መስከረም 5/2017ዓ.ም[ወልቂጤ]

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፖርቲ ጽህፈት ቤት በታላቁ የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ ለምርቃት መብቃት በሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ ዙሪያ ከከተማው አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ።
በከተማችን በሚካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ክበባት፣ተማሪዎች፣መምህራን፣የትራንስፖርት ዘርፍ ሰራተኞች፣የሴቶች አደረጃጀቶች ፣ተሽከርካሪዎች ፣የነጋዴዎች እንዲሁም ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች እንዲሳተፍ ማድረግ እንደሚጠበቅም ተጠቁሟል።

ሀሙስ በሚደረገው በድጋፍ ሰልፍ በከተማው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በነቂስ ወጥተው ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተገልጿል።
በከተማውና በክፍለከተማው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰዓቱ በመገኘት ሰልፉን መሳተፍ የሚችሉበት ምቹ ሁኔታ በትራንስፖርት ዘርፍ ምቹ ሁኔታ መፈጠር እንዳለበትም ተመላክተዋል።

ድጋፍ ሰልፉ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን ወስዶ በመስራት ይህ ትልቅ ሁነት ማሳካት እንደሚገባና የነጋዴው ማህበረሰብ ፣ስፖርት ቤቶች፣የትራንስፖርት ማህበራት፣ሴክተር መስሪያ ቤቶች ድጋፉን የሚገልጹ ባነሮችና ቲሸርቶች በማሳተም የፕሮግራሙ ድምቀት መሆን እንደሚጠበቅባቸውም አቅጣጫ ተቀምጧል።

