የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንደገለፁት የሀገሪቱ ብልጽግና ለማረጋገጥ የኢንዱስትሪው ዘርፍ ሚናው ከፍተኛ በመሆኑ መንግስት በዘርፉ የሚሰማሩ ባለሀብቶችን ለማበረታታት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ብልጽግና ለማረጋገጥ የኢንዱስትሪው ዘርፍ ሚና የጎላ ነው፦ አቶ ላጫ ጋሩማ

ጥር 14/2018(ወልቂጤ)፦የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ “የኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት በማፋጠን የሀገራችን ብልጽግና እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል አመታዊ የኢንቨስትመንት ፎረም እና የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሄደ።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንደገለፁት የሀገሪቱ ብልጽግና ለማረጋገጥ የኢንዱስትሪው ዘርፍ ሚናው ከፍተኛ በመሆኑ መንግስት በዘርፉ የሚሰማሩ ባለሀብቶችን ለማበረታታት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

በልዩልዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የሚሰማሩ ባለሀብቶች ለማነቃቃት ካላስፈላጊ ቢሮክራሲ የፀዳ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ይደረጋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በተለያዩ ወረዳዎችና ከተሞች በቂ መሬት በማዘጋጀት መስጠት እንደተቻለም አስረድተዋል።

ባለሀብቶቹ የሚገጥማቸው የኤሌክትሪክ ሀይል ተደራሽነትና የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ለመፍታት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ ጋር በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ የገለፁት አቶ ላጫ በዚህም ውጤት እየተገኘ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዞኑ ባለሀብቶች በስፋት ከሚሰሩባቸው የኢንቨስትመንት ዘርፎች መካከል ግብርና ሰፊውን ድርሻ የሚይዝ ሲሆን በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ውጤታማ ለመሆን በባለሙያ የታገዘ ስራ መስራት እንደሚኖርባቸው ገልፀዋል።

እንደ አቶ ላጫ ገለፃ ባለሀብቶች የወሰዱት መሬት የአፈርና ውኃ ጥበቃ ስራ በማጠናከር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ዛፎች በመትከል ዘላቂ አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በየዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች የተረከቡት መሬት ሙሉ በሙሉ በማልማት ረገድ ክፍተት ያለባቸውን በመለየት የኢንቨስትመንት ውላቸው እንደሚሰረዝ አቶ ላጫ አስገንዝበዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አባስ መሀመድ በበኩላቸው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በሚፈለገው ደረጃ ለማሳደግ የኢንቨስትመንት መስፋፋት ሚናው የጎላ በመሆኑ በኢንዱስትሩ ዘርፍ የሚሰማሩ ባለሀብቶች ለማበረታታት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

ባለሀብቶች በየዘረፋቸው በመደራጀት ያላቸውን አቅም ለማሳደግ የሚያስፈልጋቸውን መሰረተ ልማት እንዲያሟሉ ያስችላቸዋል ያሉት ኃላፊው ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት የፋይናንስ አቅም እንዲኖራቸው የብድር አቅርቦት ትስስር መፈጠር ይኖርባቸዋል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ አመተሩፍ ሁሴን እንደገለፁት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የሀገራችንን ብልፅግና ለማፋጠን የግል ባለሀብቱን የሚያበረታታና የኢንዱስትሪ ልማት ሊያፋጥኑ የሚችሉ የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች ማከናወን መቻሉ ገልፀዋል።

በዞኑ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች አበረታች ሲሆኑ ከ19 ነጥብ 8 ቢሊዮን በላይ ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 344 ባለሀብቶች ፈቃድ ተሰጥቷቸው ወደ ተገባር ገብተዋል።

የኢንቨስትመንት መስፋፋት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው የገለፁት ኃላፊዋ ፕሮጀክቶቹ 31 ሺህ 276 ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ችለዋል።

ፕሮጀክቶቹ በሚገኙባቸው አካባቢዎች ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በቴክኖሎጂ ሽግግርና በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ማህበራዊ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ኃላፊዋ ገልፀዋል።

አክለውም ኃላፊዋ ወደ ውጭ በሚላኩ በግብርናው ዘርፍ ውጤቶች የተሰማሩ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በአማካይ በየአመቱ 8 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኙ መሆናቸውንም ገልፀዋል።

የፎረሙ ታዳሚዎች ዞኑ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ባለሀብቶችን እያበረታታ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት በማለት የመብራት መሰረተ ልማት አለመስፋፋት እና ከተቋሙ በግዢ የሚጠየቁ ትራንስፎርመሮች ምላሽ ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ነው

Previous በ”አንትሮሽት” በእናቶች ቀን ልጆች ለእናታቸው እንዲሁም ባል ለሚስቱ ያላቸውን ፍቅርና አክብሮት የሚገልፁበት፤ ምስጋናቸውን የሚያቀርቡበት በዓል ነው።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo