባሌያቸዉ ወደ ሳይንስና ቴክኖሎጂ በማድረግ የአካባቢዉን ማህበረሰብ ችግር ሊቀርፉ የሚችሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በመፍጠርና በዘርፉ ዉጤታማ ስራዎች እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

የወልቂጤ ከተማ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት እና ከትምህርት ጽህፈት ቤት በጋራ በመተባበር ዞናዊ የሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ዉድድር ለይ ተሳታፊ ሆነዋል።

በሀገራችን ትኩረት ከተደረገባቸዉ ዘርፎች መካከል በግብርና ፣በኢንዱስትሪ ፣ በማዕድን ፣በማኒፋክቸሪንግና በሌሎችም ዘርፎች ተቋሙ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በእነኚህ የትኩረት መስኮች ቴክኖሎጂን ለማዘመንና በዲጂታል ኢኮኖሚ ለማረጋጥ ተቀብሎ የሚሰራ ተቋም መሆኑን የወልቂጤ ከተማ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሃምዱ ካሚል ገልጸዋል።

አክለውም የዘንድሮ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽን ለየት የሚያደርገዉ በአምስት ዘርፎች የሚቅረብ ስራ የተሰራ ሲሆን እነዚህም አዳዲስ ቴክኖሎጂ ፣ በመምህራንና በተማሪዎች እና በግል ተወዳዳሪዎች የቀረቡ የፈጠራ ስራዎች መኖራቸዉን ገልፀው።

ለዉድድር የቀረቡ የፈጠራ ስረዎች ለከተማው ማህበረሰብ ችግር ፈቺና በአጭር ጊዜ ዉስጥ ገበያ ላይ ቢዉሉና ምርትና ምርታማነታቸዉ የተረጋገጡ የፈጠራ ስራዎች ናቸዉም ብለዋል።

የሳይንስ ትምህርቶች አጠናክሮ እና ተማሪዎች በንድፈ ሃሳብ የሚማሩትን ትምህርት በተግባር አስደግፈው እንዲሁም የፈጠራ ስራዎችና ነገ ስራ ፈጣሪ ትውልድ በማብቃት ሀገር ተረካቢ ዜጋ መፍጠር ነው ያሉት የከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ስሜነሽ ግርማ ናቸው።

የወልቂጤ ከተማን ወክለው በፈጠራ ስራ ውድድር ላይ የተሳተፉት የሰጎመ ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት መምህር ታምራት ተስፋዬ እንደገለፁት ይዘው የቀረቡትን ዘመናዊ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ተሳክቶ ወደመሬት ወረዶ ማህበረሰቡን ለማስጠቀም ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀው።

በየትምህርት ቤቱ ያሉ ሁሉም የፈጠራ ስራ ክበባት ለተማሪዎችና ለመምህራን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የተሻሉ የፈጠራ ስራዎች እንዲሰሩ ድጋፍ ቢደረግ መልካም ነው ብለዋል።

የወልቂጤ አንደኛ ጀረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነው ሃምዱ ሙባሪክ እንደገለፁት ተማሪዎች ለፈጠራ ስራ ተነሳሽነት ያላቸው ቢሆንም የትምህርት ቤቱ በጀት በሚፈለገው ልክ ለመንቀሳቀስ ምቹ ሁኔታ ባለመፈጠሩ የተማሪዎች ፍላጎት የገደበ በመሆኑ በቀጣይ ድጋፉ የተጠናከረ መሆን መቻል አለበት ሲሉ ገልጸዋል።

የውድድርና አውደርዕይ በነገው ዕለት የዞኑ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ማጠቃለያ የሚያገኝ ይሆናል።

ሲል የዘገበው የወልቂጤ ከተማ መንግስት ኮሚኒኬሽን ነው::

Previous Gurage zone science and information technology in cooperation with the zonal education department will be held 3rd round zonal creativity competition and exhibition under the theme “encouraging innovators for higher national development” from April 18-19 in Welkite city.

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo