ህዳር 14/2019ዐዓ.ም [ወልቂጤ ]

የነገውን ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራት በተማሪዎች ምገባ ላይ የሚደረግ ወጪ ትልቅ ሀገራዊ ኢንቨስትመንት መሆኑ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ገለፀ።
ህዳር 14/2019ዐዓ.ም [ወልቂጤ ]
በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በ14ቱም የመንግስት ትምህርት ትምህርት ቤቶች ለ2575 የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች ምገባ ተጀመረ።
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እንደገለፁት በተማሪዎች ምገባ ላይ የሚደረግ ወጪ የነገውን ሀገር ተረካቢ አምራችና ሃላፊነት የሚሰማውን ትውልድ ለመገንባት የሚደረግ ትልቅ ሀገራዊ ኢንቨስትመንት ነው ሲሉ ተናግረዋል ።

በመደመር መንግሰት በኢኒሼቲቭ ፕሮግራም የተጀመረውን ትውልዱ መሰረታዊ እውቀት እንዲዝና በአግባቡ ትምህርቱን እንዲከታተል እንዲሁም የሚጠበቅበት ውጤት እንዲያመጣ የሚያግዝ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
የተማሪዎች ምገባ የትምህርት ተሳትፎ እና ጥራት በማሳደግ በእውቀት የዳበረና ለሀገር እድገትና ብልፅግና የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር በተለያዩ በኢኮኖሚ ችግር ውስጥ የሚገኙ ልጆችን ማገዝና መደገፍም ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
የተማሪዎች ምገባ በመንግስት፣በማህበረሰቡ እና ባለሀብት ተሳትፎ በሚጠበቀው መጠን ለማከናወን የሀብት አሰባሰብ ስርዓት አስቸጋሪ ሁኔታዎች መግጠሙን አስታውሰው በልዩ ቅንጅት ሁሉም የበኩሉን ጥረት በማድረግ ወደ ስራ መገባቱን አንስተዋል።

በሀብት አሰባሰብ ለትምህርትና ለልማት ህብረተሰባችን ሆነ የከተማው ባለሀብት እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነዉ ብለዋል።
ባለሀብቱ በተነሳሽነት አንድ ትምህርት ቤት በሃላፊነት በመውሰድ ምገባ እያደረጉ በመሆኑን አቶ ሙራድ ገልፀዋል ።
በመንግስት በበጀት ዓመቱ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ በልዩ ትኩረት በቅንጅትና የሚመራ በመሆኑ በክትትል ስራዎች በጥራት እየተከናወኑ መሆናቸው አንስተዋል።
ከተማ አስተዳደሩ ለተማሪዎች የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኙና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ያሉት ከንቲባው የጀመርነው ስራ በውጤት እንዲጠናቀቅ ሊያግዙን ከጎናችን ያሉ የከተማችን ነዋሪዎችም እንዲሁም እንደ SNV ድርጅቶችም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ለተማሪዎች በምገባ ምግብ የሚያቀርቡ አካላት ሀላፊነት ወስደው የሚሰሩት ስራ አጠናክረው በመቀጠል የበኩላቸው እንዲወጡ ጠቁመዋል።
ለነገ የተሻለ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመፍጠር በምናደርገው ርብርብ ሁሉም የከተማችን ማህብረሰብ እና ባለሀብቱ የበኩሉን በመወጣት ሃላፊነታችን እንወጣ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ዘመቻ እንደተናገሩት በ2018ዓ.ም ጀምሩ የተማሪዎች ምገባ ለማድረግ እንቅስቃሴ በማድረግ በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች መጀመር መቻሉን አስታወሰዋል።
በአሁን በዚህ በጀት አመት ህዝባዊ መሠረት በመፍጠር በመንግሥት ልዩ ድጋፍ ወደ ተግባር ተገባቱን ገልፀዋል።
ትውልድ ላይ የምንሰራው ስራ በመሆኑ የተማሪዎች መጠነ ማቋረጥ የሚቀንስ፣ ማርፈድ እና በተለያዩ የኢኮኖሚ ውስንት ያለባቸው ህፃናትን የምንደግፍበት ነው።

ህዝባችንን ተስፋ አድርገን አንድ ትውልድ ከትምህርት ገበታ እንዳይርቅ ትውልድን የምናድንበት ትልቅ ተግባር መሆኑ ገልፀዋል።
አጠቃላይ በከተማችን በ14ቱም የመንግስት ትምህርት ትምህርት ቤቶች ለ2575 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ምገባ መጀመሩን አስረደተዋል።
ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ምገባ በሚያደርጉት ወቅት ለስራው መስተጓጐል ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችን ለቅሞ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚስራ ተናግረዋል
የከተማችን ማህበረሰብ፣ባለሀብቶች እንዲሁም አጋር አካላት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው በማስቀጠል የነገ ሀገር ተረካቢ ልጆቻችን ላይ በጋራ እንስራ ሲሉ መልዕክ አስተላልፈዋል።

የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ምገባ ላይ ርዕሰ መምህራን በሰጡት አስተያየት መንግስት የጀመረው የምገባ መርሀ ግብር ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ቀጣይነት እንዲኖረው ህፃናት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩና ነገ ሀገር ተረካቢ በእውቀት ላይ የተመሠረት ስራ እንዲሰራ ለማስቻል የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።

