
እንደ አቶ ቃልአብ ገለፃ ወጣትነት ለለውጥ መነነሳሳት፣ለራሳችንን መገዛት የምናስተምርበት ሲሆን ጊዜው ካልተጠቀምንበት ግን ቁጭት የሚፈጥር መሆኑንም አመላክተዋል።
ዛሬ በወጣትነትህ የምትገነባው ስብዕና የነገው ማንነትህ መሰረት ነው” የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት።
ወልቂጤ-ህዳር 15/2019 ዓ.ም

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት አዘጋጅነት ከ200 በላይ ለሆኑ ወጣቶች በወጣቶች ስብእና ግንባታ፣እራስን በማወቅና በአዕምሮ ግንባታ እንዲሁም በኤች አይ ቪ ዙሪያ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
የዕለቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በወጣቶች ስብዕና ግንባታ በተመለከተ እራስን በማወቅና በአዕምሮ ግንባታ ዙሪያ ከወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በአቶ ጌቱ ደጉ እና በኤች አይ ቪ ዙሪያ ከጤና ጽህፈት ቤት በወይዘሮ ቤተልሄም የተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ቃልአብ ደመቀ በስልጠናው ተገኝተው እንደገለፁት ወጣቶች በመልካም ስብዕና መገንባት በሀገሪቱ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፏቸው እንዲያዳብሩ የሚረዳ መሆኑ ገልፀዋል።
በመልካም ስብዕና የታነፀ ትውልድና ወጣት ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ልማትና እድገት የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ ለወጣቶች በቂ ትኩረት በመስጠት እና ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ስብዕናቸው በተገቢው ሁኔታ መቅረጽ አስፈላጊነቱ የጎላ ነው ብለዋል።

እንደ አቶ ቃልአብ ገለፃ ወጣትነት ለለውጥ መነነሳሳት፣ለራሳችንን መገዛት የምናስተምርበት ሲሆን ጊዜው ካልተጠቀምንበት ግን ቁጭት የሚፈጥር መሆኑንም አመላክተዋል።
በከተማው የወጣቶች ስብዕናን ለመገንባት እና በስነ-ምግባር እንዲታነጹ ለማድረግ በክበባት፣ በአደረጃጀቶች እና በወጣት ማዕከላት በመታገዝ የተለያዩ የሰብዕና ግንባታ ስራዎች እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
በከተማው በሚሰሩ ልማቶች ያገባኛል የሚል ወጣትና በጥቅማጥቅም ያልተገነባ የወጣት ስብዕና ሊኖረን ይገባልም እንደሚገባም ተገለፀ።
ጽህፈት ቤቱ የወጣቶችን ስብዕና ከመገንባት ባለፈ በክረምትና በበጋ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ወጣቶችን በማሰማራት በከተማው በርካታ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል።

በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የትምህርትና የስነባህሪ ኮሌጅ መምህር አቶ ጌቱ ደጉ በበኩላቸው ወጣቱ ራሱን፣ ማንነቱን፣ ችሎታውን፣ ድክመቱን፣ ስሜቱን፣ ፍላጎቱንና ዓላማውን በትክክል በመረዳት ህይወቱ ማስተካከል እንዳለበትና ወጣቱ ራሱን ካላወቀ የሚፈልገውን ሕይወት ለመገንባት ሊከብድ እንደሚችል በስፋት ገልጸዋል።
ኤች አይ ቪ ማለት የሰውን ሰውነት ከበሽታ የሚከላከለውን የበሽታ መከላከያ ሥርዓት የሚያጠቃ ቫይረስ እንደሆነና ሰውነትን የመከላከያ አቅም በጣም ካዳከመ በኋላ ሊከሰት የሚችል ከባድ የበሽታ በመሆኑ ወጣቱ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ግንዛቤ የፈጠሩት ከጤና ጽህፈት ቤት በወይዘሮ ቤተልሄም ናቸው።

ወጣቶች በሰጡት አስተያየት የተሰጣቸው ስልጠና ሊገባቸው በሚችል መልኩ የተሰጠበት አግባብ አመስግነው ስልጠናው ራሳቸውን የፈተሹበት እንደሆነና ለቀጣይ እንዲህ አይነት ስልጠናዎች ተጠናክረው ቢቀጥሉ ለወጣቱ የነገ ህይወት መሠረት የሚጥል ነው ብለዋል።
በተጨማሪም ለወጣት ስብዕና ግምባታ የተዘጋጁ ማዕከላት ሁሌም ስራ ላይ ሊሆኑ እንደሚገባ አሳስበው በወጣትነት ከወደቁበት እንዴት መነሳት እንደሚቻል፣የወደፊት የወጣቱ ራዕይ እንዴት ማሳካት እንደሚቻል በቂ ዕውቀት ያገኘንበት ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

