የመንገዱ መገንባት የማዕከላዊ ኢትዮጵያን እና የኦሮሚያ ክልል ህዝቦችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስተጋብር እንደሚያጠናክር ተመላክቷል።

የኦሮሚያ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎችን የሚያገናኘው የቱሉ ቦሎ – ኬላ የመንገድ ፕሮጀክት የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ክቡር የክልላችን ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት በመካሄድ ላይ ነው።

ጥር 17/2018 (ወልቂጤ)

የመንገድ ፕሮጀክቱ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ የተገነባ ሲኾን፥ 81•1 ኪሎ ሜትር ይሸፍናል። የመንገድ ግንባታውን የቻይናው ሁናን ሁንዳ አከናውኖታል። ሀገር በቀሉ የተባበሩት የምህንድስና አማካሪዎች የግንባታውን ጥራት በመቆጣጠር እና በማማከር በኩል ተሳትፏል። ለፕሮጀክቱ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በፌደራል መንግሥት ወጪ ተደርጎበታል።

የመንገድ ፕሮጀክቱ መጠናቀቅ የኅብረተሰቡን የረጅም ጊዜ ጥያቄ ምላሽ የሰጠ ከመኾኑም ባሻገር፣ በርካታ ማኅበራዊ እና ምጣኔ-ሃብታዊ ጠቀሜታዎችን ያበረክታል።

Previous በግማሽ አመቱ ከ3 ቢሊየን 663 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በጀቶች ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉ መደረጉ የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አስታወቀ።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo