‎የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ፕሮግራም ማህበረሰቡ ለህክምና የሚያወጣውን ከፍተኛ ወጪ በመቀነስ ዜጎች በህመማቸው መጠን የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል:- የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ታደለ በቀለ

የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ፕሮግራም ማህበረሰቡ ለህክምና የሚያወጣውን ከፍተኛ ወጪ በመቀነስ ዜጎች በህመማቸው መጠን የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል:- የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ታደለ በቀለ

‎

‎ጥር 14/2018ዓ.ም [ወልቂጤ ]

‎

‎የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅህፈት ቤት የ2018 ዓመተ ምህረት የማዕጤመ ፕሮግራም አፈፃፀም ግብረ መልስ ከከተማ ጠቅላላ አመራር እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የግምገማ መድረክ አካሄደ።

‎

‎የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ታደለ በቀለ እንደገለፁት የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ፕሮግራም ማህበረሰቡ ለህክምና የሚያወጣውን ከፍተኛ ወጪ በመቀነስ ዜጎች በህመማቸው መጠን የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ሲሉ ተናግረዋል።

‎

‎በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ማዕከል ያደረገ ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የማዕጤመ ፕሮግራም ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

‎

‎ለጤና ዘርፍ መንግሥት ልዩ ትኩረት በመስጠት ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው በተለይ በማዕጤመ ፕሮግራም ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን ሁሉም በባለቤትነት ሊሰራ ይገባል ሲሉ አስረድተዋል።

‎

‎ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር የማዕጤመ ፕሮግራም ተግባራት በውጤት በመገምገም የተስተዋሉ ጉድለቶችን እየለዩ መስራት ይገባል ሲሉ አቶ ታደለ ተናግረዋል።

‎

‎በሚጠበቀው ልክ ውጤት ለማምጣት በቀሪ አጭር ጊዜያት የአዲስ ተመዝጋቢዎች እና የእድሳት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

‎

‎የአቅም ውስንነት ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን የማዕጤመ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ባለሀብቶች ሆኑ ሌሎችም በዚህ በጎ ተግባር ላይ በመሳተፍ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

‎

‎የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የጤና ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሙባረክ ዘይኑ እንደተናገሩት የማዕጤመ ፕሮግራም የሚጠበቀው ውጤት ለማምጣት ተግባራትን ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት በሀላፊነት መስራት ይገባል።

‎

‎በማዕጤመ ፕሮግራም ማህበረሰባችን ተጠቃሚ ለማድረግ ከምንሰራው ስራ ጎን ለጎን የእናቶችና ህፃናት ላይ ትኩረት አድርገን የሚሰሩ ሰራዎች አያይዘን ልንሰራ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

‎

‎በቀሪ 15 ቀን የማዕጤመ ፕሮግራም ማጠናቀቂያ ስራዎች አደረጃጀቶችን በማስፋት የነበሩብን ክፍቶች ለይተን ያሉን አጋጣሚዎች በአግባቡ ልንጠቀም ይገባል ሲሉ ሀላፊው አክለዋል ።

‎

‎የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አስራት ታደለ እንደገለፁት ህብረተሰባችንን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች በቅንጅት ልንሰራ ይገባል ብለዋል።

‎

‎ተግባራት በውጤት መታጀብ አለባቸው ያሉት አቶ አስራት ህዝቡን የሚጠቅሙ በጤና ዘርፍ መምጣት ያለበት ለውጥ ሁሉም በሀላፊነት ወስዶ መስራት ሲችል በመሆኑ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅብናል ሲሉም ጠቁመዋል።

‎

‎የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሰፋ ዘይኑ በበኩላቸው የማዕጤመ ፕሮግራም ተግባራት በሚገባ መምራትና ክፍተቶች መፈተሽ ተገቢ ነው ብለዋል።

‎

‎የመረጃ አደረጃጀት በማጠናከር ሰው ተኮር ስራዎች ላይ ሁሉም የድርሻውን ወስዶ ሊሰራም ይገባል ሲሉ ጠቁመዋል።

‎

‎በውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ባለፉት ጊዜያት በማዕጤመ ፕሮግራም ስራዎች በሚፈለገው ልክ ውጤት ያልተመዘገባቸው ተግባራትን እየለዩ በነበሩ ክፍተቶች ለውጤት መስራት ይገባል ብለዋል።

‎

‎የከተማችን ማህበረሰብ በቀሪው አጭር ጊዜ አዲስና ምዝገባና የእድሳት ስራ በአፋጣኝ በማድረግ በማአጤመ ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆን አለበት ሲሉ አክለዋል።

‎

Previous የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንደገለፁት የሀገሪቱ ብልጽግና ለማረጋገጥ የኢንዱስትሪው ዘርፍ ሚናው ከፍተኛ በመሆኑ መንግስት በዘርፉ የሚሰማሩ ባለሀብቶችን ለማበረታታት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo