7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ነፃ ፣ፍትሃዊ፣በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያለውና ዲሞክራሲያዊ ለማድረግ እየተሰራ ነው፦ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ነፃ ፣ፍትሃዊ፣በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያለውና ዲሞክራሲያዊ ለማድረግ እየተሰራ ነው፦ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል

የካቲት 17/2018(ወልቂጤ)፦የጉራጌ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በዞኑ በሁሉም መዋቅሮች የፖለቲካና የአደረጃጀት ስራዎችናን ጨምሮ የምርጫ ምቹነት ሁኔታ መነሻ በማድረግ ያደረገውን የሱፐርቪዥን ስራ ሪፖርት ደጋፊ አመራሮች በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ ገምግሟል።

የጉራጌ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል እንደገለፁት በዞኑ የፖለቲካና የአደረጃጀት ስራዎች ለማጠናከር የሚያስችል ወጥነት ባለው መልኩ ስራዎች እየተሰሩ ነው።

በዚህም ያሉ ጉድለቶች ለማረም እና ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል ብሎም የህዝቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በዞኑ ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በስሩ የሚገኙ ሁሉም መዋቅሮች የብልፅግና ህብረትና በቤተሰብ ደረጃ የሱፐርቪዥን ስራ ተሠርቶ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴያቸው ተገምግሟል ብለዋል።

በሱፐርቪዥኑ የፖለቲካና የአደረጃጀት እንዲሁም የምርጫ ምቹነትን ጨምሮ አዳዲስ የኢንሼቲቭ ስራዎች በተገቢው ምልከታ መደረጉን የገለፁት አቶ አለማየሁ በመንግስትና ህብረተሰብ ተሳትፎ የተሰሩ ማህበራዊ ልማቶች ተሞክሮ ሊሆኑ የሚችሉ መሆኑን አብራርተዋል።

አመራሩ በምርጫ ስራዎች ህዝቡ ያለው ግንዛቤ የበለጠ እንዲያሳድግ ሊሰራ ይገባል ያሉት አቶ አለማየሁ ለዚህም በቤተሰብ ደረጃ የሚሰሩ ስራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል በማለት አፅንዎት ሰጥተዋል።

በቀጣይም የድጋፍና ክትትል ስራዎች አጠናክሮ በመስራት ወደ ብልፅግና የሚደረገው ጉዞ ለማፋጠን በየደረጃዉ የሚገኘው አመራርና አባላት ግንባር ቀደም ሆነው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም የምርጫ ምቹነት 100% ማሳከት በማለት እየተሰራ ያለው ስራ እንደጅምር አበረታች መሆኑን አመላክተው አሁንም ፓርቲው ያስቀመጣቸውን መሰረታዊ የምርጫ ግቦች ለማሳካት የቅድመ ምርጫ ተግባራት በታቀደላቸው ጊዜ መፈፀም ያስፈልጋል ብለዋል።

የብልፅግና ፓርቲ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ነፃ ፣ፍትሃዊ፣በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያለውና ዲሞክራሲያዊ ለማድረግ ከወትሮው በተለየ መልኩ እየሰራ ነው ያሉት ኃላፊው በዞናችንም ይሄንን እውን ለማድረግ የሚያስችል መድላድል እንዳለ በሱፐርቪዥኑ ማረጋገጥ እንደተቻለ አስገንዝበዋል።

በጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ናስር ሀሰን በበኩላቸው የፓርቲ ተቋም ግንባታ ስራዎች ከቅንጫፍ ጽ/ቤት ጀምሮ እስከ ቤተሰብ ድረስ ያሉ አደረጃጆቶች ይበልጥ ተጠናክረው በመስራት እየተመዘገቡ ያሉ ለውጦች በዘላቂነት ሊያስቀጥሉ ይገባል ብለዋል ።

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊነት ፣ፍትሀዊነት ነፃ እና ተዓማኒነት እንዲኖረው አየተሰሩ ያሉ ስራዎች ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።

በሱፐርቪዥን የተለዩ ጠንካራ አፈፃፀሞች ማስቀጠልና ጉድለች ደግሞ ፈጥሮ በማረም የህዝቡ ፖለቲካዊ ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ላይ ይበልጥ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሁሉም መረባረብ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፈይሰል ሀሰን፣ የወረዳና ከተማ ደጋፊ አመራሮች ጨምሮ ሌሎችም ተሳትፈዋል።

Previous የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት በማሻሻል የህብረተሰቡን እርካታ ከፍ ለማድረግ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተገለፀ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo