ፋይዳ መታወቂያና ኢቲዮ ኮደርስ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ያለው ሚና የጎላ በመሆኑ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆን አመራሩ የትኩረት አጀንዳው አድርጎ መምራት እንዳለበት ተገለጸ።

ፋይዳ መታወቂያና ኢቲዮ ኮደርስ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ያለው ሚና የጎላ በመሆኑ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆን አመራሩ የትኩረት አጀንዳው አድርጎ መምራት እንዳለበት ተገለጸ።

መስከረም 30/2018ዓ.ም[ወከልቂጤ ]

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር “ዲጂታል ማህበራዊ ግንኙነት ለሀገራችን ሁለንተናዊ ብልጽግና “በሚልየ2017 የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባና የኢትዮ ኮደርስ አፈጻጸምና የ2018 አቅጣጫ ላይ ያተኮረ የንቅናቄ መድረክ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ ተካሄደ።

ሀገራችን ኢትዮጲያ ዲጂታል ኢትዮጲያ ን ለመገንባት ካመጣው ኢኒሼቲቭ ኢትዮ ኮደርስ ና ፋይዳ መታወቂያ ተጠቃሽ መሆናቸውን አንስተው የዘመነች ኢትዮጲያን ለመገንባት ና ለመቀላቀል ከቴክኖሎጂው መዋሀድ ያስፈልጋል ሲሉ የወልቂጤ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ የሆኑት አቶ ታደለ በቀለ አስረድተዋል ።

በአሁኑ ሰዓት እየተበራከተ የመጣው የባንክ ዝርፊያዎች ለመከላከል የመንግስት ኢኒሼቲቭ በመከተል በቴክኖሎጂው ዘርፍ ከጊዜው ጋር አብረን በመዘመን ውጤታማና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት አሰጣጥ እናጎልብትም ሲሉ አቶ ታደለ አመላክተዋል ።

ወጣቱ ትዉልድ የቴክኖሎጂ ኢንሸቲቮችን የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና እና ዲጂታል ፋይዳ መታዉቂያ በመውሰድ ተጠቃሚ እንዲሆን በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልጸው እንደ ሀገር የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑንም አንስተዋል።

በከተማውም ሆነ እንደሀገር በቀጣይ የሚሰጡ አገልግሎቶች በብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ብቻ የሚሰጡበት ሁኔታ ስለሚኖር ማንኛውም እድሜው ከ 5 ዓመት በላይ የሆነው ኢትዮጵያዊ ዲጂታል መታወቂያን እንዲያወጣ ሲሉ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የጤና ጽህፈትሰ ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ሙባረክ ዘይኑ አብራርተዋል ።

የሀገር ኢንሼቲቨ የሆነው ኢትዮ ኮደርስና ፋይዳ መታወቂያ የውዴታ ግዴታ መሆኑን አንስተው ትምህርት ተቋማት ና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ አርአያ በመሆን ሌሎችን ማቀላቀል ተገቢ ነውም ብለዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን የሚያስችል ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ወጣቶች፣ መምህራን፣ሴቶች፣ የማህበር አደረጃጀቶች ና ስልጠናውን ያልወሰዱ ባለሙያዎች በስልጠና እንዲሳተፉ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም አመላክተዋል።

በቀጣይ በተለያዩ ተቋም የሚሰጡ አገልግሎቶች ከብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ጋር በማስተሳሰር የሚሰጡበት ሁኔታ ስለሚኖር ማንኛውም እድሜው ከ 5 ዓመት በላይ የሆነው ኢትዮጵያዊ ዲጂታል መታወቂያን እንዲያወጣ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የወልቂጤ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሰፋ ዘይኑ በንግግራቸው ፋይዳ መታወቂያና ኢቲዮ ኮደርስ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ያለው ሚና የጎላ በመሆኑ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆን አመራሩ የትኩረት አጀንዳው አድርጎ መምራት እንዳለበት ተናግረዋል።

አቶ ሰፋ አያይዘውም በ2018 191 ሺህ የማህበረሰባችን ክፍል ከህጻን እስከ አዋቂ ፋይዳ መታወቂያ ሊኖረው እንደሚገባም ገልጸዋል።

ኢትዮ ፖስትና ኢትዮ ቴሌ ባለሙያዎች ሁሉም በየደረጃው ኬት ተዘጋጅቶ በመመዝገብ የነበሩ ተግዳሮቶችን መሻገር ያስፈልጋል ሲሉ ጠቁመዋል ።

በ2017 እቅድ አፈጻጸምከ200 ሺህ በላይ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸው ያጋጠሙ ችግሮችን በማሻሻል የነበሩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል መስራት ያስፈልጋል ሲሉ አሳስበዋል።

ከዚህ ቀደም ለምዝገባ የትምህርት ዘርፉ ላይ የገጠመ ችግር መኖሩን አስታውሰው አሁን ባለድርሻ አካሉ በየደረጃው ያለው ማህበረሰቡን ግንዛቤ ፈጥሮ ወደ መመዝገቢያ ማዕከል ሲመጡ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘት አለበት ያሉት ደግሞ የወልቂጤ ከተማ ምክርቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ መንዚላት አህመድ ናቸው።

የተለወጠች አለም ላይ ሆኖ ለውጥ አለመቀበል አይቻልም ያሉት አፈ-ጉባኤዋ የዲጂታል መታወቂያ እድሜያቸው ከ5 አመት ጀምሮ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ኪቶችን አስፍቶ በመስራት ማሳካት ይኖርብናልም ብለዋል።

ከወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጽህፈት ቤትና

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ሀላፊዎች የ2017 የዲጂታል መታወቂያ አፈጻጸምና የቀጣይ አቅጣጫ በተመለከተ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በውይይቱ በፋይዳ መታወቂያ አሰጣጥ ዙሪያ በርካታ ሀሳቦችና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከመድረኩና ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል ።

ከተሳታፊዎቹ በሰጡት አስተያየትም በዚህ ኢኒሼቲቭ የታቀደው እቅድ ለማሳካት በተለያዩ ማህበራዊ መሰረቶች አጋጣሚ ና ለአልግሎት በሚመጡ ተገልጋዮች ግንዛቤ በመፍጠር እቅዱ ውጤታማ ለማድረግ እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

በስራ ባህሪያቸው መሰረት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጡን ከፋይዳ መታወቂያ በማስተሳሰር የበኩላቸውን ሚና እንሚወጡም ገልጸዋል።

በውይይቱ በፋይዳ መታወቂያ አሰጣጥ ዙሪያ በርካታ ሀሳቦችና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከመድረኩና ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል ።

Previous የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት፣ በሁለት ዘርፍ አንደኛ በመዉጣት የዋንጫ እና ልዩ ተሸላሚ ሆኖአል።

Leave Your Comment

የቋንቋ አማራጭ

🇺🇸 English
🇪🇹 አማርኛ
🇪🇹 Afan Oromo