



በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎሮሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ከትምህርት ጽህፈት ቤት ጋር በጋራ በመሆን “ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለሁለንተናዊ ሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ የፈጠራ ስራ ውድድሮች ሽልማትና የፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
የሳይንስና ፈጠራ ውድድር ዓላማው አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ መምህራን እና ተማሪዎች ፈጠራን የሚያበረታታ በትምህርት ያገኙትን በሳይንስና ፈጠራ ስራ ተጨባጭ ለማድረግ ታሳቢ የተደረገ ሲሆን፡፡
የተማሪዎች የፈጠራ ሥራ የሀገራዊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ መሰረቶች እንደመሆናቸው መጠን በፈጠራና በቴክኖሎጂ በመታገዝ ሀገራዊ ልማትና እድገትን ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት የተማሪዎች ሚና የሚያጠናክር ስለ መሆኑን ተመላክቷል።
በመርሀ ግብሩ የከተማው ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት የፖለቲካ ዘርፍ ተጠሪ አቶ ጴጥሮስ አስራት፣ የአደረጃጀት ዘርፍ ተጠሪ ወይዘሮ መንዚላት አህመድ፣የጉራጌ ዞን ትምህርት መመሪያ ሀላፊ አቶ መብራቴ ወልደማሪያም የወልቂጤ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወይዘሮ ስሜነሽ ግርማ ፣በወልቂጤ ከተማ ሳይንስና ኢንፎሮሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሃምዱ ካሚል፣ርዕሳነ መምህራንና የፈጠራ ስራ ተጠሪ መምህራኖች፣የሁለቱም ጽህፈት ቤት ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።


