“የገቢ አሰባሰብ ስራ የብልፅግና ጉዟችንን የሚያፋጥን የራስን አቅም የመገንቢያ ቁልፍ መሳሪያ ነው” የጉራጌ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል:-

“የገቢ አሰባሰብ ስራ የብልፅግና ጉዟችንን የሚያፋጥን የራስን አቅም የመገንቢያ ቁልፍ መሳሪያ ነው” የጉራጌ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል:-

ታህሳስ 27/2018(ወልቂጤ) የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል የዞኑን የልማት ግቦች ለማሳካት የገቢ አሰባሰብ ስራ በታህሳስ ወር 60% የማድረስ ግብ ለማሳካትና ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ የወልቂጤ ከተማ የፊት አመራሮች፤ የማዘጋጃና የገቢ ማኔጅመንት አካላት በተገኙበት ግምገማ አካሄደዋል።

በግምገማው ወቅት ኃላፊው እንደገለጹት፤ የብልፅግና ፓርቲ ዋነኛ ራዕይ ለማሳካት የኢኮኖሚ ነፃነትን ማረጋገጥና በራስ አቅም የሚመራ የልማት ስራ መስራት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የውስጥ ገቢያችንን በአግባቡ በመሰብሰብ ህዝቡ በየደረጃው የሚያነሳቸው የልማት ፍላጎቶች ማሳካትና የጀመርናቸውን ካፒታል ፕሮጀክቶች ማጠናቀቅ ይኖርብናል ብለዋል።

ሀላፊው አያይዘውም ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ ብቻ ሳይሆን፣ የተሰበሰበው ሀብት ለታለመለት የህዝብ አገልግሎትና መሠረተ ልማት መዋሉን ማረጋገጥ የብልፅግና መገለጫ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

በዞኑ በእስካሁን ሂደት በያዝነው ወር እንደ ዞን ከ550 ሚሊዮን ብር በላይ የተሰበሰበ ቢሆንም በመደበኛና ማዘጋጃ በታህሳስ ወር 1.16 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ከተቀመጠው ግብ አንፃር ዝቅተኛ አፈፃፀም ላይ ይገኛል ብለዋል።

በመጨረሻም፣ የዞኑ ዋና ተጠሪ “ብልፅግና የሚረጋገጠው በተግባርና በውጤት ነው” ስለሆነም የየደረጃው አመራር የገቢ አሰባሰብ ስራውን እንደ ፖለቲካዊ ግዴታ በመቁጠር ለተቀመጠው ግብ ስኬት በትጋት እንዲሰራ አሳስበዋል።

የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር የገቢ አሰባሰብ ስራ የሁሉ ልማቶቾ መሳካት ቁልፍ ተግባር እንደሆነ አመላክተው በከተማው ገቢ አሟጦ ለመሰብሰብ የሚያስችል ስራ ከምንጊዜውም በላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የገቢዎች ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ደግፌ መልስ በመድረኩ ተገኝተው እንዳሉት በዞኑ አየተሰራው ያለው የገቢ አሰባሰብ ስራ አበረታች መሆኑ አስቀምጠው በቀጣይ ግቡን ለማሳካት ከመደበኛ ገቢ አንፃር የቫት ገቢ ጠንካራ ክትትል እንዲደረግ እና የማዘጋጃ ገቢ በቅንጅት እንዲሰራ አሳስበዋል።

በመድረኩ የዞኑ ገቢዎች መምሪያ ሀላፊ አቶ ሚነወር ሀያቱ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ፣ የወልቂጤ ከተማ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ታደለ በቀለ ጨምሮ የዞን፣ የከተማው የፊት አመራሮች የማዘጋጃ ማኔጅመንት አካላትና ሌሎች የሚመለከታቸው ተገኝተዋል።

የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

Previous የጉራጌ ዞን ሔተነ ያትየድርም የቹቻ መምርያ ኣላፊ አበቃጥ አበራ ወንድሙ የባሮኸማ የዞን የመንግስት ቢተረነ ንወሻት ዋፍካሁና የጉራጊና ፊንሸ ቶዋትኸኸር ምዬ ምዬ ፊንሸዌ በኮምፒውተርም በስልክ መምር ይጠፊኸማ ሐሮት ቶጥብጥ በፏር ቢቸንዌ በሜና ቤትዌ ይቾችቧኸማ ዮዋሜ ፎረታ ንቅየው።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo