የሀገር ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ የጉራጌ ዞን ወጣቶች እያደረጉት ያለው ንቁ ተሳትፎ አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው ገለጹ።

የሀገር ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ የጉራጌ ዞን ወጣቶች እያደረጉት ያለው ንቁ ተሳትፎ አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመድረኩ ላይ እንዳሉት የጉራጌ ዞን ወጣቶች ለሀገር ልማትና እድገት የሚያደርጉት ንቁ ተሳትፎ ለሁሉም ወጣቶች በሞዴልነት የሚጠቀስ ነው።

በመሆኑም የዞኑ ወጣቶች ይህንኑ ንቁ ተሳትፎ አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ አስገንዝበዋል።

በዞኑ የተጀመሩ የመንገድ፣ የውሃ፣ የጤና፣ የትምህርት፣ የስራ እድል ፈጠራ፣ የመዝናኛ ማዕከላት ግንባታዎች እና ሊሰሩ የታቀዱ ፕሮጀክቶች ተሰርተው የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።

የወልቂጤ ከተማ ማስተር ፕላን ወደ ስራ አስገብቶ ተግባራዊ ለማድረግ የክልሉ መንግስት በአጽንኦት እየሰራ ይገኛል ያሉት ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው ይህንንም ተግባር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰፊ ውይይት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።

የክልሉ መንግስት በትኩረት ከሚሰራባቸው አጀንዳዎች ሰላምን ማረጋገጥ፣ ግብርና በማዘመን የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት፣ የገቢ አቅምን አሟጦ መጠቀም፣ የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት ማስፋት፣ የህብረተሰቡን ጤናን ማስጠበቅ፣ ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር፣ ንግድና ኢንቨስትመንት ማስፋፋት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

የዞኑ ወጣቶች በሰላም፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካው እያደረጉት ያለው ንቁ ተሳትፎ በማጠናከር የብልጽግና ጉዞ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ይግለጡ አብዛ እንዳሉት የተጀመረዉን የብልፅግና ጉዞ ለማስቀጠል ባለፉት ጊዜያት የተዛነፉ ጉዳዮችን ለማረም ከወጣቱ ጋር በመቀናጀት በጋራ እየተሠራ ይገኛል።

ዛሬ ከጉራጌ ዞን ወጣቶች ጋር በተደረገዉ ዉይይት ላይ የተነሱ የሰላም፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና የፖለቲካዊ ጥያቄዎች በየደረጃው በመለየት መፍትሄ ለማስቀመጥ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የጉራጌ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ አንድነት የራሱን አሻራ አሳርፏል ያሉት አቶ ይግለጡ በቀጣይም የብልጽግና ጉዞ እውን እንዲሆን የጉራጌ ወጣቶችም በመደመር እሳቤ ፓርቲው ያቀዳቸው እቅዶች ተፈጻሚ እንዲሆኑ ከመንግስት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንደገለፁት፣ በዞኑ የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት ይሰራል ያሉ ሲሆን እነዚህም አጠናክሮ በመስራት ዞኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም ለማድረግ እንጥራለን ብለዋል።

የጉራጌ ህዝብ ከትንሽ ተነስቶ የሀብት ማማ ላይ የመድረስ ጠንካራ የስራ ባህል ያለው ሀገሩንም የሚወድ ብዙ ጀነራሎችም ለሀገሪቱ ያበረከተ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል ።

በመሆኑም የጉራጌን ፖለቲካ ከእጁ ለመንጠቅ የተደረገው ሙከራ የጉራጌ ህዝብ በእጅጉ የሚያወግዘው መሆኑን የገለጹት አቶ ላጫ ወጣቱ ለውጡን ያዋለደ በመሆኑ ቀጣይም ለውጡን ለማጽናት ከመንግስት ጎን በመሆን መስራት ይጠበቅበታል።

ጠቅላይ ሚኒስትራችንም ተጨማሪ እድል ሰጥተውን ከህዝባችን ጋር ለመመካከር በተደጋጋሚ ወደ ዞኑ መምጣታቸዉ ለዞኑ ህዝብ ያላቸውን ክብርና ፍቅር ማሳያ በመሆኑ በነገው ዕለትም ሁሉም ማህበረሰብ ባለው የእንግዳ አቀባበል ባህል መሰረት በክብር እንድንቀበል ጥሪ አቅርበዋል።

Previous የመርካቶው ነጻ አውጭ- ፊታውራሪ ሩጋ አሻሜ

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo